TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አቶ በረከት ስምዖን⬇️

የAssociated Press ጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት ከአቶ በረከት ስምዖን ጋር ያደረገው ቃለ-ምልልስ።

(ከእንግሊዘኛ የተተረጎመ)
በኤልያስ መሰረት(AP)
=====☆☆☆======☆☆☆=====

▪️#ጥያቄ: በመጀመርያ ብአዴን ሰሞኑን እርስዎ ላይ ስለወሰደው እርምጃ እናውራ። እርምጃው የተወሰደበት አካሄድ ምን ይመስል ነበር? እርስዎስ እንዴት ያዩታል? ተቀብለውታል?

▫️አቶ በረከት : መሰረተቢስ እርምጃ ነው። እንዲታወቅ የምፈልገው እኔ ስብሰባው ላይ እንዳልነበርኩ እና ይህንንም ለእነርሱ ማሳወቄን ነው። ይህም የሆነው በአሁኑ ሰአት በክልሉ ላይ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ነው። በአሁን ሰአት ክልሉ ላይ የህግ የበላይነት የለም። እርግጥ እየሆነ ያለው የደቦ ፍርድ (mob justice) ነው። ይህንንም የክልሉ መንግስት መቆጣጠር የቻለበት ሁኔታ አይታይም። የተጠቀሰውን የንግድ ድርጅት በተመለከተ ስለተባለው ጉዳይ ያለኝ ሪከርድ ይመሰክራል።

በእኔ አስተዳደር ምንም #የጠፋ ነገር የለም። እንደ እኔ አስተሳሰብ ይሄ እርምጃ የመጣው አንደኛ ምክትል ጠ/ሚሩን በቅርቡ በተካሄደው የመተካካት ወቅት አለመደገፌ፣ በአቋሜ የማልደራደር ስለሆነ እና ፊት ለፊት ስለምናገር እንዲሁም የማጥራት አካሄድ (cleansing move) ነው። ምክንያቱም በረከት ከተለየ አካባቢ የመጣ ነው ስለሚባል ነው። እርግጥ ቤተሰቦቼ የኤርትራ ስር መሰረት ቢኖራቸውም እኔ ተወልጄ ያደግኩት ጎንደር ነው። የንግድ ድርጅቱን በተመለከተ አመታዊ የኦዲት ሪፖርት አለው። የእኛ ድርጅት ከኤፈርት ድርጅቶች አንደኛ ነው ታክስን በመክፈል ጨምሮ። በዚህ እኔ እርግጠኛ ነኝ።

▪️#ጥያቄ: በብአዴን የተወሰደውን እርምጃ ሲሰሙ አዘኑ፣ ደነገጡ ወይስ ሌላ ስሜት አጫረቦት?

▫️አቶ በረከት: ይሄ የሚጠበቅ ነገር ነበር። ይሄ ገና የመጀመርያቸው ነው (just a tip of the iceberg)። ወደፊት ሌሎች ተመሳሳይ ጉዳዮች ይመጣሉ ብዬ እገምታለሁ። እኔ ላይ ግን ምንም ችግር ይመጣል ብዬ አልፈራም ምክንያቱም ንፁህ ነኝ በዛ ላይ ለመብቴ እታገላለሁ።

▪️#ጥያቄ: የጠ/ሚር አብይን ፈጣን ለውጦች እንዴት ያዩዋቸዋል?

▫️አቶ በረከት: በእርግጥ ጠ/ሚሩ እየተገበሩት ያለው ለውጥ ኢህአዴግ ባለፈው ዲሴምበር ያሳለፈውን ነው። ሁላችንም የዚህ ለውጥ አካል ነበርን። ስለዚህ ስለ ለውጥ አስፈላጊነት ምንም ጥርጥር የለኝም። ጥሩ ለውጦች እያየን ነው።

▪️#ጥያቄ: ከሳምንታት በፊት እርሶ አሉበት ተብሎ የታሰበ በአማራ ክልል የሚገኝ ሆቴል እና መኪና ጥቃት ደርሶበት ነበር። ጥቃቱ አላስደነገጥዎትም? እርስዎስ በወቅቱ እዛ ነበሩ?

▫️አቶ በረከት: በወቅቱ እኔ #እቤቴ እንጂ እዛ #አልነበርኩም። ይህ የሚሳየው ግን በክልልሉ ያለው አስተዳደር ቁጥጥር ማጣቱን ነው። ህግ ያለው በቡድኖች እጅ ሆኖዋል።

▪️#ጥያቄ: የወደፊት የፖለቲካ ህይወቶ ምን ሊመስል ይችላል? ወይስ ፖለቲካ በቃዎት?

▫️አቶ በረከት: አሁን ያለው የፖለቲካ ሁኔታ ከእኔ ግለ- አስየሳሰብ ጋር አብሮ ስላማይሄድ አልቀጥልም። I'm thinking of coping with it Lidetu's style (የልደቱን ስታይል ለመከተል እያሰብኩ ነው)። አሁን ያለው ሁናቴ ፖለቲካን fair በሆነ መልኩ ለማካሄድ ያመቻል ብዬ አላምንም።

▪️#ጥያቄ: በቅርቡ የቀድሞው ጠ/ሚር ታምራት ላይኔ ባለቤት እርስዎ ላይ ወቀሳ ሰንዝረዋል። እርሳቸው በመታሰራቸው በእርግጥ ደስተኛ ነበሩ? ከሆነስ ለምን?

▫️አቶ በረከት: የእርሱ ጉዳይ በፍርድ ቤት ተወስኖ ከዛ ደሞ በህግ መሰረት ተፈቷል። 12 አመት ትምህርት ካላስተማረው እኔ ምንም ማረግ አልችልም። እስር ላይ የቆየው ባላደረገው ነገር አይደለም። ማንም ጣቱን ወደ እኔ አሁን ላይ ቢቀስር ለእኔ ምንም ማለት አይደለም።

▪️#ጥያቄ: አንድ ምክር ለጠ/ሚር አብይ ለግሷቸው ብልዎት እርሱ ምን ይሆናል?

▫️አቶ በረከት: እኔ እየሰራህ ያለውን ጥሩ ስራ ቀጥልበት ነው የምለው። ቃል የገባሀቸውን ነገሮችም ፈፅማቸው ልለው እወዳለሁ። ይህ የይቅርታ እና ምህረት ግዜ ወደፊትም መቀጠል አለበት። ዋናው ግን ይህ ሀገር sensetive ስለሆነ የ balance ስራ ሁሌ መሰራት አለበት። ጠ/ሚሩ እንዲሳካላቸው እመኛለሁ።

▪️#ጥያቄ: ጠ/ሚሩ ሹመት ሊሰጥዎ አስበዋል እንበል። ሹመቱን ይቀበላሉ ወይስ በተቃራኒው?

አቶ በረከት: በፍፁም! የእስካሁኑ ይበቃኛል።

📌ማሳሰብያ: ይህ ለAP ዜና ታስቦ የተደረገ እና አንድ ሁለት ፓራግራፍ ከእሳቸው ለማግኘት ታስቦ የተደረ ቃለ መጠይቅ ነው። ስለዚህ አላማው ለአለም አቀፍ ዜና መሆኑን ተረድታችሁ ይሄንን ሳይጠይቅ፤ ያንኛውን ሳያነሳ እንደማትሉ ተስፋ አረጋለሁ።

©ኤልያስ መሰረት(የAP ጋዜጠኛ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ፖሊስ ተጨማሪ 8 ቀን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ተፈቀደለት።

ቀሲስ በላይ መኮንን በሃሰተኛ ሰነድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአፍሪካ ኅብረት የባንክ ሒሳብ ወደ ሌላ የባንክ ሒሳብ ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማዘዋወር ሲሞክሩ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወሳል።

በተጠረጠሩበት ወንጀል ዛሬ ለ2ኛ ጊዜ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበዋል።

ከእሳቸው ጋር ሌሎች 2 ግለሰቦች ያሬድ ፍስሃ እና ጣባ ገናና የተባሉ ቀርበዋል።

ከዚህ ቀደም ለፌዴራል መርማሪ ፖሊስ 7 ቀን መሰጠቱ ይታወሳል።

በዚህ ጊዜ መርማሪ ፖሊስ ምን እንደሰራ ለችሎቱ አስረድቷል።

ፖሊስ ምን አለ ?

- " የምስክሮችን ቃል ተቀብያለሁ። "
- " በተጠርጣሪዎች እጅ ላይ የተገኘ ኤሌክትሮኒክስ ምርመራ እንዲደረግ ለሚመለከተው ተቋም ጠይቂያለሁ። "
- " የቴክኒክ ምርመራ እንዲሰጠኝ በደብዳቤ ጠይቂያለሁ። "
- " ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ለአፍሪካ ህብረት የሰነድ ማስረጃዎች እንዲሰጠኝ ጠይቂያለሁ። "
- " ተጠርጣሪዎቹ በስማቸው የሚገኙ ሂሳቦችን ለማጣራት ማረጋገጫ እንዲሰጠኝ በደብዳቤ ጠይቂያለሁ። "
- " በወቅቱ የነበረ የካሜራ ቅጂ ጠይቂያለሁ። "
- " ለወንጀል ተግባር የዋለ ተሽከርካሪ ማረጋገጫ ከሚመለከተው ተቋም ጠይቂየለሁ። "
- " በቀሲስ በላይ ሁለት መኖሪያ ቤቶች ላይ ብርበራ አድርጌ በብርበራ የተገኘ የጦር መሳሪያ ህጋዊነት የማረጋገጥ ስራ እየሰራሁ ነው። " ... ብሏል።

የቀሩ ስራዎች ፦
- " ከተለያዩ ተቋማት የሰነድ ማስረጃ መሰብሰብ። "
- " ተጨማሪ ምስክሮችን ቃል መቀበል። "
- " ግብረአበሮችን ተከታትሎ መያዝ። "
- " ተጨማሪ ሀብት የማፍራት ተግባሮች ላይ የማጣራት ስራ መስራት ሌላም ሰፊ የምርመራ ስራ ስለሚያስፈልግ ተጨማሪ የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ " ብሏል።

የተፈጸመው ድርጊት " ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያለንን መልካም ግንኙነት ጥላሸት የሚቀባ ተግባር ነው " ብሏል።

ተጠርጣሪው ቀሲስ በላይ መኮንንን ጨምሮ ሌሎቹም ተጠርጣሪዎች በ6 ጠበቆች ተወክለው ነው የቀረቡት።

ጠበቆቻቸው ምን አሉ ?

° " የቀረበው የጊዜ ቀጠሮ መጠየቂያ ምክንያቶች ደንበኞቻችን ተጨማሪ በእስር ለማቆየት የሚያስችል አይደለም " ብለዋል።

° " ቀሲስ በላይ የተገኘው የጦር መሳሪያ ህጋዊ ነው። ሀብት ማፍራት ከተጠረጠሩበት ወንጀል ጋር ሊገናኝ አይገባም " ብለዋል።

° " የሃይማኖት አባት መሆናቸው ፣ የልማት ስራ አስተባባሪ በመሆናቸው ፣ ቋሚ አድራሻ ያላቸው በመሆኑ ቢወጡ ከመንግስት ተቋማት የሚመጡ ማስረጃዎችን የማጥፋት አቅም የላቸውም " ብለዋል።

ስለሆነም የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።

ቀሲስ በላይ መኮንን ምን አሉ ?

ወንጀል አለመፈጸማቸውን ገልጸዋል።

ለሀገር እንዲሁም ፖሊስ ተባባሪ መሆናቸውን ተናግረዋል።

➡️ " ምሽት ላይ #እቤቴ_እየሄድኩ ጠዋት ላይ ልምጣላችሁ " በማለት ፖሊስን መጠየቃቸውን ለችሎቱ አስረድተዋል።

ከእሳቸው ጋር አብረው የታሰሩት #ሹፌራቸው እና #አጃቢያቸው እንደሆኑ ገልጸው ምንም የወንጀል ተሳትፎ በሌለበት ሁኔታ ከኔ ጋር ተጨማሪ ጊዜ በእስር ማቆየት ተገቢ አይደለም በማለት የዋስትና መብታቸው እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።

ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ቢወጡ ማስረጃ ሊሰወር ይችላል በማለት የዋስትና ጥያቄያቸውን ተቃውሟል።

የግራ ቀኝ ክርክሩን የተመለከተው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ተጠርጣሪው ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ለጊዜው በማለፍ ለፖሊስ የ8 ቀን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ፈቅዷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ ፥ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት (#ኤፍቢሲ) መሆኑን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia