TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዋልድባ! በዋልድባ ገዳም መነኮሳት አባቶች ላይ ቀርቦ የነበረው ክስ አለመቋረጡ ተሰምቷል። በተለያዩ የማህባረሰብ ሚዲዎች የመነኮሳቱ ክስ ዛሬ ተቋርጧል በሚል መረጃዎች ሲሰራጩ ቢውልም ጠበቃቸው ለቪኦኤ በሰጡት ቃል የመነኮሳቱ ክስ አለመቋረጡን ገልፀዋል። እንደ ጠበቃቸው ገለፃ የክስ ሂደቱ እንደሚቋረጥ ከፍርድ ቤት አካባቢ መረጃ ደርሷቸው የነበር ቢሆንም በዛሬው እለት ከዋለው ችሎት ክሱ አለመቋረጡን ሊረዱ ችለዋል።

በተጨማሪ፦ በዛሬው እለት መነኮሳቱ ለችሎት ቀርበው በእስር ቤት ውስጥ ሃይማኖት ልብሳቸውን እንዲያወልቁ መገደዳቸውን እንዲሁም መደብደባቸውን ተናግረዋል።

#VOAamharic
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቦንብ ፈንድቶ ቢያንስ 14 ሰዎች ሞቱ!

በአፍጋኒስታን መዲና ካቡል በሚገኘው የፖሊስ ጽህፈት ቤት አጠገብ ዛሬ መኪና ውስጥ የተጠመደ ከባድ ቦምብ ፍንድቶ ቢያንስ 14 ሰዎች መገደላቸውን የሀገሪቱ ባለሥልጣኖች ገልፀዋል።

Via #VOAamharic
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰላም ማረጋገጥ ከተቻለ ወታደራዊ ዕዙ ግዳጁን በሁለት ወር ውስጥ አጠናቅቆ ይወጣል፤ የማይረጋጋ ከሆነ ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጭምር ሊታወጅ ይችላል!

በሃዋሳ ከተማ አሳቻ ሰዓትና ቦታ በመጠበቅ የሚፈፀሙ የወንጀል ድርጊቶችና የሰዎች ማንንት ላይ ያተኮሩ ትንኮሳዎች ነዋሪው ተርጋግቶ እንዳይኖርና ስጋት ውስጥ እንዲገባ አድርጓል ሲሉ የከተማዪቱ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
 
ክልሉን እያስተዳደረ ካለው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አስፈፃሚ ዕዝ ጋር የከተማዪቱ ነዋሪዎች ተወካዮች በየተወያዩበት ወቅት ወታደራዊው ዕዝ እንዲያበቃና የመከላከያ ሠራዊትም ከከተማው #እንዲወጣ የጠየቁ ነበሩ።

በሌላ በኩል ደግሞ “የለም ሠራዊቱ መቆየት አለበት፤ ሰላም ያገኘነው ወታደራዊ ዕዙ፣ የመከላከያ ሠራዊትና ፌዴራል ፖሊስ ከተማዪን ከተቆጣጠሩ ወዲህ ነው” ያሉም ነበሩ። ሰላም ማረጋገጥ ከተቻለ ወታደራዊ ዕዙ ግዳጁን በሁለት ወር ውስጥ አጠናቅቆ እንደሚወጣ፤ የማይረጋጋ ከሆነ ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጭምር ሊታወጅ እንድሚችል ዕዙ አስታውቋል።

Via #VOAamharic
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከ4 ቀን በኃላ ህይወቱ የተረፈው ወጣት!

የ28 ዓመቱ የኮምቦድያ ወጣት ሰመ ቦራ #ለአራት ቀን በድንጋይ ዋሻ ውስጥ ቆይቶ በህይወት ተርፏል፡፡ አደጋው የተፈጠረው በዋሻው ውስጥ የሌሊት ወፍ ኩስ እየሰበሰበ በነበረበት ጊዜ ነው፡፡ የሀገሬው ሰው የሌሊት ወፍ ኩስ ውስጥ የሚገኝ ሻጋታ ለመድኃኒትነት ይጠቅማል የሚል ዕምነት አላቸው፡፡

Via #VOAAmharic
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በምዕራብ ጉጂ ዞንና በደቡብ ክልል አራት ሰዎች ተገደሉ!

በምዕራብ ጉጂ ዞን #ገላና ወረዳና በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ፣ ባለፉት ሁለት ቀናት በደረሱ ጥቃቶች አራት ሰዎች እንደተገደሉ የወረዳዎቹ ባለሥልጣናት ተናገሩ፡፡ በጥቃቱ 5 ሰዎች መቁሰላቸውም ታውቋል።

Via #VOAAmharic
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አቶ ጌታቸው አሰፋ ለእውቅና የምስክር ወረቀት ወደመድረኩ ተጠርተው የነበረ ቢሆንም ቀርበው ሲወስዱ አልታዩም!"

የህወሓት 45ኛ ዓመት የምስረታ "የካቲት 11" በዓል ምክንያት በማድረግም ለነባር ታጋዮች ዕውቅና ተሰጥቷል።

- በትጥቅ ትግሉ ጊዜ ለነበሩ የህወሓት ታጋዮች የእውቅና መርሃ ግብር በትለንትነው ዕለት አዘጋጅቶ ነበር። ፓርቲውን ለመሰረቱ፣ ለስራ አስፈፃሚና በማዕከላይ ኮሚቴዎች እንዲሁም የቁጥጥር ኮሚሽን አመራር ለነበሩና ላሉ ታጋዮች እውቅና ሰጥቷል።

- ትላንት በነበረው የእውቅና መስጠት መርሃ ግብር አቶ ስዩም መስፍን፣ አቶ ስዬ አብርሃ፣ ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤን ጨምሮ የፓርቲው ነባር አመራሮች ተገኝተው ነበር።

- በመርሃ ግብሩ ላይ በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ እንደሚፈልጉ በተደጋጋሚ የሚገለፀው የቀድሞው የመረጃና ደህንነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ ለእውቅና የምስክር ወረቀት ወደመድረኩ ተጠርተው የነበረ ቢሆንም ቀርበው ሲወስዱ አልታዩም።

ተጨማሪ መረጃ፦

- ህወሓት እስካሁን ድረስ ለ91,000 ታጋዮች የእውቅና ምስክር ወረቀት ሰጥቷል።

- የህወሓት 45ኛ አመት ምስረታን ምክንያት በማድረግ በመቐለ ከተማ አዳዲስ የመንገድ ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል።

- መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።

- ዛሬ በመቐለ የጎዳና ላይ ትርኢት ቀርቧል።

- ሰኔ 15 የተገደሉት የሜጀር ጀነራል ገዛኢ ኣበራ የመታሰቢያ ሃውልት ትላንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል እና ቤተሰቦቻቸው ተመርቋል።

#VOAAmharic
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia