TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Metekel

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን ጥቃት አሁንም ቀጥሏል። የሰዎች ህይወት እያለፈ ነው፥ንብረትም እየወደመ ነው።

• አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ታኅሳስ 26 በጭላንቆ ቀበሌ 7 ንፁሃን ዜጎች እና 4 የመከላከያ አባላት ለቡለን ወረዳ አጎራባች ከሆነው ካማሺ ዞን ያሶ ወረዳ የገቡ የታጠቁ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ መገደላቸውን በቅዳሜው እትሙ አስነብቧል።

• በወምበራ ወረዳ በጎንዲ በተባለ ቦታ ባለፈው ሳምንት ሀሙስ የጸጥታ ሀይሎችን ጨምሮ በግብርና ስራ ላይ የተሰማሩ 16 ሰዎች በተፈፀመባቸው ጥቃት ተገድለዋል። በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

• ጉባ ወረዳ ትናንት በደረሰ ጥቃት 11 ሰዎች ተገድለዋል።

• ትላንት ለሊት ድባጤ ወረዳ 'ቆርቃ ቀበሌ' በታጣቂዎች በተከፈተ ጥቃት ከ60 በላይ ንፁሃን መገደላቸውን የአይን እማኞች እና ከጥቃቱ ያመለጡ ሰዎችን ዋቢ አድርጎ ቪኦኤ ዘግቧል።

ከ25 በላይ ሰዎች ቆስለዋል፣ እጅግ ከፍተኛ ንብረት እንደወደመ ተነገሯል።

ቪኦኤ ሬድዮ ፥አንድ የአካባቢው የኮማንድ ፖስት አባል ጥቃቱ መፈፀሙን አረጋግጠዋል ብሏል። ነገር ግን የደረሰውን ጉዳት መጠን አልገለፁም፤አላረጋገጡም፣ መረጃም አልሰጡም።

የአካባቢው የቲክቫህ አባላት በተፈፀመው ጥቃት የሟቾች ቁጥር ከመቶ በላይ ነው ብለዋል።

• ትላንት እንዲሁም ዛሬ ከቻግኒ ወደ ግልገል በለስ በሚሄዱ መኪናዎች ላይ ጥቃት ተፈፅሞ ሁለት ሰው ሲገደል ሌሎች ቆስለዋል። ትላንት 1 ሰው ዛሬ 1 ሰው ተገድሏል።

አጠቃላይ ከላይ የተሰባሰቡት መረጃዎች የአይን እማኞችና ነዋሪዎች የሰጧቸው ሲሆኑ በመንግስት በኩል የተብራራ ዝርዝር መረጃ እስካሁን አልተሰጠም።

አሁንም አካባቢው ከፍተኛ የስጋት ቀጠና መሆኑን ነዋሪዎች እየገለፁ ነው።

ምንጭ፦ቢቢሲ፣ቪኦኤ፣አዲስማለዳ፣ዶቼ ቨለ
@tikvahethiopia
ጎንደር ለአስመራ ጥሪ አደረገች።

በጎንደር በድምቀት ለሚከበረው የጥምቀት በዓል ለአስመራ ህዝብ ጥሪ መተላለፉን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መመሪያ አስታውቋል።

ጎንደር ከአስመራ ህዝብ ጋር የነበራትን ጥንታዊ የጠበቀ ግንኙነት ለማስቀጠል እና አብሮነትን ለማጠናከር አስመራ በበዓሉ እንድትታደም መጋበዟን ነው ከከተማ አስተዳደሩ ባህል ቱሪዝም ስፖርት መመሪያ የተገኘው መረጃ የሚገልፀው።

ባህረ ጥምቀቱን ምክንያት በማድረግ ወደ ጎንደር የሚሄዱ እንግዶችም በቦታው ሲገኙ ከሃይማኖታዊ ክዋኔ በተጨማሪ የጎንደርን ጥንታዊ፣ ታሪካዊ እና ባህላዊ ቅርሶችን እንዲጎበኙ ዝግጅት ተደርጓል።

እንግዳ አክባሪው ፣ ፍጹም የኢትዮጵያዊነት እሳቤ እና አመለካከት ያለው የጎንደር ህዝብ እንግዶችን ለመቀበል ቅድም ዝግጀት ማጠናቀቁን ነው መምሪያው ያስታወቀው።

ባህረ ጥምቀቱን ለማክበር ሲደረግ የነበረው ሰፊ ዝግጅት መጠናቀቁን የጎንደር ከተማ ባህል ቱሪዝም እና ስፖርት መመሪያ አስታወቋል። ~ AMMA

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#DonaldTrump

የትራምፕ ደጋፊዎች ከፈጸሙት የአመጽ ድረጊት ጋር በተያያዘ ፣ የአሜሪካ ም/ቤት ፕሬዝዳንቱ በ25ኛው የአሜሪካ ሕገ መንግሥት ማሻሻያ መሰረት ከስልጣን እንዲወርዱ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስ ፣ ሀገሪቱን በአግባቡ መምራት ያልቻለ ፕሬዝዳንንት ከስልጣኑ ተነስቶ ምክትሉ መሪነቱን እንዲረከብ የሚደነግገውን 25ኛውን ማሻሻያ እንደማይተገብሩት ገልጸዋል፡፡

ይህንን ተከትሎም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንቱን በኢምፒችመንት ከስልጣን ለማውረድ ዝግጅት ጀምሯል፡፡

ምክር ቤቱ አመጽ በመቀስቀስ ወንጀል ፕሬዝዳንቱን ለመክሰስ ዛሬ ድምጽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ይህም ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን በአሜሪካ ታሪክ ለሁለተኛ ጊዜ ኢምፒችመንት የሚካሄድባቸው መሪ ያደርጋቸዋል፡፡

ትራምፕ ከኋይት ሀውስ ለመውጣት የቀራቸው 1 ሳምንት ቢሆንም ፣ ፕሬዝዳንቱ በኢምፒችመንት እንዲነሱ ባለቀ ሰዓት ሩጫ መጀመሩ ፣ በዋነኛነት ከዚህ በኋላ ለፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዳይቀርቡ ለማድረግ በማሰብ ነው፡፡ (አል ዓይን)

@tikvahethiopiaBOT
አዲስ አበባ ስታዲየም ሊታደስ ነው።

የኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን የአዲስ አበባ ስታዲየምን የዕድሳት ስራ ለማከናወን ስምምነት  መፈረሙን አስታወቀ።

ስምምነቱ የተፈረመው የዲዛይን ፣ የማማከርና የቁጥጥር አገልግሎቱን ከሚያከናውነው ዮናስ አባይ አማካሪ አርክቴክቸር እና ኢንጅነሪንግ ከተባለ ድርጅት ጋር ነው።

የዲዛይን ስራውን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ እንደሚያቀርብ ኮሚሽኑ ገልጿል።

የዲዛይን ስራው የካፍ ስታንዳርድን ጠብቆ እንደሚሰራ ነው የተገለፀው።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBO
ትራምፕ ከዩትዩብ ለ7 ቀን ታገዱ።

ዩቲዩብ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የድርጅቱን ደንብ ጥሰዋል በሚል አግዷቸዋል።

በጉግል የሚተዳደረው ዩቲዩብ፤ ፕሬዝዳንት ትራምፕ አዳዲስ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን እንዳይለጥፉ ወይንም ደግሞ በቀጥታ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን እንዳያጋሩ ለሰባት ቀን ያህል ማገዱን ያስታወቀ ሲሆን፤ እግዱ ከዚህም ረዘም ያለ ጊዜ ሊቆይ ይችላል ሲል አስጠንቅቋል።

ኩባንያው የዶናልድ ትራምፕን ገጽ፣ የድርጅቱን አመጽን አለማነሳሳት የሚለውን ደንብ ጥሷል ሲል ተናግሯል።

ፕሬዝዳንቱ ማክሰኞ ማታ በርካታ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ያጋሩ ሲሆን የተወሰኑት አሁንም በሰሌዳቸው ላይ ይገኛሉ።

ዩትዩብ ባገዳቸው የዶናልድ ትራምፕ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ውስጥ ምን እንዳሉ የጠቀሰው ነገር የለም።

ይህ ውሳኔ የተሰማው የተለያዩ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ፕሬዝዳንቱ ከዩቲዩብ እንዲታገዱ የሚጠይቅ ማስታወቂያ ለመልቀቅ ከዛቱ በኋላ መሆኑን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የሱዳን ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ተከሰከሰ።

አንድ የሱዳን ወታደራዊ ሄሊኮፕተር በ 'ጋዳሬፍ ግዛት' ከሚገኘው ዋድ ዛይድ አውሮፕላን ማረፊያ እንደተነሳ ወዲያውኑ ተከስክሶ በእሳት መያያዙን የሱዳን ዜና ወኪልን (ሱና) ዋቢ አድርጎ አል ዓይን ኒውስ ዘግቧል፡፡

በሄሊኮፕተሩ ውስጥ የነበሩ ሦስት (3) ግለሰቦች ተርፈዋል።

ሄሊኮፕተሩ በምን ምክንያት ሊከሰከስ እንደቻለ እስካሁን የተገለፀ ነገር የለም።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#DrLiaTadesse

ዶ/ር ሊያ ታደሰ የኮቪድ-19 ክትባትን ተደራሽ ለማድረግ በሚሰራ አለም አቀፍ የንቅናቄ ቡድን ውስጥ በአስተባባሪነት መመረጣቸውን MoH ገለፀ።

የንቅናቄ ቡድኑ በአለም አቀፉ የጤና ድርጅት እና የክትባት ትብብር የሚመራ ሲሆን የኮሮናቫረስ ክትባት ለሁሉም ሀገራት በፍትሀዊነት ተደራሽ እንዲሆን የሚሰራ ነው፡፡

በቡድኑ አስተባባሪ ሆነው የተመረጡት የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፣ የኢንዶኔዢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬትኖ ማርሱዲ እና የካናዳ የአለም አቀፍ የልማት ሚኒስትር ካሪና ጉልድ ናቸው፡፡

ቡድኑ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላላቸው 92 የአለማችን ሀገራት ተደራሽ እንደሚሆን ነው ያስታውቀው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Ethiopia

ፕሬዚደንት ሣህለወርቅ ዘዉዴ የባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርነትና የአምባሳደርነት ሹመት ሰጡ።

ፕሬዚዳንቷ በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 71 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት ሰባት የባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርነትና የአምባሳደርነት ሹመት ሰጥተዋል።

በዚህም ፦

- ወይዘሮ ደሚቱ ሀምቢሳ ቦንሳ

- ጄኔራል አደም ሞሐመድ

- አቶ ሌንጮ አየለ ባቲ

- አቶ ሀደራ አበራ አድማሱ

- አቶ ነቢል ማሀዲ አብዱላሂ እና

- አቶ መላኩ ለገሰ አድማሱን በባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርነት ሰጥተዋል።

እንዲሁም አቶ እሸቴ ወልደየስን በአምባሳደርነት የሾሙ መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አስታውቋል። ~ ENA

@tikvahethiopia
ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች ተገደሉ።

መከላከያ ሰራዊት አቶ ስዩም መስፍንን ጨምሮ ሌሎችም የህወሓት አመራሮች መደምሰሳቸውን አሳውቋል።

አመራሮቹ በተከዜ ወንዝ ዳርቻ አካባቢ ተደብቀው እንደነበር እና ከነ ጠባቂዎቻቸው እና ከወታደራዊ አመራሮቻቸው ጋር እንደተደመሰሱ ሀገር መከላከያ ገልጿል።

የተደመሰሱት አመራሮች ፦

1. አቶ ስዩም መስፍን - የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩ እንዲሁም ውጊያውን የመሩና ሰራዊቱ ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀስ ያዘዙ፣ በመጨረሻም በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ ውጊያ እንዲከፈት ትዕዛዝ የሰጡ፣

2. አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ - የህወሓት ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር የነበሩ

3. አቶ አባይ ፀሃዬ - የህወሓት ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር የነበሩ

4. ኮሎኔል ኪሮስ ሀጎስ - ከመከላከያ የከዱ ከነጥበቃዎቻቸው ተደምስሰዋል።

በሌላ በኩል በቁጥጥር ስር የዋሉ ወታደራዊ እንዲሁም የክልል አመራሮች ፦

1. ኮሎኔል ገብረመስቀል ገብረ ኪዳን - ከመከላከያ የከዱ
2. ኮሎኔል ፍስሃ ብርሃኔ - ከመከላከያ የከዱ፤
3. ኮሎኔል ዘረአብሩክ ታደሰ - ከመከላከያ የከዱ፤
4. ኮማንደር ገብረኪዳን አስገዶም - የልዩ ሀይል ክፍለ ጦር አዛዥ የነበሩ
5. አቶ መብራህቶም ክንዴ ሀይሉ - የክልሉ ውሃ ስራዎች ድርጅት ፋይናንስ ሀላፊ የነበሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ሀላፊ ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ፣ አሁንም የተደበቁ የህወሓት ቡድን አባላት በሰላማዊ መንገድ እጅ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል። ~ ኢዜአ

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#FireAlert

በጦራ ከተማ በተለምዶ "ኑርቴ ነዳጅ" አከባቢ ከፍተኛ የሆነ የእሳት አደጋ መነሳቱን የከተማዋ ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት አስታውቋል።

እስካሁን ባለው ሂደት እሳቱን ለማጥፋት ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ እንዳለና የወራቤ ከተማ እሳት ማጥፊያ መኪና ወደ ስፍራው መንቀሳቀሱ ታውቋል።

መሰል አደጋዎች በሌሎች ወረዳዎችና ከተሞች እንዳይከሰቱ ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ የስልጤ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ መልዕክት አስተላልፏል።

ዝርዝር መረጃ አሰባስበን እናቀርባለን።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Tora

በጦራ ከተማ ከንግድ ባንክ በስተደቡብ ኑርቴ ነዳጅ ቤት አካባቢ የተነሳው ከፍተኛ የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።

የእሳት አደጋው መንሰኤ ምን እንደሆነ ለግዜው አልታወቀም።

Via Tora Town PR
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የእሳት አደጋው ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ጦራ ከተማ 'ኑርቴ ነዳጅ ቤት' አካባቢ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደገ በህብረተሰቡ ከፍተኛ ርብርብ ሙሉበሙ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የእሳት አደጋው በሰው ህይወት ላይ ያደረሰው ጉዳት የለም።

በንብረት ላይ ያደረሰው ጉዳት እየተጣራ መሆኑን የከተማው ህዝብ ግንኙነት አሳውቋል።

@tikvahethiopia