TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የነዋሪዎች መታወቂያ መታደል ጀመረ‼️

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጊዜው #አቋርጦት የነበረውን ነባሩን የነዋሪዎች መታወቂያ እንደገና ማደል መጀመሩን ካፒታል አስነብቧል፡፡ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ኮምፒውተር ላይ የጣት አሻራን በመስጠት ሊያትመው ባሰበው አዲስ የነዋሪዎች መታወቂያ ላይ #በብሄር ማንነት ፋንታ #የደም_ዐይነትን ለማስፈር አቅዶ ነበር፡፡ ሆኖም ባጋጠመው የሶፍትዌር ቴክኖሎጅ ችግር እና በባለድርሻ አካላት ቅንጅት ማነስ ሳቢያ ተግባራዊ ማድረግ አልቻለም፡፡ እናም ቀደም ሲል በ5 ብር ይሰጥ የነበረውን ነባሩን የቀበሌ መታወቂያ እንደገና ለነዋሪዎች በ10 ብር ክፍያ መስጠት ጀምሯል፡፡ ለመታወቂያ ዕድሳት ከ10-20 ብር፣ የጠፋውን ለመተካት ደሞ ከ10-30 ብር ይከፈላል፡፡ በቅርቡ ግን ሁሉንም ነገር አስተካክየ አዲሱን መታወቂያ ተግባራዊ አደርጋለሁ ብሏል- ኤጀንሲው፡፡

via wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ፦

"የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር የከተማውን ፕላን ለማስጠበቅ አረንጓዴ ቦታዎችን፣ ወንዝ ዳርቻዎችን፣ አስተዳደሩ ካሳ ከፍሎባቸው ቤት የተሰራባቸውን እና ባለሃብቶች #ከተፈቀደላቸው በላይ የያዙትን ቦታ ላይ የተሰሩትን ቤቶች ዛሬ ማፍረሱ ይታወቃል። ሆኖም በFB ገጽ ላይ Etiopian DJ የኢትዮጵያ ሙዚቃ የቤቶችን ፈረሳ በተመለከተ #በብሄር ላይ የተመሰረተ ፈረሳ ነው፣ ሚዲያ እንዳይገባ ተከልክሎአል ከሁሉ በላይ ደግሞ ሁለት ሰው #ሞቶል እንዲሁም ቆስለዋል በማለት FB ላይ የለጠፈው ነገር ፍጹም #ውሸት እና በብሔር ላይ የተመሰረተ ፈረሳ የለለ ሚዲያዎችም የነበሩ እና አንድም ሰው እንኮን ሊሞት የቆሰለም ያልነበረ መሆኑን ከተቆቆመው ኮማንድ ፖስት ማረጋገጥ ተችሎል።በመሆኑም Ethiopian Dj ም ሆነ ለሎች በ FB ላይ የምለጥፉ ከእንደዚህ አይነት ድርጊት ብርቁ መልካም ነው እንላለን።"

©ኤልያስ መሰረት
@tsegabwolde @tikvahethiopia