TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Adwa በዓድዋ ከተማ ተቋርጦ የነበረው የመብራት አገልግሎት በዛሬው ዕለት መጀመሩ ተገለፀ። ዶክተር ኣብርሃም በላይ በዓድዋ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ አገልግሎት በዛሬው ዕለት መጀመሩን ለኢፕድ አሳውቀዋል። ዶ/ር ኣብርሃም ፥ "የተቀሩት አክሱም ፣ ሽሬ እና ሑመራ በአጭር ግዜ የመብራት አገልግሎት እንዲያገኙ እየተሰራ ነው" ብለዋል፡፡ @tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#UPDATE

የአክሱምና ሽረ ከተሞች እንዲሁም አካባቢያቸው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማምሻውን እንዳገኙ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።

የሑመራ እና ወልቃይት ከተሞችና አካባቢያቸውን ኤሌክትሪክ ለማገናኘትም ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Ethiopia

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገው 4,980 የኮሮና ቫይረስ ላብራቶሪ ምርመራ 351 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧል።

ባለፉት 24 ሰዓት የሶስት ሰዎች ሞት ሲመዘገብ ፤ 188 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን እስካሁን ከተደረገው ከ1.8 ሚሊዮን በላይ የላብራቶሪ ምርመራ 131,546 ሰዎች ላይ ኮቪድ-19 ተገኝቷል ፥ ከነዚህ መካከል 2,033 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ ፥ 116,335 ሰዎች አገግመዋል።

@tikvahethiopia
የጥምቀት በዓል የጸሎት ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው !

በኢትዮጵያ ጥር 11 በሚከበረው የጥምቀት በዓል በታቦታት ማደሪያዎች ጥምቀተ ባህር ዙሪያ የጸሎት ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው።

በአዲስ አበባ ከተማ ጃንሜዳም እንዲሁ የጸሎት ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ሲሆን በርካታ ምዕመናን ታድመዋል።

በስነ-ስርዓቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ አቡነ ማቲያስን ጨምሮ ብጹአን አባቶች ተገኝተዋል።

በተጨማሪ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ብጹአን አባቶች መገኘታቸው ታውቋል። ~ ENA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጥምቀት በዓል እየተከበረ ይገኛል።

የ2013 ዓ.ም የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ እየተከበረ ይገኛል።

PHOTO : TIKVAH, ENA, GONDAR COMMU. , AMMA
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
በሱዳን ደቡብ ዳርፉር አዲስ ግጭት ተቀሰቀሰ።

በሱዳን ደቡብ ዳርፉር ግዛት በሪዜይጋት እና ፈላታ ጎሳዎች መካከል ትናንት ሰኞ ግጭት መቀስቀሱን አል ዓይን የሱዳን ዜና ወኪልን ዋቢ አድርጎ አል ዓይን ኒውስ (AlAIN) ዘግቧል፡፡

በአካባቢው አንድ እረኛ መገደሉን ተከትሎ በሁለቱ ጎሳዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ሰዎች ተገድለዋል፥ ቆስለዋል ሲሉ የደቡብ ዳርፉር አስተዳዳሪ ሙሳ ማህዲ ገልጸዋል፡፡

ከእረኛው ግድያ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ዳርፉር ዋና ከተማ ንያላ 85 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው አል ጣዊል መንደር ፣ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ነው ሰዎች የተገደሉት እና የቆሰሉት፡፡

አሁን ከደረሰው ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ ለመከላከል ግጭቱ ወደተከሰተበት አካባቢ ተጨማሪ የጸጥታ ኃይሎች መላካቸውንም የግዛቱ አስተዳዳሪ ተናግረዋል፡፡

ከ3 ቀናት በፊት ጥር 08 በሱዳን የምዕራብ ዳርፉር ግዛት ዋና ከተማ አል ጂኔይና በጎሳ ግጭት የሞቱ ሰዎች 129 መድረሳቸው መገለፁ ኣይዘነጋም። ~ አል ዓይን

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Sudan

እንደ AFP መረጃ በሱዳን በ "ደቡብ ዳርፉር" በኩል በተቀሰቀሰው የጎሳ ግጭት እስካሁን 55 ሰዎች ሞተዋል ፥ 37 ሰዎች ቆስለዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የጥምቀት በዓል በኤርትራ ተከበረ።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመግታት በተቀመጠው ጥብቅ በሆነ ገደብ የዘንድሮው የጥምቀት በዓል #በኤርትራ ተከብሯል።

በበዓሉ በኮቪድ-19 ምክንያት በርካቶች መገኘት አልቻሉም።

በኤርትራ መዲና "አስመራ ከተማ" (ከላይ ፎቶው ተያይዟል) በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች የጥምቀት በዓል በልዩ ሁኔታ ተከብሯል።

ኤርትራ ውስጥ እስካሁን በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር 1,877 ሲሆን ከነዚህ መካከል 1,073 ሰዎች አገግመዋል ፤ 6 ሰዎች ደግሞ በበሽታው ሞተዋል።

ወረርሽኙ እንዳይስፋፋ በሀገሪቱ ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል።

Photo : Yemane G. Meskel
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
በጃንሜዳ ያደሩ ታቦታት ወደ መቅደሳቸው እየተሸኙ ነው።

አ/አ ጃንሜዳ ካደሩት የ15 ደብሮች ታቦታት መካከል የ12 ደብሮች ታቦታት ወደ መቅደሳቸው እየተሸኙ ነው።

ምዕመናኑ ታቦታቱን በእልልታና በሆታ፤ ካህናቱ በአኮቴት (ምስጋና) እና ሽብሸባ ታቦታቱን ወደ መቅደሳቸው እየሸኙ ይገኛሉ። ~ ENA

@tikvahethiopia
የጥምቀት በዓል በካቶሊክ እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከበረ።

የጥምቀት በዓል በካቶሊክ እምነት ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ዝግጅቶች ተከብሯል።

PHOTO : ኢቲቪ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT