ቢቢሲ በቻይና ታገደ !
ቻይናን በተመለከተ የሚሰራቸው ዘገባዎች አድሎአዊ እና ሀሰተኛ ናቸው በሚል ነው ቢቢሲ የታገደው፡፡
የቻይናው የብሮድካስቲንግ ተቆጣጣሪ ‘ቢቢሲ ወርልድ ኒውስ’ን በሀገሪቱ ከባድ የይዘት ጥሰት ፈጽሟል በሚል ከአየር ላይ ማውረዱን ይፋ አድርጓል፡፡
ቻይናን በተመለከተ ቢቢሲ የሚሰራቸው ዘገባዎች የዜና ዘገባ እውነተኛ እና ከአድሎ የነጻ መሆን አለበት ከሚሉት መስፈርቶች ጋር የሚቃረን መሆኑ የተገለጸ ሲሆን እና የቻይናን ብሄራዊ ጥቅሞች እና የህዝቡን አብሮነት የሚጻረር እንደሆነም የሀገሪቱ ብሮድካስቲንግ ተቆጣጣሪ አስታውቋል፡፡
“ቻናሉ በቻይና እንደ ባህር ማዶ ቻናል ለማሰራጨት የሚያስፈልጉትን መስፈርቶች ማሟላት ባለመቻሉ ፣ ቢቢሲ ወርልድ ኒውስ በቻይና ግዛት ውስጥ አገልግሎቱን እንዲቀጥል አይፈቀደለትም፡፡
ብሔራዊ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን አስተዳደር ለአዲሱ ዓመት የቢቢሲን የስርጭት ጥያቄ አይቀበልም” ብሏል ተቆጣጣሪ መስሪያ ቤቱ በመግለጫው፡፡
የሆንግ ኮንግ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ከአርብ ጀምሮ የ’ቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ’ን እና የቢቢሲ ሳምንታዊ ዜናን እንደማያሰራጭ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
የቢቢሲ ቃል አቀባይ ለCNN ፥ “የቻይና ባለሥልጣናት ይህንን እርምጃ ለመውሰድ በመወሰናቸው ቅር ብሎናል ፤ ቢቢሲ በዓለም ላይ እምነት የሚጣልበት ዓለም አቀፍ የዜና አውታር ሲሆን የዓለም ዘገባዎችን በፍትሃዊነት ፣ በገለልተኝነት የሚያቀርብ ነው” ብለዋል፡፡
የቻይናው ዓለም አቀፍ የቴሌቪዥን ኔትዎርክ "CGTN" ም በብሪታኒያ እንዳይሰራጭ ከሳምንት በፊት ታግዷል፡፡ ቻይና እና ብሪታንያ ከሆንግ ኮንግ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የሆነ አለመግባባት መፍጠራቸው ይታወቃል፡፡
ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#Woldia "...የታሪፍ ማሻሻያ ይደረግለን" - የባጃጅ አሽከርካሪዎች ከሰሞኑን በተደረገ ቤንዚንና ናፍጣ ዋጋ ጭማሪ ዙሪያ ከወልዲያ ከተማ ባጃጅ አሽከርካሪዎች ጋር ዛሬ ውይይት መደረጉን ወልዲያ ኮሚኒኬሽን አሳውቋል። በውይይቱ ከቤንዚን እና ናፍጣ የዋጋ ጭማሪ በተጨማሪም የተሽከርካሪዎች የመለዋወጫ እቃ መጨመሩ በነበረው ታሪፍ ለመስራት አላስቻለንም ያሉ አሽከርካሪዎቹ የታሪፍ ማሻሻያ እንዲደረግላቸው…
በወልድያ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍ ተሻሻለ፡፡
የወልዲያ ከተማ የትራንስፖርት ዋና ሥራ ክፍል ከቤኒዚን የዋጋ ጭማሪ ጋር ተያይዞ የባጃጅ ታሪፍን መሻሻሉን በዛሬው ዕለት አስታውቋል፡፡
የተሻሻለው ታሪፍ ከላይ ተያይዟል።
ከታሪፍ ውጭ ለሚደረግ ህገ-ወጥ ምዝበራ ተገልጋዮች መብታቸውን ለማስከበር ከተሟላ መረጃ ጋር ጥቆማ በስልክ በአካላም መስጠት የሚችሉ መሆኑን ተገልጿል ፤ ለስልክ ጥቆማ : 033-331-04-32 መጠቀም ይቻላል ተብሏል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ኡመር ከጅግጅጋ ወደ ቀብሪደሃር ከተማ አቀኑ !
የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ኡመር የተመራው የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ከጅግጅጋ ከተማ ወደ ቀብሪደሃር ከተማ አቅንተዋል።
ፕሬዝዳንት ሙስጠፌ በነገው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ተማሪዎችን የሚያስመሪቀው የቀብሪደሃር ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች የምረቃ ሥነ ስርዓት ላይ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።
የቀብሪደሃር ዩኒቨርስቲ ሶስተኛው ትውልድ ከሚባሉት ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን በሶማሊ ክልልም ከጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ ቀጥሎ ሁለተኛው ዩኒቨርስቲ ነው። (SRTV)

በአለታ ወንዶ ትላንት በደረሰ እሳት አደጋ እስካሁን መጠኑ ያልታወቀ ንብረት ወድሟል !
ትላንት ከቀኑ 9:00 በአለታ ወንዶ ከተማ መሳለሚያ ቀበሌ ልዩ ስሙ መለቦ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ድንገት በተፈጠረ እሳት ለግዜዉ ግምቱ ያልታወቀ ንብረት እና የሱቆች ቃጠሎ ዉድመት ደርሷል።
ቃጠሎዉ ከባድ ከመሆኑ አንፃር የከተማዉ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ በቁጥጥር ስር ባያዉለው ኖሮ በከተማዉ ለይ ከፍተኛ ጉዳት ሊደርስ ይችል ነበር።
የአለታ ወንዶ ከተማ አስተዳደር አደጋዉን ለመቆጣጠር ዋጋ ለከፈለው ለአለታ ወንዶ ህዝብ በይፋ አክብሮቱን እና ምስጋናውን አቅርቧል።

አሜሪካና UN የኢትዮጵያን ጥረት ለመደገፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት ዳግም አረጋገጡ !
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት አንቶኒ ብሊንከን ከተባበሩት መንግስታት (UN) ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር በትላንትናው ዕለት በስልክ ባደረጉት የትውውቅ ቆይታ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረገጹ እንዳስታወቀው ፣ ሁለቱ ግለሰቦች ከተወያዩባቸው ጉዳዮች መካከል በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ያለው ወቅታዊ ጉዳይ ይገኝበታል፡፡
ኢትዮጵያን በተመለከተው ውይይታቸው ፣ ሁለቱም በትግራይ ክልል ለተፈጠረው ቀውስ ምላሽ ለመስጠት የኢትዮጵያን ጥረት ለመደገፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል፡፡
[U.S. Department of State , AlIN News]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት አንቶኒ ብሊንከን ከተባበሩት መንግስታት (UN) ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር በትላንትናው ዕለት በስልክ ባደረጉት የትውውቅ ቆይታ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረገጹ እንዳስታወቀው ፣ ሁለቱ ግለሰቦች ከተወያዩባቸው ጉዳዮች መካከል በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ያለው ወቅታዊ ጉዳይ ይገኝበታል፡፡
ኢትዮጵያን በተመለከተው ውይይታቸው ፣ ሁለቱም በትግራይ ክልል ለተፈጠረው ቀውስ ምላሽ ለመስጠት የኢትዮጵያን ጥረት ለመደገፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል፡፡
[U.S. Department of State , AlIN News]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የትግራይ_ክልል_ነዋሪዎች_ስለሚገኙበት_ወቅታዊ_ሁኔታ.pdf
ፆታዊ ጥቃት በትግራይ #EHRC :
በትግራይ ክልል የተከሰተው ጦርነት እና የቀድሞ መስተዳደር መፍረስ ተከትሎ ፆታዊ ጥቃቶች ታፈፅመዋል።
በመቐለ ከሚገኙ ህክምና ባለሞያዎች እንዲሁም ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ በተገኙ መረጃዎች መሰረት ፥ ባለፉት 2 ወራት ብቻ በመቐለ ሆስፒታል 52 ፣ በአይደር ሆስፒታል 27 ፣ በአዲግራት ሆስፒታል 22 ፣ ዓዲግራት ሆስፒታል 22 ፣ በውቅሮ ሆስፒታል 7 በአጠቃላይ 108 የአስገድዶ መድፈር ጥቃቶች ለጤና ተቋማት ሪፖርት ተደርገዋል።
ፆታዊ ጥቃት ተጎጂዎች ወንጀሉን ለማሳወቅ እና ህክምና እርዳታ ለማግኘት የሚሄዱባቸው እንደ ፖሊስ ጣቢያ እና ጤና ጣቢያ ያሉ ተቋማት በአንዳንድ አካባቢዎች ፈርሰው በመቆየታቸው ሪፖርት የተደረጉ ጥቃቶች ቁጥር ትክክለኛውን የጉዳት መጠንና ስፋት እንደማያዳይ እና ፆታዊ ጥቃት መጠኑ ከዚህ የበለጠ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።
እንደጤና ዘርፉ ሰራተኞች ማብራሪያ በክልሉ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ የጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ የህክምባ እርዳታ ፈላጊዎች በምሽት ወደ ጤና ተቋማት እንዳይሄዱ እንቅፋት መሆኑ አሳሳቢ ነው።
* የሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ በትግራይ የፆታዊ ጥቃቶችን የሚያጣራ ግብረ ኃይል ወደ መቐለ ልኮ ነበር ፥ ዛሬ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዝርዝር መረጃ ባያወጣም በክልሉ ፆታዊ ጥቃቶች መኖራቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።
* ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ልኮት በነበረው መረጃ በትግራይ ፆታዊ ጥቃቶች እየተፈፀሙ መሆኑን ገልፆ ነበር።
* UNም በትግራይ ፆታዊ ጥቃት/በሴቶች ላይ አስገድዶ መደፈር መፈፀሙን የሚገልፁ መረጃዎች እንዳሉት መግለፁን ይታወሳል።

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ መግለጫ :
ኦፌኮ "ለሚጠፋ የዜጎቻችንና አባሎቻችን ሕይወት መንግስት ኃላፊነቱን ይወስዳል" ሲል መግለጫ አወጣ።
ፓርቲው በሀገሪቱ ሕግ መሠረት ተመዝግቦ እና ዓላማውን በሠላማዊ አግባብ ብቻ ታግሎ ለማሳካት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ገልጿል።
የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ በመግለጫው ፥ "ፖሊሲያችን ፣ የፖለቲካ ፕሮግራማችን ፣ አቋማችን በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነትን በማግኘቱ ምቾት ያልተሰማው ገዥው ፓርቲ (ኢህአዴግ/ብልፅግና) በተለይ ከ2005 ጀምሮ አባሎቻችን ደጋፊዎቻችንን በአሸባሪነት በመፈረጅ ክስ መስርቶ ሲያንገላታ ከቆየ በኋላ የሞቱት ሞተው በሕይወት የተረፉትና በየእስር ቤቶች ፊዳቸውን ሲቆጥሩ የነበሩት ቄሮ/ቃሬ በአጠቃላይ ሕብረተሰባችን በከፈሉት መስዋዕትነት በ2010 ዓም አጋማሽ በኋላ ሊፈቱ ችለዋል" ሲል አስታውሷል።
ፓርቲው አክሎም፥ "ከዚሁ ጊዜ በኋላ ለረጅም ጊዜ ስንመኘው የነበረው ዴሞክራሲ ሰፍኖ አዲስቷ ኢትዮጵያን እንገነባለን ብለን ተስፋ የሰነቅን ቢሆንም፤ከ2011 አጋማሽ በኋላ በአገረሸው የብልፅግና ፓርቲ ጭፍን የማሳደድ፣ የማሰርና የመግደል እርምጃዎች የተነሳ አንዳች ወንጀል ያልፈጸሙ ከከፍተኛ አካል ጀምሮ እስከ ታችኛው እርከን ድረስ የሚገኙ አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን የሌለ የወንጀል ታፔላ ተለጥፎባቸው እስር ቤቶች እንዲታጎሩ በመደረጋቸው፤ ተስፋችን ሟሸሸ፤ የሕዝቦችን መብትና ነፃነት ለማስከበር ሌላ የትግል ምዕራፍ እንዲካሄድም ጠይቋል" ብሏል።
ኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ የታሳሪ አባሎቹና ወገኖቹ ትግል የግላቸው ወይም የፓርቲውን ፍላጎት ለማስጠበቅ እንዳልሆነ ገልጾ ከ15 ቀናት በፊት የጀመሩት የረሃብ አድማ በሕይወታቸው ላይ "ከፍተኛ አደጋ" እንዲያዣንብብ ማደረጉን አሳውቋል።
* ተጨማሪ የመግለጫው ሃሳብ ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአንዳንድ አግልግሎት ላይ የዋጋ ጭማሪ ማድረጉን አስታወቀ !
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአንዳንድ የአገልግሎት ዋጋዎች ላይ የማሻሻያ ጭማሪ ማድረጉን አስታውቋል።
ባንኩ ጭማሪውን ለማድረግ የተገደደው ባለፉት 5 ዓመታት የባንኩ እድገት በአማካይ 26 በመቶ በመሆኑ ሂደቱ እየቀነሰ በመምጣቱ መሆኑን የባንኩ ፕሬዝደንት አቶ አቤ ሳኖ ዛሬ አስታውቀዋል።
በዚህም የኮርፖሬት ቦንድ የብድር ወለድ 8 በመቶ የነበረው 9 በመቶ ደርሷል።
ለቤቶች ልማት በ9.5 በመቶ የብድር ወለድ ይሰጥ የነበረ ሲሆን የነበረው 10.5 በመቶ ተደርጓል።
ለውጭ ምንዛሪ አገልግሎትም በ90 ቀናት ወይም በአንድ ፔሬድ የነበረው 5.5 በመቶ ሲሆን አሁን ወደ 9.5 በመቶ ከፍ ማለቱ ተገልጿል።
ነገር ግን ለኤሌክትሪክ ኃይል፣ ለመድሀኒት አቅርቦት ፣ ለስኳር ፣ ለማዳበሪያ እንዲሁም ለዘይት የሚያስፈልጉ የውጭ ምንዛሪያዎች በ4.5 በመቶ ዝቅ ተደርጓል።
የተደረጉት የምንዛሪ አገልግሎት ዋጋ ማሻሻያዎች ከዚህ ወር (የካቲት) ጀምሮ እንደሚተገበሩ ባንኩ መግለፁን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

#Ethiopia😷
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ከተደረገው 7,056 የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ 686 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋገጠ።
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የ6 ሰዎች ሞት ሲመዘገብ ፤ 242 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ 145,548 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህ መካከል ፣2,177 ሰዎች ሞተዋል፤ 127,864 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
አሁን ላይ 260 ሰዎች በፀና ታመው በህክምና ክትትል ላይ ይገኛሉ።
#Purpose #Tikvah

የመተከል ዞን 12ኛ ክፍል ተፈታኞች ጉዳይ ፦
በመተከል ዞን 8 ትምህርት ቤት ከፀጥታ ጋር በተያያዘ አሁን ድረስ ምዝገባ አልተጠናቀም።
ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎቹ ተመዝግበው ፈተናውን እንዲወስዱ ለማድረግ የፀጥታውን ሁኔታም የማረጋገጥ ስራ ከክልሉ ጋር አብሮ እየሰራ እንደሚገኝ በትላንት መገለጫው አሳውቋል።
ነገር ግን በአካባቢው ችግሮቹ ካልተፈቱና የፀጥታ ችግር ካለ በመተከል ዞን 8 የፈተና ጣቢያዎች ያሉትን ተማሪዎች ወደ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ / ሌላ ከተሞች አጓጉዞ የማስፈተን እቅድም እንዳለ ተገልጿል።
ትምህርት ሚኒስቴር በአካባቢው ያሉት ችግሮች በሚቀጥለው 1 ወይም 2 ሳምንት ተፈተው ተማሪዎች ባሉበት ሁኔታ/ቦታ ሆነው ይፈተናሉ የሚል እምነት እንዳለው አሳውቋል።
በአካባቢው የከፋ ሁኔታ ከተፈጠረ ግን በትራንፖርት ወደ አሶሳ ከተማ / አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተጓጉዘው እንዲፈተኑ ይደረጋል ተብሏል።

የ2013 ዓ/ም ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች ጉዳይ ፦
የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በ2013 ዓ/ም መጨረሻ (ሰኔ አካባቢ) ፈተናቸውን እንዲወስዱ ለማድረግ ከወዲሁ ስራዎች እየተሰሩ ነው ተብሏል።
በ2012 ባች በታብሌቶች መዘግየት የቀረው የኦንላይ ፈተና የ2013 ዓ/ም ተፈታኞች ፈተናውን በኦንላይን እንዲወስዱ ለማድረግ እንደሚሰራ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።
አጠቃላይ የ2013 ዓ/ም ተፈታኞች ወደ 800,000 ይሆናሉ።
ትምህርት ሚኒስቴር ለ74 ዓመታት ሲሰጥ የነበረውን የፈተና አሰጣጥ ሂደት በመቀየር ከ2012 ባች ጀምሮ በኦንላይ ለማስፈተን ጥረት ቢያደርግም ግዢ የተፈፀመባቸው 500 ሺህ ታብሌቶች በኮቪድ-19 ምክንያት ወደሀገር ባለመግባታቸው ሳይሳካ ቀርቷል፤ በ2013 ባች ግን ተግባራዊ ለማድረግ በሙሉ አቅሙ እንደሚሰራ አሳውቋል።
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ጫና የሚገኘውን የትምህርት ዘመን ከግምት ውስጥ አስገብቶ በ2013 ብሄራዊ ፈተና ላይ ችግር እንዳይገጥም ከወዲሁ እየሰራ እንደሚገኝ አሳውቋል።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሪፖርቶች ፦
- ባለፉት 24 ሰዓት በመላው ዓለም 12,356 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መሞታቸው ሲረጋገጥ 423,186 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ታውቋል።
- በአሜሪካ ወረርሽኙ ሲጀምር 1 ብሎ የጀመረው የሟቾች ቁጥር ዛሬ ላይ 492,521 ደርሷል። በየዕለቱ በሺዎች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን እንደቅጠል እየረገፉ ነው። ባለፉት 24 ሰዓት 2,908 የUS ዜጎች በበሽታው ሞተዋል።
- በሜክሲኮ በኮቪድ-19 በሽታ የሞቱ አጠቃላይ ሰዎች 171,234 ደርሷል። ከነዚህ መካከል የ1,474 ሰዎች ሞት የተመዘገበው ትላንት ነው።
- ብራዚል ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓት 1,204 ሰዎች በበሽታው ሞተዋል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 237,601 ደርሷል።
- በተጨማሪ ሩስያ 507 ፣ UK 758 ፣ ስፔን 530 ፣ ፈረንሳይ 429 ፣ ጀርመን 523 ፣ ጣልያን 316 ዜጎቻቸውን በ24 ሰዓት አጥተዋል።
- በአህጉረ አፍሪካ አጠቃላይ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 3,753,441 የደረሱ ሲሆን ከነዚህ መካከል 97,950 ህይወቱ ኣልፏል።
- በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ-19 በሽታ የተያዙ ሰዎች 108,730,653 ደርሰዋል ከነዚህ መካከል 2,394,127 ሰዎች ሲሞቱ 80,753,857 ሰዎች አገግመዋል።
ክትባትን የተመለከቱ ጉዳዮች ፦
- በአሜሪካ ዋሽንግቶን ግዛት እስከዛሬ አጠቃላይ የተሰጠው የኮቪድ-19 ክትባት 1 ሚሊዮን ደርሷል። የጤና ጉደዮች ባለስልጣናት ትላንት አርብ 1 ሚሊዮን ክትባት መሰጠቱትን ይፋ አድርገዋል።
- ጎረቤት ኬንያ ይህ ወር ሳይጠናቀቀ የአስትራዜንካ ክትባትን እንደምትቀበል እና ለዜጎቿ እንደምትሰጥ ተሰምቷል። ኬንያ የክትባቱ ውጤታማነት ላይ የሚነሱትን ሀሳቦች ችላ በማለት ነው ክትባቱን የምታስገባው።

የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ !
#WollegaUniversity
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 3ሺህ 398 ተማሪዎችን ዛሬ በወለጋ ስታዲየም እያስመረቀ ነው።
የዩኒቨርሲቲው እያስመረቃቸው ካሉት ተማሪዎች የመጀመሪያ ዲግሪ 3013፣ በሁለተኛ ዲግሪ 344፣ በህክምና ዶክትሪት 40 እና የአካዳሚክ ዶክተር በአጠቃላይ 3 ሺህ 398 ናቸው።
#KebridharUniversity
ቀብሪ ደሀር ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 612 ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው። ለዚሁ ስነስርዓት የክልሉ ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ እና የፌዴራል እንዲሁም የክልሉ ባለስልጣናት ትላንት ወደቀብሪድሃር መጓዛቸው ይታወቃል።
#JimmaUniversity
ጅማ ዩኒቨርስቲ በ2ተኛ ዙር በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ያሠለጠናቸውን 4ሺህ 338 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።
ከተመራቂዎቹ መካከል 3,950 በመጀመሪያ ዲግሪ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 1 ሺህ 530 ሴቶች ናቸው። በ2ተኛ ዲግሪ ደግሞ 45 ሴቶች የሚገኙበት 354 ተማሪዎች ተመርቀዋል፡፡ 3 ተማሪዎች በ3ተኛ ዲግሪ እና 4 ተማሪዎች ደግሞ የ 'ሰብ ስፔሻሊቲ' ተመራቂ ይገኙበታል፡፡
#ArsiUniversity
አርሲ ዩኒቨርሲቲ በህክምና ስፔሻሊቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 24 ሰልጣኞቹን በመጀመሪያ ዙር አስመርቋል፡፡
#KotebeMetropolitanUniversity
ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ 2039 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው ፤ 1 ሺህ 104 በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 222 በ2ኛ ዲግሪና 711 በዲፕሎማ።
ምንጭ፦ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ፣ SRTV፣ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፣ኤፍ ቢሲ