#ስጋ
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰይድ እንድሪስ የ2016 ዓ/ም የገና በዓል ዝግጅትን በተመለከተ ምን አሉ ?
* ሰሞኑን የተለያዩ ኦፕሬሽኖች ሰርተናል። 200 ቤቶች አካበቢ ለማየት ሞክረን ከዛ ውስጥ በ30 ቤቶች ሕገ ወጥ ስጋ የተገኘበት ሁኔታ ነው የተፈጠረው።
* 15 ቤቶች ሙሉ ለሙሉ #አንዲታሸጉ ያደረግንበት ፣ ሌላ ተጨማሪ 10 ቤቶች ደግሞ ሕገ ወጥ (ሀሰተኛ) የስጋ ምርመራ ሰነድ ይዘው ህብረተሰቡን እያታለሉ ሥጋ ሲሸጡ የነበሩበት ሁኔታ መኖሩን ያዬንበት ሂደት አለ።
* አጠቃላይ ባደረግነው ሂደት 1,500 ኪሎግራም ሕገ ወጥ በሦስት ቀናት ውስጥ ተሰብስቦ እዚህ መጥቶ እንዲወገድ የተደረገበት ሂደት አለ።
* ባደረግነው ዳሰሳ #የሕገወጥ እንስሳት እርድ አለ። ከዚያ ውጪ ግን በእምነትም ይሁን በባህላችን ባዕድ የሆኑ እንስሳት ታርደው ወደ ገበያ የቀረቡበት ሂደት የለም። የተያዘው ሥጋ፦
- የበሬ ፣
- የፍዬል
- የበግ ፣ ግን በሕገ ወጥ መንገድ የታረደ ነው።
* የበሬ ስጋ የአንድ (1) ኪሎ ዋጋ ከ550 እስከ 570 ብር በዕለቱ ሽያጭ ይከናወናል። በአራት መስኮቶች የበግ እና የፍየል ስጋም ሽያጭ ይከናወናል። የበግ ስጋ በ500 ብር ፣ የፍየል በ510 ብር በኪሎ ግራም ለበዓሉም ለመደበኛ ቀናትም የሚያቀርቡበት በዚህ ደረጃ ተዘጋጅቷል።
" የባዕድ እንስሳት / #አህያ ስጋ እየተሸጠ ነው " ሲባል በነበረው ጉዳይ ምን ተባለ ? ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-01-05
#ቲክቫህኢትዮጵያ
@tikvahethiopia

Telegraph
Tikvah Ethiopia
“ 10 ቤቶች ሀሰተኛ የስጋ ምርመራ ሰነድ ይዘው ህብረተሰቡን እያታለሉ ስጋ ሲሸጡ የነበሩበት ሁኔታ መኖሩን ያዬንበት ሂደት አለ ” - አቶ ሰይድ እንድሪስ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰይድ እንድሪስ የ2016 ዓ/ም የገና በዓል ዝግጅትን በተመለከተ ለጋዜጠኞች በሰጡት ገለጻ፣ “ሉካንዳ ቤት ሂደው ከሚገዙት በተጨማሪ እንስሳትን በራሳቸው ይዘው ለሚመጡ የግል ተጠቃሚዎች የበዓሉ ጠዋት…