#Breaking
ንብረትነቱ የሳውዝ ዌስት አየር መንገድ የሆነ ሌላ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ባጋጠመው የሞተር ብልሽት ምክንያት በረራውን #አቋረጠ።
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ በደረሰው #አደጋ ምክንያት ከበረራ #የታገደው ይህ ቦይንግ 737 አውሮፕላን በወቅቱ ተሳፋሪ ያልጫነ ሲሆን አብራሪዎቹ ካሊፎርኒያ ወደሚገኘው የሳውዝ ዌስት አየር መንገድ ወስዶ ለማቆም ጉዞ በጀመሩ በአስር ደቂቃ ውስጥ በአውሮፕላኑ አንደኛ ሞተር ላይ በተፈጠረ ብልሽት ሞተሩ ከልክ በላይ #በመሞቁ ምክንያት ወደ ካሊፎርኒያ ያደርጉት የነበረው በረራ ተቋርጦ ኦርላንዶ ውስጥ በድንገት ለማረፍ ተገደዋል ሲል cnbc ከደቂቃዎች በፊት ዘግቧል።
'የቦይንግ ካምፓኒ በአለም አቀፍ ደረጃ የደረሰበትን ኪሳራ ለማካካስ በማሰብ በሚመስል መልኩ ሰሞኑን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የደረሰውን አደጋ ከማሰልጠኛ ሲሙሌተርና አውሮፕላኑን ያበር ከነበረው ፓይለት ጋር በተያያዘ ያጋጠመ አደጋ ለማስመሰል በኒውዮርክ ታይምስና በአንዳንድ የውጭ ሚዲያዎች አማካኝነት የተሳሳተ ዘገባ መሰራቱ ይታወሳል።
Via waltainfo.com
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#DrTedrosAdhanom
የዓለም ጤና ድርጅት /WHO/ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መድሃኒት ለማግኘት ሲጠቀምበት የነበረውን የፀረ ወባ መድሃኒት ፣ ሃይድሮክሲክሎሮክዊን ለጊዜው #አቋረጠ።
የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ቦርድ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከአምስት ቀን በፊት በታተመው ላንሰት የሕክምና መጽሔት ላይ የወጣውን የጥናት ሪፖርት መሰረት አድርጎ ነው። በዚህ ጥናት መሰረት መድሃኒቱ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎችን ሞት #ያፋጥናል ይላል።
የዓለም ጤና ድርጅት [WHO] ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት "የከፍተኛ አመራሮቹ ቡድን አባላቱ #የሃይድሮክሲክሎሮክዊን ሙከራ ደህንነቱ ዳግም በደህንነት ቁጥጥር ቦርዱ እስኪመረመር ድረስ ለጊዜው እንዲቋረጥ ወስነዋል" ብለዋል። ሌሎቹ የምርምር ስራዎች ግን መቀጠላቸውን ገልፀዋል።
'ሃይድሮክሲክሎሮክዊን' (የፀረ ወባ መድሃኒት) በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ሌሎች መሪዎች ለኮሮና ቫይረስ ሕሙማን ቢሰጥ በፍጥነት እንዲያገግሙ ያደርጋል በሚል ሲወደስ ቆይቶ ነበር።
#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia