TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጥያቄ #የጋራመኖሪያ_ቤቶች

ብዙ ሲባልለት የነበረው የ20/80 እና የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ከብዙ መናጋገሪያ ጉዳዮች በኃላ ሙሉ በሙሉ መሰረዙ ይታወሳል።

በቀጣይ ዕጣው መቼ ይወጣል ? የሚለው ለጊዜው ባይታወቅም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ " ከገጠመን ችግር ተነስተን ተገቢውን ሁሉ ጥንቃቄ በማድረግ በፍጥነት ዳግም እጣ በማውጣት በፍትሀዊነት ተደራሽ ለማድረግ እንሰራለን " ሲሉ አሳውቀዋል።

የቀጣዩ ዕጣ ከመውጣቱ በፊት ግን የተለያዩ አካላት ከወዲሁ እጅግ ልዩ ጥንቃቄ እንዲደረግ እና ታማኝነት ፍትሃዊነት እንዲረጋገጥ እየጠየቁ ይገኛሉ።

ቤት ይደርሰናል በማለት ረጅም ዓመታት እየተቸገሩ ቆጥበው በተስፋ የሚጠባበቁ ነዋሪዎች መካከል በርካታ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በቀጣዩ ዕጣ አወጣጥ ዙሪያ መልዕክታቸውን እየላኩ ጥያቄ እያቀረቡ ይገኛሉ።

ከነዚህ መካከል በቀጣይ ዕጣው የመውጣት ሂደት ላይ ሁሉም ለዕጣው ብቁ ሆነው የተገኙት ቆጣቢዎች ዕጣ ከመውጣቱ በፊት የስም ዝርዝራቸው በይፋ እንዲገለፅ ፣ ከዕጣው መውጣት በፊት ቤቶቹ ያሉበት ሳይት ቤቶቹ ካሉበት ወለል ጋር እንዲገለፅ፣ በሂደቱ ዕጣ የማይወጣላቸው ቤቶች አጠቃላይ ምን ያህል እንደሆኑ በግልፅ እንዲብራራ ጠይቀዋል።

ሌላው የ20/80 የባለ 3 መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች አሁን በሚወጣው ዕጣ ላይ እንዲካተቱ ጠይቀዋል።

ባለፈው ውድቅ በተደረገው የዕጣ አወጣጥ ከ1997 ተመዝጋቢዎች በአግባቡ እየቆጠቡ ያሉ ጥቂቶች መኖራቸው መግለፁ ይታወሳል (በቤት አስተዳዳሪው ቦርድ ውሳኔ ፕሮግራሙ ከሲስተም ውጭ ቢሆንም)።

እኚህ ቆጣቢዎች በባለፈው ዕጣ ውስጥ ያልተካተቱ ከመረጃ ውስንነትና በባለፈው ሲስተም ላይ የመረጃ መመሰቃቀልን ለመከላከል ሲሆን በልዩ ሁኔታ ለብቻቸው እንዲስተናገዱ መወሰኑ ይታወቃል።

የባለፈው ዕጣ አወጣጥ የ20/80 የባለሶስት መኝታ ቆጣቢዎች በቀጣዩ ላይ በዕጣው ላይ እንዲካተቱ ከወዲሁ እንዲሰራ ጠይቀዋል።

ሌላው የ2005 የ20/80 ባለሶስት መኝታ ቆጣቢዎች በርካታ ጥያቄ ያላቸው ሲሆን በ13ኛው ዙር ተጀምሮ በ14ኛው ዙር አለመካተቱ ጥያቄ እንደፈጠረባቸው ፤ ግልፅ የሆነ ማብራሪያም እንደሚፈልጉ በመግለፅ አስተዳደሩ በድጋሚ አጢኖት በቀጣይ ላይ እንዲካተቱ ጠይቀዋል።

በተለይ ማብራሪያውን እየጠየቁ የሚገኙት ላለፉት 9 ዓመታ እየቆጠቡ የሚገኙት ወገኖች በ13ኛው ዙር የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ወቅት በብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሳይቀር በ1997 ለባለ3 መኝታ የተመዘገበ የለም ሁሉም በ2005 የተመዘገቡ ስለሆነ ወደእነሱ ይተላለፋል ተብሎ ነበር ነገር ግን በ14ኛው ዙር አለመካከተቱ ግልፅ ማብራሪያ የሚያስፈልገው መሆኑን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia