TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AdigratUniversity

የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለ8ኛ ጊዜ 2,576 ተማሪዎቹን እያስመረቀ ይገኛል።

ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በትግራይ በነበረው ጦርነት ውድመት ደርሶበት ስለነበር ተማሪዎቹ ቀሪ ትምህርታቸውን በመቐለ ዩንቨርስቲ እንዲያጠቅቁ ተደርጎ ነው ዛሬ እየተመረቁ የሚገኙት።

በሌላ በኩል በቅርቡ ተማሪዎችን ያስመረቀው መቐለ ዩኒቨርስቲ ቀሪ 608 ተመራቂ ተማሪዎችን በ2ተኛ ዙር እያስመረቀ እንደሚገኝ ከኢዜአ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በ24 ሰዓት 4 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገንዘብ አባዝተን እንሠጣለን በማለት ሲያጭበረብሩ የነበሩ 2 የካሜሮናውን ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ !

በአዲስ አበባ በማታለል ወንጀል ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሁለት ካሜሮናውያን የአሜሪካ ዶላርን ጨምሮ የተለያዩ አገራት የገንዘብ ኖቶችን በ24 ሰዓት ውስጥ እያባዛን እንሰጣለን በማለት ሲያጭበረብሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በፓስፖርት ስማቸው ናዋ ሳምፕሰን እና ጁዲ አያምባንግ ተብለው የሚጠሩት እነዚህ ካሜሮናዊያን ተጠርጣሪዎች በአዲስ አበባ ቆይታቸው ማርክና ሳምሶን በሚሉ ሃሰተኛ ስሞች እንደሚጠቀሙ የጠቀሰው ኮሚሽኑ የደቡብ አፍሪካ ዜግነት ጭምር እንዳላቸው በመናገር እና ከተለያዩ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር ሲንቀሳቀሱ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።

ተጨማሪ : https://telegra.ph/AddisAbabaPolice-02-13

(የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#TheWhiteHouse

ፕሬዘዳንት ባይደን ስልጣን ዘመናቸው ከማብቃቱ በፊት በሽብር የተጠረጠሩ ግለሰቦች የሚታሰሩበትን የ "ጓንታናሞ ባይ" እስር ቤትን የመዝጋት አላማ እንዳላቸው ኋይት ኃውስ ትላንት አስታውቋል፡፡

የቀድሞ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፈረንጆቹ 2016 በተካሄደው የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የጓንታናሞ ባይ እስርቤትን በስራ ላይ እንደሚቆይና “በመጥፎ ሰዎች” እንደሚሞላ ገልጸው ነበር፡፡

በባራክ ኦባማ ጊዜ እስረኖች እንደሚለቀቁ ቃል ተገብቶላቸው ነበር፤ ነገር ግን ኦባማ የኮንግረሱን ፍቃድ ስላላገኙ እስረኞቹ መፈታት አልተሳካም፡፡

በውቅቱ የአሁኑ ፕሬዘዳንት ባይደን የኦባማ ምክትል ነበሩ፡፡

በአሜሪካ "ሴፕቴምበር 11" የተከሰተውን ከባድ አቀናብሬያለሁ ብሎ ኃላፊነት የወሰደውን ፓኪስታናዊ ካሊድ ሸህ መሃመድን ጨምሮ ከ”ዋር ኦን ቴረር” ጋር ግኝኑነት ያላቸው ፍረደኖች በወታደራዊው እስርቤት ይገኛሉ፡፡

በእስርቤቱ እስካሁን 40 እስርኞች የሚገኙበት ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 26ቱ "አደገኞች" ናቸው ተብለው የማይለቀቁና የፍርድ ሂደቱም ነገሩ ውስብስብ ስለሆነ የተጓተተባቸው ናቸው፡፡

AlAin News
Reuters
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የትግራይ ክልል ሪፖርቶች ፦

- በመቐለ 80 በመቶ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ወደ ስራ መመለሳቸው።

- የትግራይ መልሶ ማቋቋም ስምምነት ፊርማ።

- የክልል ትግራይ ገቢዎች ባለስልጣን የግብር መሰብሰብ ስራ ለመጀመር መዘጋጀት።

- የሰላም ሚኒስቴር በትግራይ እየተደረገ ያለው ድጋፍ መቀጠሉን መግለፁ ።

- በትግራይ የተለያዩ ከተሞች የቀጠለው ተቃውሞ እና አድማ።

- በአክሱም ፣ ውቅሮ፣ በሽረ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ የሰዎች ህይወት ስለማለፉ።

- በአክሱም ከተማ የ "ኤርትራ ሰራዊት" ተኩስ ከፍቷል ስለመባሉ።

- በመቐለ ከተማ ከቀናት አድማ/ተቃውሞ በኃላ ከትላንት ጀምሮ ሁሉም አይነት መደበኛ እንቅስቃሴ መጀመሩ።

- የትግራይ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን በክልሉ ጉዳይ ዝርዝር መረጃ እና መግለጫ እንደሚሰጥ ማሳወቁ።

- የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሰጡት አስተያየት እና ያስተላለፉት መልዕክት።

(ለቲክቫህ አባላት የቀረበ)

(Tikvah Family - የካቲት 6 ቀን 2013 ዓ/ም)

https://telegra.ph/TikvahFamily-02-13
በዓዲግራት ከተማ የባንክ አገልግሎት ጀመረ።

በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች ተቋርጦ የቆየውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተገለፀ።

የዓዲግራት ንግድ ባንክ ቅርጫፍ አገልግሎት መጀመሩን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ኢተነሽ ንጉሰ ለክልሉ ቴሌቪዥን ገልፀዋል።

የአክሱም እና ሽረ ቅርጫፎች በቅርብ ቀን ውስጥ ይከፈታሉ ሲሉ ወ/ሮ ኢተነሽ ተናግረዋል።

የዓድዋ ንግድ ባንክ ቅርጫፍ የደረሰበት ጉዳት ከባድ በመሆኑ ከተወሰነ ጊዜ በኃላ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጎ ይከፈታል ብለዋል የቢሮ ኃላፊዋ።

አገልግሎት በጀመሩ ባንኮች አገልግሎቱ ከጀመረበት ቀን አንስቶ በ14 ቀን ውስጥ ነባሩ የብር ኖት ቅያሬ እንደሚደረግ ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከ2 ሚሊዮን ጄሪካን በላይ የምግብ ዘይት በቁጥጥር ስር ዋለ !

በአዲስ አበባ ከተማ "ጀሞ ሚካኤል" አካባቢ ልዩ ስሙ "አንበሳ ጋራዥ" በሚባለው ቦታ በሕገ ወጥ መንገድ የተከማቸ ከሁለት ሚሊዮን ጄሪካን በላይ ፓልም የምግብ ዘይት ዛሬ በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢብኮ ገለፀ።

በሕገ ወጥ መንገድ የተከማቸው ዘይት ሊያዝ የቻለው ፌዴራል ፖሊስ እና የላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከኅብረተሰቡ የደረሳቸውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ለ2 ሳምንታት ባደረጉት ክትትል ነው ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NewsAlert

በቤኒሻንጉል ጉመዝ ክልል ውስጥ 'የከፋ' የአመራር ችግር የታየባቸው አመራሮች ከኃላፊነት ሲነሱ የከፋ አመራር የለባቸውም የተባሉት ደግሞ ሽግሽግ አደረጉ !

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብልፅግና ፓርቲ ፥ በቅርቡ የተካሄደውን የከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ኮንፈረንስ ተከትሎ ህብረ-ብሔራዊነትን በጠበቀ መልኩ አዲስ የአመራር ምደባ እና ሽግሽግ መደረጉን አሳወቀ።

በህዝብ በማስተቸት የከፋ ችግር የታባታቸውን አመራሮች በማንሳት በአዲስ እንዲተኩ በማድረግና የከፋ ችግር የሌለባቸውን ደግሞ በማሸጋሸግ የመተከል ዞንና ወረዳዎች መዋቅር መልሶ የማደራጀት ስራ ተሰርቷል ብሏል።

የመተከል ዞን መምሪያ መዋቅር መልሶ ለማደራጀት በተወሰደ እርምጃ የትምህርት መምሪያ ፣ የከተማ ልማት እና የንግድ መምሪያ፣ ግብርና ተፈጥሮ ሀብት መምሪያ፣ ፍትህ መምሪያ እንዲሁም የውሃ እና ማዕድን መምሪያ ኃላፊ ቦታ ላይ የአመራር አዲስ ምደባና ሽግሽግ ስራ ተሰርቷል ተብሏል።

- የወምበራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ቦታዎች በሌላ አመራር እንዲተኩ ተደርጓል።

- የቡለን ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ እና ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ቦታዎች በሌላ አመራር እንዲተኩ ተደርጓል።

- የድባጢ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ቦታ በሌላ አመራር እንዲተካ ተደርጓል።

- የማንዱራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ቦታ በሌላ አመራር እንዲተካ ተደርጓል።

- የጉባ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና ምክትል ዋና አስተዳዳሪ ቦታዎች በሌላ አመራር እንዲተኩ ተደርጓል።

በተመሳሳይ የካቢኔ እና የጽ/ቤት ኃላፊ ቦታዎች ላይ የአመራር አዲስ ምደባ እና የማሸጋሸግ ስራ በመስራት መልሶ የማዋቀር ስራ መስራቱ ተገልጿል።

* ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Ethiopia😷

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ከተደረገው 6,500 የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ 756 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋገጠ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የ4 ሰዎች ሞት ሲመዘገብ ፤ 155 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ 145,704 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህ መካከል ፣2,181 ሰዎች ሞተዋል፤ 128,019 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

አሁን ላይ 270 ሰዎች በፀና ታመው በህክምና ክትትል ላይ ይገኛሉ።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የመቐለ፣ አክሱም፣ ዓዲግራት እና ራያ ዩኒቨርሲቲዎች የጋራ ፎረም ምስረታ ዛሬ ተካሄደ !

በትግራይ የሚገኙት አራቱ ዩኒቨርሲቲዎች (መቐለ፣ ራያ ፣ አክሱም ፣ ዓዲግራት ) ወደቀድሞ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱ የሚያስችል ፎረም ምስረታ ዛሬ በመቐለ ተካሄደ።

ፎረሙ በተለይም ከየካቲት 29 ጀምሮ የሀገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱትን በትግራይ ያሉ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዎቹ ገብተው እንዲፈተኑ ለማድረግ ድጋፍ ያደርጋል ተብሏል።

በተጨማሪ በክልሉ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት በሚሰራው ስራ አስተዋጽዖ እንደሚያደርግ ነው የተገለፀ።

በሌላ በኩል አራቱም ዩኒቨርሲቲዎች በትግራይ የተፈጠረው ሰብዓዊ እና ማህበራዊ ቀውስ ለመፍታት ለሚደረገው ስራ የ20 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

መቐለ ዩኒቨርሲቲ 10 ሚሊዮን ብር ፣ አክሱም 4 ሚሊዮን፣ ዓዲግራት 4 ሚሊዮን እንዲሁም ራያ ዩኒቨርሲቲ 2 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአዳቡል ድማሉ ወረዳ በደለቲ፣ ኮንቦድሽ እና በዮንግ ቀበሌዎች ብሄርን መሰረት አድርገው ህይወት ባጠፉ 89 ግለስቦች ላይ እስከ 23 ዓመት ድረስ በጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ !

የፌዴራል ዐቃቤ ህግ በእነ ዳዊት አብዲሳ መዝገብ ክስ ካቀረበባቸው 117 ሰዎች መካከል በ89ኙ ላይ እንደ ወንጀል ተሳትፏቸው ከ7 – 23 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ተወሰነ።

ቅጣቱ ሊጣል የቻለው ተከሳሾቹ በነኃሴ ወር 2010 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአዳቡል ድማሉ ወረዳ፤ በደለቲ፣ ኮንቦድሽ እና በዮንግ ቀበሌዎች ብሄርን መሰረት አድርገው በፈጸሙት ወንጀል የ30 ሰዎች ህይወት እንዲያልፍ፣ 13,500 ነዋሪዎች ከቄዬአቸው እንዲፈናቀሉ እና 1,396 ቤቶች እንዲቃጠሉ በማድረጋቸው እንደወንጀል ተሳትፏቸው በወንጀል ህጉ አንቀጽ 240 (3) እና 539 (1) ሀ ስር ክስ ተመስርቶባቸው ቆይቷል።

ጉዳዩን ቀርቦለት የነበረውም የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተዘዋዋሪ ወንጀል ችሎት የክርክር ሂደቱ ተጠናቆ የካቲት 5 ቀን 2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ፍርድ መሰረት በ89 ተከሳሾች ላይ እንደተሳትፏቸው ደረጃ ጥፋተኛ መሆናቸውን አረጋግጦ ከ7 ዓመት እስከ 23 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል፡፡

ምንጭ፦ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ (EPA)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ቻይና ለWHO ቀልፍ መረጃ መከልከሏ ተሰማ!

ቻይና የኮሮና አመጣጥ እየመረመረ ላለው የአለም አቀፉ ጤና ድርጅት ቡድን ቁልፍ የሆኑ መረጃ መከልከሏን የመርማሪው ቡድን አባል ተናገሩ።

የስነህይወት ተመራማሪው ዶሚኒክ ድዋየር ቡድኑ መጀመሪያ ተመዘገቡ የተባሉ ህሙማንን ጥሬ መረጃ እንዲሰጧቸው መጠያቃቸውንና ይህም ደግሞ የተለመደ አሰራር መሆኑን ለሮይተርስ፣ዋል ስትሪት ጆርናልና ኒውዮርክ ታይምስ ተናግረዋል።

ነገር ግን በጠየቁት መሰረት ሳይሆን ያገኙት አጭር ማጠቃለያ ነው።

መርማሪዎቹ በአውሮፓውያኑ ታህሳስ 2019 በኮሮናቫይረስ የተያዙ የመጀመሪያ ህሙማን የተባሉ 174 ኬዞችን ጥሬ መረጃ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

መጀመሪያ ከተያዙ መካከል ቫይረሱ ተገኝቶበታል የተባለው የውሃን የስጋ ገበያ ጋር ንክኪ አላቸው የተባሉ ግማሾቹ የሚሆኑት ብቻ ናቸው።

"ለዚያም ነው ይህንን መረጃ እንዲሰጠን አጥብቀን እየጠየቅን ያለነው። ለምን መረጃውን አይሰጡንም? በዚህ ላይ ምንም ማለት አልችልም። ፖለቲካዊ ይሁን? አስቸጋሪ ስለሆነ ይሁን? ወይም መረጃው ሊኖርበት ያልቻለው ሌላ ምክንያት ይኖር ይሆን ወይ የሚለውን አላውቅም። ያው ማድረግ የሚቻለው የተለያዩ ግምቶችን ማስቀመጥ ነው" ብለዋል።

ቲያ ኮልሰን ፊሸር የተባሉ የመርማሪው ቡድን አባልና የወረርሽኝ ከፍተኛ ባለሙያ በበኩላቸው ምርመራው በከፍተኛ ሁኔታ "ጂኦ ፖለቲካል" መልክ እንዳለው ለኒውዮርክ ታይምስ ተናግረዋል።

"ቻይና ለምርመራው በሯን እንድትከፍት ምን ያህል ጫና እየተደረገባት እንደሆነ ሁላችንም የምናውቀው ነው። ከዚያም ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ወቀሳዎች እየቀረቡ ነው" ብለዋል ተመራማሪዋ።

በሚቀጥለው ሳምንት ይወጣል ተብሎ በሚጠበቀው የመርማሪው ቡድን የመጨረሻ ሪፖርት የመረጃዎች ክልከላ እንደሚካተት ፕሮፌሰር ዶሚኒክ ይናገራሉ።

Via BBC
@tikvahethiopia
የፖለቲከኞቹ የረሃብ አድማ ፦

- እነአቶ ጃዋር መሀመድ በረሃብ አድማ ዛሬ 18ኛ ቀናቸውን መያዛቸው

- የፖለቲከኞቹ የጤና ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ

- እነዶ/ር ኢሊሊ ጀማል ባለው ሁኔታ ተገደው ክትትል ማቆማቸው

- ጠበቃ ከድር ቡሎ በተደጋጋሚ ውስኔ የተሰጠበት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ መጣሱን መግለፃቸው

- ICRC አባላት ፖለቲከኞቹ ያሉበትን ሁኔታ መጎብኘታቸው

- አቶ በቀለ ገርባ ወደግል የህክምና ተቋማ እንዳይወሰዱ መከልከላቸው

- ስንት ቀን ያለምግብ መቆየት ይቻላል ? የዶ/ር ኢሊሊ ጀማል ምላሽ

https://telegra.ph/JawarMohammed-02-14
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደምቢዶሎ ቆይታ ፦

ጠ/ሚር ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ በቄለም ወለጋ 50 ኪ.ሜ. ርዝመት ያለውን የደምቢዶሎ-ጋምቤላ ጎዳና አካል የሆነ የመንገድ ግንባታ ማስጀመራቸውን ገልፀዋል።

ዶክተር አብይ ዛሬ ያስጀመሩት በ1.6 ቢሊየን ብር በጀት የሚገነባውን የደምቢዶሎ - ሙጊ - ዶላ የአስፓልት የመንገድ ስራን ነው።

በሌላ በኩል ዛሬ ጥዋት ደምቢዶሎ የነበሩት ዶ/ር አብይ በማህበራዊ ሚዲያ ይፋዊ ገፆቻቸው ላይ ባሰራጩት መልዕክት በአካባቢው "ሰላም የማስፈንና የማረጋጋት ጥረታችን ውጤታማ ሆኗል" ብለዋል።

'ቄለም ወለጋ' በሀገሪቱ ከፍተኛ ዕድገት የማስመዝገብ ዐቅም ካላቸው ስፍራዎች አንዱ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "የጋራ ሰላማችንን በማስጠበቅ፣ በጋራ የአካባቢውን ምርታማነት ለማሳደግ እንተጋለን" ሲሉ ፅፈዋል።

ዛሬ በነበረው መንገድ ማስጀመሪያ መርኃግብር ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተገኝተው ነበር።

PHOTO : PM Dr. Abiy Ahmed
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia