TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
አሜሪካ 500 ሺህ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎችን እየገነባች እንደሆነ ፕሬዜዳንቷ ገልፀዋል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደራቸው በመላ አገሪቱ 500,000 የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎችን እየገነባ እንደሆነ አሳውቀዋል። በአሜሪካ የኤሌክትሪክ መኪና ተገልጋዮች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ ሲሆን ሀገሪቱም ይህንን በእጅጉ እያበረታታች ነው። በአሜሪካ…
#EV

አሁን ላይ በተለያዩ የዓለማችን ሀገራት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በብዛት ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛሉ።

ከዓለማችን ሀገራት መካከል #አሜሪካ በ2050 ከካርቦን-ነፃ እንድትሆን አሽከርካሪዎች በነዳጅ ኃይል ከሚሰሩ ወደ ኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች እንዲቀይሩ ማድረግ ወሳኝ እንደሆነ ታምናለች።

በ2030 ከአዳዲስ የመኪና ሽያጭ ግማሹ የኤሌክትሪክ/ ሃይብሪድ ተሽከርካሪዎች እንዲሆኑ ግብ አላት፤ እ.ኤ.አ. በ2030 ግማሹ ኤሌክትሪክ ከሆኑ፣ በ2050 በአሜሪካ ጎዳናዎች ከሚሽከረከሩት መኪኖች ከ60-70 በመቶ የኤሌክትሪክ / ሃይብሪድ ተሽከርካሪዎች ሊሸፍኑ ይችላሉ።

ለዚህም የመኪና ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች በስፋት እየተገነቡ ይገኛሉ (እስከ 2030 ደረስ 500,000 የመገባት እቅድ አላት) ።

አሁን ላይ አሜሪካ ምን ያህል ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች አሏት ?

(እንደ ኤስ ኤንድ ፒ ሞቢሊቲ መረጃ)

- 126,500 ደረጃ ሁለት (የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በ5 ሰዓት ሙሉ የሚያደርጉ) ጣቢያዎች፤

- 20,431 ደረጃ 3 (ከ15-20 ደቂቃ ውስጥ ተሽከርካሪዎችን 80% የሚያደርጉ)  ጣቢያዎች፤

- 16,822 የቴስላ ሱፐርቻርጀር እና የቴስላ ቻርጅ ማድረጊያ መዳረሻዎች አሉ።

ኤስ ኤንድ ፒ ሞቢሊቲ፤ በ2025 እስከ 7.8 ሚሊዮን በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በአሜሪካ ጎዳናዎች ላይ ሊኖሩ እንደሚችሉ ተንብዮ ለዚህም 700,000 ደረጃ ሁለት እና 70,000 ሶስት የቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች ሊኖሩ ይገባል ብሏል።

በ2030 ደግሞ 28.3 ሚሊዮን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ይኖራሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ለዚህም 2.13 ሚሊዮን የደረጃ 2 እና 170,000 ደረጃ 3 የቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች ያስፈልጋሉ።

ይሄ የመኪና ባለቤቶች በቤታቸው ከሚገጥሙት የቻርጅ ማድረጊያ ተጨማሪ ነው።

@tikvahethiopia