TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
4,615 ተተኳሽ የክላሽ ጥይት ተያዘ።

ትላንት ከመቐለ ከተማ ወደ ባህር ዳር ከተማ ሲጓጓዝ ከነበረ አይሱዙ FSR መካከለኛ የጭነት ተሽከርካሪ በወልደያ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በጉምሩክ ሰራተኞች አማካኝነት በተካሄደ ፍተሻ ብዛቱ 4,615 የሆኑ ተተኳሽ የክላሽ ጥይቶች መያዛቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹን በመደበቅ ለማሳለፍ የሞከሩ አሽከርካሪውን ጨምሮ 4 ተጠርጣሪዎች  በቁጥጥር ስር ውለው ተጨማሪ ማጣራት እየተደረገባቸው ይገኛል ተብሏል።

@tikvahethiopiaBOT
ሀዋሳ ከተማ የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ።

ከጥር 10 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚከበረውን የጥምቀት በዓል ምክንያት በማድረግ በሀዋሳ ከተማ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደርጓል።

በዓሉ በሚከበርበት ወቅት ህዝበ ክርስትያኑም ሆነ የከተማው ነዋሪ እንዲሁም አሽከርካሪዎች ለትራፊክ ፍሰቱ ተገቢውን ድጋፍ በመጠቆም በበዓሉ ዋዜማ ከየቤተክርስትያናቱ ታቦታቱ ሲወጡም ሆነ ሲገቡ በትራፊክ ፖሊስ ሞተረኛ እየታጀቡ ቅድምያ የሚሰጥ ይሆናል።

በዋናነት የሚዘጉ መንገዶች ፦

- ከሱሙዳ /ቅዱስ ገብረኤል ቤተ-ክርስትያን እስከ ማዘጋጃ አደባባይ በዓሉ ሚከበርበት ድረስ

- ከግሎባል ጋራዥ እስከ ማዘጋጃ አደባባይ በዓሉ ሚከበርበት ድረስ

- ከአዲሱ ዳህላክ እስከ ማዘጋጃ አደባባይ/ በዓሉ ሚከበርበት ድረስ መንገዱ የሚዘጋ ይሆናል።

ለጥቆማና አስተያየት ለበለጠ መረጃ ሀዋሣ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የ24 ሰዓት መረጃ ሰልክ ቁጥር 0462201046 ላይ መደወል ይቻላል።

(በሲዳማ ክልላዊ መንግሥት፣ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፓሊስ መምሪያ)

@tikvahethiopia
"የባለፈው ስህተት አይደገምም" - የጎንደር ከተማ አስተዳደር

በጎንደር ከተማ ባለፈው ዓመት ምዕመናን ተሰብሰበው ባህር ጥምቀቱን ለማክበር ለባህር ጥምቀቱ የተሰራው ርብራብ ተደርምሶ በሰው ህይወት ላይ ጉዳት መድርሱ የሚዘነጋ አይደለም።

በዚህ ዓመት የባለፈው ዓመት "ስህተት እንዳይደገምም" በክልሉ መንግሥት ድጋፍ ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የወጣበት የብረት ርብራብ መሠራቱን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ አስታወቋል።

በሌላ በኩል ፦

ጎንደር ከተማ ለከተራ ዝግጅት ማድረጓ ተገልጿል። በከተማዋ የአስፖልት ፅዳት በወጣቶች ተከናውኗል፡፡

በባህረ ጥምቀቱ ግቢ ውስጥ ያለውን ሁነት የሚያሳይ ትልቅ ስክሪን ተዘጋጅቷል፡፡ ከተማዋን በልዩ ልዩ መልኩ የማስዋብ ሥራም ተሠርቷል፡፡

Via AMMA
@tikvahethiopia
#Adwa

በዓድዋ ከተማ ተቋርጦ የነበረው የመብራት አገልግሎት በዛሬው ዕለት መጀመሩ ተገለፀ።

ዶክተር ኣብርሃም በላይ በዓድዋ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ አገልግሎት በዛሬው ዕለት መጀመሩን ለኢፕድ አሳውቀዋል።

ዶ/ር ኣብርሃም ፥ "የተቀሩት አክሱም ፣ ሽሬ እና ሑመራ በአጭር ግዜ የመብራት አገልግሎት እንዲያገኙ እየተሰራ ነው" ብለዋል፡፡

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የመቐለ ዩኒቨርስቲ ለሁሉም መደበኛ ነባር ተማሪዎቹ ጥሪ አደረገ።

የመቐለ ዩኒቨርስቲ ለሁሉም "ነባር ተማሪዎች" የመግቢያ ቀን ጥር 29 እና ጥር 30/05/13 ዓ.ም መሆኑን ከዩኒቨርስቲው የተማሪዎች ህብረት ፅሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ዩኒቨርስቲው ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተናገድ አስፈላጊ የሚባሉ ዝግጅቶችን በመጨረሱን ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ትምህርት የሚጀምረው የካቲት 01/06/13 ዓ.ም መሆኑን አስታውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የአትሌቶቹን ህይወት የቀጠፈው የትራፊክ አደጋ !

ትላንት እሁድ ጥር 9 ቀን 2013 ዓ/ም በኦሮሚያ ክልል ጊንጪ እና ኦለንኮሚ ከተሞች መካከል በተከሰተ የመኪና አደጋ የአትሌቶች ህይወት አልፏል።

በዚህ አደጋ ህይወታቸው ያለፈው ፦

1. አትሌት ሆርሴ ነጋ
2. አትሌት ባጫ በቀለ እንዲሁም
3. ዶ/ር ሙሉጌታ ኃይሉ ናቸው።

መረጃው ከኦሮሚያ ውሃ ስራዎች አትሌትክስ ክለብ ነው።

Via Ethiopia Athletics Federation
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#ከተራ

በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በየዓመቱ ጥር 10 ቀን የሚውለው የከተራ በዓል በድምቀት ተከብሮ ውሏል።

በክልል፣ ዞን፣ ወረዳ ደረጃ የሚገኙ የቲክቫህ አባላት በዓሉ በሰላም ተከብሮ መዋሉን እንዲሁም የበዓሉን ድባብ የሚያሳዩ ፎቶዎችን እያጋሩ ይገኛሉ።

www.tikvahethiopia.net በመግባት በአካባቢያችሁ የበዓል ድባብ ፎቶዎችን ማስቀመጥ ትችላላችሁ።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBO
TIKVAH-ETHIOPIA
ባለፉት 2 ቀናት በሱዳን ዳርፉር 83 ሰዎች ተገደሉ ! በሱዳን ምዕራብ ዳርፉር ግዛት በሁለት ጎሳዎች መካከል በተነሳ ግጭት በትንሹ 83 ሰዎች ተገድለዋል። የሱዳን ዜና አገልግሎት (ሱና) የሐኪሞች ማኅበርን ጠቅሶ እንደጻፈው ግጭቱ በዳርፉር ግዛት ዋና ከተማ ኢል ገነይና ቅዳሜ ዕለት ነው የተከሰተው። የግጭቱ መነሻ አንድ ሰው በጩቤ ተወግቶ መገደሉ ነው ተብሏል። አሁን ግጭቱን ተከትሎ በዳርፉር ሰዓት…
#UPDATE

የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ፣ በምዕራብ ዳርፉር የተከሰተው ግጭት እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል፡፡

ዋና ፀሐፊው ዛሬ ባወጡት መግለጫ፣ በጎሳዎች መካከል እየተባባሰ ባለው ግጭት ከተከሰተው ሞት እና መፈናቀል በተጨማሪ 50 ሺ ያክል ሰዎች መፈናቀላቸውንም ገልጸዋል፡፡

የሱዳን ባለስልጣናት ችግሩን ለመቅረፍ የሚያስችሉ እርምጃዎችን እንዲወስዱም አሳስበዋል፡፡

በሱዳን ዳርፉር በተከሰተው የጎሳ ግጭት የሟቾች ቁጥር ወደ 129 ከፍ ማለቱ ተገልጿል። ~ AlAIN

@tikvahethiopia
#Gondar

በኢትዮጵያ የጥምቀት በዓል በልዩ ድምቀት ከሚከበርባቸው ከተሞች መካከል ታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ ቀዳሚ ናት።

በዓሉን ለመታደምም በመቶ ሺህ የሚቆጠር የውጭ እና የሀገር ውስጥ ዜጋ በከተማው ይገኛል።

ለበዓሉ በጎንደር ከተማ የምትገኙ የቲህቫህ አባላት ፣ እንዲሁም የጎንደር ነዋሪ የሆናችሁ አባላቶች ለማንኛውም የመረጃ አገልግሎት የጎንደር ከተማ የፖሊስ ጣቢያዎች ስልክ ቁጥሮችን መዝግቧቸው ፦

• ጎንደር ከስተዳደር ፖሊስ መምሪያ - 0581110401

• 1ኛ/ዋ/ፖሊስ ጣቢያ -0581110196

• 2ኛ ዋ/ፖሊስ ጣቢያ -0581110197

• 3ኛ ዋ/ፖሊስ ጣቢያ -0581116641

• 4ኛ ዋ/ፖሊስ ጣቢያ -0581110373

• 5ኛ ዋ/ ፖሊስ ጣቢያ- 0581140013

• 6ኛ ዋ/ ፖሊስ ጣቢያ- 0581141344

• 7ኛ ዋ/ ፖሊስ ጣቢያ- 0584480214

* ጎንደር ከተማ እሳት አደጋ ስልክ ቁጥር
- 0581110122

• 0588110317 (Wireless)

* ለድንተኛ አምቡላንስ - O918789738

ስልክ ቁጥሮቹ ከጎንደር ከተማ ኮሚኒኬሽን የተገኙ ናቸው።

መልካም የጥምቀት በዓል!

የነገውን የበዓል ድባብ በ www.tikvahethiopia.net ላይ ማስቀመጥ እንደምትችሉ ከወዲሁ ለመግለፅ እንወዳለን።

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ ላይ የሰጣቸው ውሳኔዎች!

@tikvahethiopia
ምርጫ ቦርድ ህወሓትን በሚመለከት ያሳለፈው ውሳኔ ፦

ቦርዱ ህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ (ሕወሃት) የአመጻ ተግባር ላይ ተሰማርቷል ወይ የሚለውን ሁኔታ ለማጣራት በፓርቲው የተሰጡ መግለጫዎችን እና በይፋ የሚታወቁ ጥሬ ሃቆችን በማቅረብ ፓርቲው ኃይልን መሠረት ያደረገ የአመጻ ተግባር ላይ መሣተፉን አረጋግጧል፡፡

በተጨማሪም ፓርቲው መልስ የመስጠት እድል እንዲኖረው በማሰብ በፓርቲው እና በቦርዱ መካከል አገናኝ በመሆን ይሰሩ የነበሩትን የፓርቲውን የአዲስ አበባ ቢሮ የቀድሞ ተወካይ ለማነጋገር ጥረት ያደረገ ሲሆን ተወካዮም ፓርቲውን መወከል እንደማይችሉ ገልጸዋል። በመሆኑም፦

ሀ. በአዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 98/1//4/ መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፓርቲውን ህጋዊ ሰውነት ሰርዞታል። በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 99 መሠረት የፓርቲው ኃላፊዎች በፓርቲው ስም መንቀሳቀስ እንደማይችሉም ውሳኔ አስተላልፏል።

ለ. የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ በፓርቲው እና በፓርቲው አመራሮች ላይ በሚያደርገው ምርመራ የሚገኙ በህወሐት ሥም የተመዘገቡ ተንቀሳቃሽና የማይንቀሳቀስ ንብረቶችን በተመለከተ ያገኘውን ዝርዝር መረጃ እንዲልክ ቦርዱ ጥያቄ አቅርቧል።

ሐ. የፓርቲው ንብረት በአዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 99/2/ መሠረት ንብረቱ ተጣርቶ ዕዳ ካለበት ለዕዳው መሸፈኛ እንዲውል፤ ይሁንና እዳውን ሸፍኖ የሚተርፍ ንብረት ከተገኘ ቀሪው ገንዘብና ንብረት በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 99/3/ መሠረት ለሥነ ዜጋና መራጮች ትምህርት እንዲውል ቦርዱ ወስኗል፡፡

Via NEBE
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot