TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.89K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የኢታብ ሣሙና ፋብሪካ ባለቤት አቶ #እስክንድር_ተስፋዬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። አቶ እስክንድር በ2006 ዓ.ም 14.6 ሚሊየን ብር ግብር በመክፈላቸው ከደቡብ ክልል ግብር ከፋዮች #አንደኛ ወጥተው የዋንጫና ሜዳልያ ሽልማት ከቀድሞ የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ #ደሴ_ዳልኬ እጅ ተበርክቶላቸዋል። እንዲሁም በ2010 ዓ.ም. ጥቅምት ወር ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የ1 ሚሊዮን ብር ቦንድ በመግዛት ለሀገራቸው ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክተዋል። ከምንም በላይ ደግሞ አቶ እስክንድር ለበርካታ #ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር የቻሉ ባለሀብት ናቸው።

ኢትዮጵያ ታታሪ ልጇን አጥታለች!
ነብስ ይማር!
#TIKVAHETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🇪🇹ዮሚፍ ቀጀልቻ ድርብርብ ድል አስመዝግቧል🇪🇹

ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ በ ኦስሎ ዳይመንድ ሊግ ከ ደቂቃዎች በፊት በተደረገው የ 3,000 ሜትር ውድድር #አንደኛ በመውጣት አሸንፏል።

ዮሚፍ 7:26.25 በሆነ ደቂቃ በመግባት የግሉን ምርጥ ሰዓት እንዲሁም የ ቦታውን ሪከርድ በመስበር ውድድሩን በ በላይነት ማጠናቀቅ ችሏል።

ዮሚፍ በጀግናው አትሌት ሀይሌ ገብረ ስላሴ ተይዞ የቆየውን የቦታውን ሪከርድ 1.17 ሴኮንዶቻ በማሻሻል ሪከርዱን ሰብሯል።

ዮሚፍ ቀጀልቻ በኦስሎ ዳይመንድ ሊግ የገባበት ደቂቃ የአለማችን ሰባተኛው ፈጣን ሰዓት መሆኑ ይፋ ተደርጓ ።

ከዚህ በተጨማሪም የዮሚፍ ቀጀልቻ ድል " የዳይመንድ ሊግ አዲስ ሪከርድ " በመሆን ተመዝግቧል።

ቲክቫህ ስፖርት : t.iss.one/joinchat/VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA 🇪🇹 #Tokyo2020 ዛሬ ሌሊት ከ9፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚደረጉ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ የአለም አትሌቲክስ ባወጣው የተወዳዳሪዎች ዝርዝር መሰረት ከዚህ በታች የተገለፁ የሀገራችን አትሌቶች ውድድሮቻቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል። በ800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ፦ - ሀብታም አለሙ - ነፃነት ደስታ - ወርቅውሃ ጌታቸው በ3000 ሜትር መሰናክል ወንዶች ማጣሪያ ፦ - ጌትነት ዋለ - ለሜቻ ግርማ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ETHIOPIA🇪🇹

አትሌት ለሜቻ ግርማ 3,000 መሰናክል በመጀመሪያው ምድብ የማጣሪያ ውድድሩን አድርጎ 8:09.83 #አንደኛ ሆኖ አልፏል።

በሁለተኛው ምድብ ውድድሩን ያካሄደው የሀገራችን ልጅ አትሌት ጌትነት ዋለ 8:12.28 በሆነ ሰዓት በመግባት #ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል፤ ወደቀጣይ ዙር አልፏል።

በመጨረሻው ሶስተኛ ምድብ ውድድሩን ያካሄደው አትሌት ታደሰ ታከለ 8:24.69 በሆነ ሰዓት 8ኛ ደረጃ ይዞ በማጠናቀቁ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ሳይችል ቀርቷል።

@tikvahethsport @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ : ሲፋን ሀሰን ከወደቀችበት ተነስታ ድል አደረገች።

ትላንት በተካሄደ የ1,500 ሜትር ማጣሪያ ውድድር ኔዘርላንዳዊቷ (በትውልድ ኢትዮጵያዊ) ሲፋን ሀሰን በመጨረሻው ዙር ላይ ተጠልፋ ብትወድቅም ተነስታ ውድድሯን #አንደኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቃለች።

በርካቶችንም በጥንካሬዋ እና ተስፋን ባለመቁረጧን በማህበራዊ ሚዲያው ላይ እያሞጋገሷት ነው።

ሲፋን ሀሰን በቶኪዮ ኦሎምፒክ በምትወዳደርባቸው የውድድር ዘርፎች ውጤት ታስመዘግባለች ተብለው ከሚጠበቁ የዓለማችን አትሌቶች ቅድሚያ የተሰጣት ናት።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ኢትዮጵያ ከዓለም #1ኛ ሆና አጠናቀቀች። ሀገራችን #ኢትዮጵያ በቤልግሬድ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮን ከዓለም አንደኛ ሆና አጠናቀቀች። #አሜሪካ ሁለተኛ ፤ #ቤልጂየም ደግሞ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል። በቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያ ፦ 🥇4 ወርቅ፣ 🥈3 ብር፣ 🥉2 ነሃስ፣ በድምሩ 9 ሜዳሊያዎች ማግኘት ችላለች። እንኳን ደስ አላችሁ…
#USA

አሜሪካ ለኢትዮጵያውያን አትሌቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈች።

አሜሪካ እዚህ አዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲዋ በኩል ፤ በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና አስደናቂ ብቃትን ላሳዩ መላው የኢትዮጵያ አትሌቶች " እንኳን ደስ አላችሁ " መልዕክት አስተላልፋለች።

ሀገራችን #ኢትዮጵያ በቤልግሬድ የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮን ከዓለም #አንደኛ ሆና ማጠናቀቋ ይታወቃል።

አሜሪካ ከኢትዮጵያ በመቀጠል ከዓለም ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ነው የጨረሰችው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia 🇪🇹 ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትካፈልበት ተጠባቂው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ዛሬ ለሊት ይጀምራል። ዛሬ ለሊት አትሌቶቻችን ውድድራቸውን ያካሂዳሉ። በዚህም መሰረት :- - ሌሊት 9:15 :- የወንዶች 3,000 ሜትር መሰናክል ማጣርያ 🇪🇹 ለሜቻ ግርማ 🇪🇹 ጌትነት ዋሌ 🇪🇹 ኃይለማሪያም አማረ - ሌሊት 10:10 :- የሴቶች 1,500 ሜትር ማጣርያ 🇪🇹 ጉዳፍ ፀጋይ…
#ኢትዮጵያ🇪🇹

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶቻችን የሚሳተፉበት የኦሪጎን የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና እየተካሄደ ይገኛል።

በአሁን ሰዓት የ3,000 ሜትር መሰናክል ማጣርያ እየተካሄደ ነው።

በመጀመሪያው ምድብ ፦ የሀገራችን ልጅ ጌትነት ዋለ 8.17.49 በመግባት 4ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል። በምርጥ ሰዓት ወደ ፍፃሜው አልፏል።

በምድብ ሁለት ፦ አትሌታችን ለሜቻ ግርማ 8.19.63 በመግባት #አንደኛ በመሆን አጠናቋል በቀጥታም አልፏል።

በምድብ ሶስት ፦ ኃይለማርያም አማረ አንደኛ በመሆን አጠናቋል። ወደ ቀጣይ ዙር በቀጥታ አልፏል።

እንኳን ደስ አለን 🇪🇹❤️ !!

ቲክቫህ ስፖርት : https://t.iss.one/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethiopia @tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #ኢትዮጵያ🇪🇹 ሶስተኛ እና አራተኛ ላይ የሚገኙት ኬንያ እና ኢትዮጵያ ናቸው። 🇪🇹 አባብል የሻነ ፉክክሩ እጅግ በጣም ከባድ ነው። ድል ለሀገራችን🇪🇹❤️! @tikvahethiopia
#Update

ከፍተኛ ተጋድሎ ስታደርግ የነበረችው 🇪🇹 አባብል የሻነ ውድድሩን አቋርጣለች።

#አንደኛ እና #ሁለተኛ ደረጃ ላይ ያሉት ኬንያ እና ኢትዮጵያ ናቸው። ተያይዘው ነው እየሄዱ ያሉት።

ከኃላ ቀርተው የነበሩት የእስራኤል እና የኤርትራ አትሌቶች ወደፊት ገስግሰው 3ኛ እና 4ኛ ላይ ይገኛሉ።

More : @tikvahethsport

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
አንድ ዓመት ስለደፈነው የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት የኢትዮጵያ መንግሥት ፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፣ ህወሓት እና ሀገራት ምን አሉ ?

የኢትዮጵያ መንግሥት

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፤ የፕሪቶሪያው ግጭት የማስቆም ስምምነት ዋና ዉጤት " የጦር መሣሪያ ላንቃ መዘጋቱ " እንደሆነ አሳውቋል።

ሚኒስቴር ከግጭት ማቆሙ ስምምነት በኋላ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮች የምትጠቀስበት ሁኔታ ካለፈው ዓመት የተለየ ሆኗል ብሏል።

ስምምነቱ ኢትዮጵያ በብዙ መንገድ ከተለያዩ ሀገሮች ጋር ያላትን ግንኙነት መለወጡን የግለፀው ሚኒስቴር መ/ቤቱ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ፣ ከአየርላንድ እንዲሁም ከአውሮጳ ሕብረት/EU ጋር ያላትን ግንኙነት እንዲሻሻል ማድረጉን እንደ ማሳያ ገልጿል።

ስምምነቱ ለኢትዮጵያ ምን አስገኘ ለሚለው ጥያቄም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር " ሰላም አስገኝቷል " ሲሉ ምላሽ ሰጥቷል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፤ ምንም እንኳን በተደረሰው ስምምነት ግጭት በመቆሙ ሻክረው የነበሩ ግንኙነቶች አሁን መልካቸውን ቢቀይሩም የምልሶ ግንባታ እና የጦርነቱ ሰለባዎችን መልሶ በማቋቋም ረገድ እጥረት መኖሩን አልሸሸገም ሲል ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ጊዜያዊ አስተዳደር

በአሁን ሰዓት ትግራይ ክልልን እያስተዳደረ የሚገኘው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እና የስምምነቱ ፈራሚ ህወሓት በየፊናቸው የሰላም ስምምነቱን አንደኛ አመት አስመልክተው መግለጫ አውጥተዋል።

ጊዚያዊው አስተዳደሩ በመግላጫው ላይ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ህዝቡን ለማጥፋት ሲካሄድ የነበረን ዘመቻ እንዲሁም እንደ ብሄር ትግራዋይ እንዲጠፋ የህዝቡ ባህል፣ ቋንቋና ታሪክ ከሰዎች ህሊና ሳይቀር እንዲሰረዝ የተጎነጎነ ሴራ እንዲገታ አድርጓል ብሏል።

ስምምነቱ ሁሉም ፍላጎቶች እና ወደ ጦርነት ያስገቡ ጠንቆች በተቻለ መጠን ሰላማዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ብቻ ሊሳካ ይችላል የሚል በር መክፈቱን አመልክቷል።

ስምምነቱ አንድ አመት ቢሞላውም እስከ አሁን ድረስ ነፃ ያልወጣ ህዝብ ነፃ የማውጣት ፣ የተፈናቀለ ወደ ቄየው የመመለስ ፣ ህገ-መንግስታዊና ሉአላዊ የትግራይ ግዛት የማረጋገጥ ጉዳይ ፈፅሞ አልተነካም ፤ አሁንም ህዝቡ መከራ ውስጥ እየኖረ ነው ሲል ጊዜያዊ አስተዳደሩ አመልክቷል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ የፕሪቶሪያው የሰላም ውል በዓለም ማህበረሰብ ፊት የተፈፀመ ስምምነት እንደመሆኑ መጠን ፣ የዓለም ማህበረሰብ በአፈፃፀሙ ያሉ እንቅፋቶች በማስወገድና የትግራይ ህዝብ ኑሮ ወደ ነበረበት የመመለስ ህጋዊና ሞራላዊ ግዴታውን እንዲፈፅም ሲል ጥሪ አቅርቧል።

ህወሓት

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ( #ህወሓት ) በፊናው ባወጣው መግለጫ ስምምነቱ የዘላቂና አስተማማኝ ሰላም መሰረት መሆኑን ገልጿል።

ለስምምነቱ ተፈፃሚነት አባላቱና ደጋፊዎቹ በማሳተፍ በቁርጠኝነት እየታገለ መቆየቱንና ትግሉ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመልክቷል።

" የስምምነቱ ፈራሚ የሆነው የኢትዮጵያ መንግስት በውሉ ላይ የተቀመጡ ወሳኝ መሰረታዊ አበይት ጉዳዮች በአግባቡ አልፈፀመም " ያለው ህወሓት " ይህንንም የዓለም ማህበረሰብ የሚያውቀው ሃቅ ነው " ሲል ገልጿል።

" በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እስከ አሁነ የተገኙት ድሎች በማክበር ፤ የተቀሩት እንዲፈፀሙ የፌደራል መንግስት በውሉ መሰረት ሃላፊነቱ መፈፀም ይገባዋል ፤ ውሉ እንዲፈረም ሚና የነበራቸው ሁሉም አካላት ኢጋድ ፣ የአፍሪካ ህብረት ፣ የአሜሪካ መንግስት ፣ የአውሮፓ ህብረት ፣  ተሰሚነት ያላቸው የሰብአዊ መብት ተማጓቾችና የሚድያ ተቋማት እንዲሁም የዓለም ማህበረሰብ ሞራላዊና  ፓለቲካዊ ሃላፊነታቸው መወጣት ይገባቸዋል " ሲል ህወሓት በመግለጫው አስገንዝበዋል።

ሀገራት ምን አሉ ?

መቀመጫቸው አዲስ አበባ የሆኑ #የአስር_ሀገራት ኤምባሲዎች በኢትዮጵያ ለ2 ዓመታት ተካሂዶ በነበረው ግጭት ተሳትፈው የነበሩ ሁሉም ወገኖች የሰላም ስምምነቱን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እንዲያደርጉ እና አሉ ያሏቸውም ተግዳሮቶች በንግግር መፍትሄ እንዲያገኙ ጥሪ አድርግዋል።
- አውስትራሊያ፣
- ካናዳ፣
- ዴንማርክ፣
- ፊንላንድ፣
- ጃፓን፣
- ኔዘርላንድስ፣
- ኒውዚላንድ፣
- ኖርዌይ፣
- ስውዲን፣
- ዩናይትድ ኪንግደም/ዩኬ በጋራ ባወጡት መግለጫ፣ የፕሪቶሪያው ስምምነት ከተካሄደ ወዲህ በግጭቱ የተሳተፉ ሁሉም ወገኖች ሰላምን ለማምጣት ያደርጉትን ጥረት አድንቀዋል።

ስምምነቱ የተፈረመበት #አንደኛ_ዓመት ፣ የተመዘገቡ መልካም ውጤቶች የሚደነቁብት እንዲሁም ደግሞ ተግዳሮቶች እንዳሉ እና የተሟላና አስተማማኝ ሰላምን ለማረጋገጥ ጥረቶች በእጥፍ መቀጠል እንዳለባቸው ግንዛቤ የሚወሠድበት መሆኑን ኤምባሲዎቹ አመልክተዋል።

ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የጀመረው ደም አፋሳሹ ፣ እጅግ አውዳሚና አስከፊው መነሻውን ትግራይ አድርጎ ወደ አጎራባችን ክልሎች የተዛመተው ጦርነት ከ2 አመት በኃላ ህወሓትና የፌደራል መንግስት በደቡብ አፍሪካዋ የፕሪቶሪያ ከተማ ጥቅምት 24/2015 ዓ.ም በፈረሙት ግጭት ማቆም ጨምሮ በርካታ ጉዳዮች ባካተተ የሰላም ስምምነት ውል ጦርነቱ መቋጫ ማግኘቱ ይታወሳል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።
                  
@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ዘንድሮ በመላ ሀገሪቱ የ " ኬጂ " ተማሪዎች እንግሊዝኛ ቋንቋ እየተማሩ አይደለም።

የመዋዕለ ህጻናት ተማሪዎች " ኤ፣ ቢ፣ ሲ፣ ዲ… " ን በዜማ መቁጠር፣ " ኤ ፎር አፕል፣ ቢ ፎር ቦል… " እያሉ ቃላት መመሥረትም አቁመዋል።

ከዚህ ዓመት ጀምሮ " ስፖክን ኢንግሊሽ " እና " ኢንግሊሽ ሊትሬቸር " ከ " ኬጂ " ተማሪዎች የትምህርት ዓይነቶች ውስጥ ተሰርዘዋል።

እንደ ቀድሞው በአማርኛ ሂሳብ፤ በእንግሊዝኛ " ማትስ " እያሉ የቁጥሮችን አጠራር በሁለት ቋንቋ መሸምደድም ቀርቷል።

የዘንድሮ የ " ኬጂ " ተማሪዎች ለአካባቢ ሳይንስ እና ለ " ጄኔራል ሳይንስ " ሁለት ደብተር አይዙም።

በአራት ዓመታቸው " ነርሰሪ " የሚገቡት ህጻናት፣ በ6 ዓመታቸው ከ " ዩ ኬጂ " ሲመረቁ የሚያውቁት ብቸኛ የፊደል ገበታ የአፍ መፍቻ ቋንቋቸውን እንዲሆን ተደርጓል።

ልጆችን እንግሊዝኛ በማስተማር ተመራጭ የሆኑት የግል መዋለ ህጻናት ከዚህ ዓመት ጀምሮ ሁሉንም ትምህርት የሚሰጡት በአካባቢው የአፍ መፍቻ ቋንቋ ብቻ ነው።

በአዲሱ የትምህርት ሚኒስቴር አሠራር መሠረት ተማሪዎች እንግሊዝኛ ቋንቋን እንደ አንድ ትምህርት መማር የሚጀምሩት #አንደኛ_ክፍል ሲደርሱ ነው።

ከዚህ ዓመት ጀምሮ መተግበር የጀመረው ሥርዓተ ትምህርት ህጻናት የሚማሩትን ትምህርት በተለያዩ የትምህርት ዓይነቶች (ሰብጀክት) አይከፋፍልም።

የኬጂ ተማሪዎች እንደ ቀድሞው ሂሳብ፣ አማርኛ ወይም አካባቢ ሳይንስ የሚባሉ የትምህርት ዓይነቶች አይኖሯቸውም። በትምህርት አይነቶች ፋንታ ህጻናቱ የሚማሩት " ጭብጦችን " ነው።

ለምሳሌ፤ የመጀመሪያ ዓመት የመዋለ ህጻናት ተማሪዎች ስድስት ጭብጦችን ይማራሉ። ከእነዚህ ጭብጦች ውስጥ፦
* ስለ እኔ፣ ስለ ቤቴ እና ስለ ቤተሰቦቼ
* ትምህርት ቤቴ እና አካባቢዬ የሚሉት ይገኙበታል።

የኬጂ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ከሚማሯቸው ጭብጦች ውስጥ ደግሞ ፦
* ዋሊያ
* ህዋ
* ተክሎች እና መጓጓዣ ተጠቃሽ ናቸው።

በአዲሱ ካሪኩለም መሠረት ህጻናቱ እንደ ቀድሞው አብዛኛውን ጊዜያቸውን ክፍል ውስጥ ቁጭ ብለው ከሰሌዳ እና ከደብተር ጋር እንዲፋጠጡ አይደረግም።

ዘንድሮ የኬጂ ተማሪዎች የሚማሩባቸው ዋነኛ መንገዶች ጨዋታ፣ መዝሙር እና ተረት ናቸው።

በአዲሱ ካሪኩለም የኬጂ ተማሪዎች እንግሊዝኛ እንዲማሩ አይደርግም። በእንግሊዝኛ ምንም ነገር የለም። ሁሉም ነገር በአፍ መፍቻ ቋንቋ ይሰጣል።

የኬጂ ትምህርት ይዘት መቀነስ ያላስደሰታቸው ወላጆችም ያሉ ሲሆን ተማሪዎች ከአቅማቸው በታች እንዲማሩ እያደረገ ነው ብለዋል።

በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶችም ከወላጆች ቅሬታ እየተቀበሉ መሆኑን የአዲስ አበባ የግል ትምህርት ቤቶች አሠሪዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ አበራ ጣሰው አሳውቀዋል።

የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ካሪኩለሙ በዝግጅት ላይ በነበረበት ወቅት የትምህርት ይዘቱ መቀነሱን እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት መውጣቱን በተመለከተ ማኅበሩ ተቃውሞ አስተያየት መስጠቱንም አስታውሰዋል።

የቅድመ አንደኛ ሥርዓተ ትምህርትን ካዘጋጁ ባለሙያዎች አንዱ የሆኑት ዶ/ር ታደሰ ጃለታ ፤ " ቤተሰብ ልጁ እንግሊዝኛ ከቻለ፣ ፊደል ከቆጠረ ወይም መደመር ከቻለ ተምሯል፣ አድጓል ብሎ ያስባል። በህጻናት ደረጃ ትምህርት እርሱ አይደለም " ብለዋል።

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/BBC-AMAHRIC-01-24

Credit - #BBCAMAHRIC

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA🇪🇹

ከሰሞኑን በፔሩ፣ ሊማ ሲካሄድ በቆየ የዓለም ከ20 ዓመት በታች ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ከአሜሪካ በመቀጠል ከዓለም ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች።

ኢትዮጵያ:- 
6️⃣ የወርቅ፣
2️⃣ የብር
2️⃣ የነሀስ ሜዳሊያ በማግኘት ነው ከዓለም ሁለተኛ ከአፍሪካ ደግሞ #አንደኛ በመሆን ያጠናቀቀችው።

Via @tikvahethsport