TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Sidama

" ... እንዲዘጉ በተወሰነባቸዉ 17 ኮሌጆች ልጆቻችሁን ከማስተማር ተቆጠቡ " - የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ

በሲዳማ ክልል የሚንቀሳቀሱ ኮሌጆችና የሙያ ማሰልጠኛዎች በአብዛኛዉ ከደረጃ በታች መሆናቸዉ ተከትሎ 17 ኮሌጆች #መዘጋታቸዉ ተገለጸ።

የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ኮሌጆችና የሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ጋር ባካሄደዉ የኦዲት ሪፖርትና የዉይይት መድረክ በክልሉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ኮሌጆችና የሙያ ማሰልጠኛዎች በህገወጥ ስራ መሰማራታቸዉ ገልጿል።

የቢሮዉ ሃላፊ የሆኑት ወይዘሮ ሀገረጽዮን አበበ በዚህዉ ወቅት እንደገለጹት ኮሌጆቹ ገበያመር የሆነ አካሄዳቸውና በህግ የመመራት ስታንዳርዳቸዉ በስራ ላይ እንዲቆዩ መሠረት መሆኑን ገልጸዋል።

በእለቱ የኦዲት ግኝቱን ተመስርቶ 17 ኮሌጆች ስራ እንዲያቆሙ ሲወሰን ኮሌጆቹ በመላዉ ሲዳማ የጀመሯቸዉን የማስተማር ስራዎች አቁመዉ ፈቃዳቸዉን እንዲመልሱ ተነግሯቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ያላግባብ #ሳያስተምሩ_አስመርቀዉ ስራ ፈላጊና የሀገር ሸክም በማድረጋቸዉ በህግ ተጠያቂ እንደሚደረጉ የተገለጸ ሲሆን ቢሮዉ እጁ ላይ ያለዉን መረጃ ባፋጣኝ ለክልሉ ፍትህ ቢሮ እንደሚልክ ገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪ ማህበረሰቡ እንዲዘጉ በተወሰነባቸዉ 17 ኮሌጆች ልጆቻቸዉን ከማስተማር እንዲቆጠቡ የተገለፀ ሲሆን ከዚህ በኋላ በመላዉ ሲዳማ ክልል ከገበያዉ በላይ የተማረ ሰዉ በመኖሩ የአካዉንቲንግ ማርኬቲንግና የሰዉ ሀይል አስተዳደር ትምህርቶችን መማርም ሆነ ማስተማር የተከለከለ መሆኑን ተገልጿል።

በህገወጥነት የተዘጉ ኮሌጆች ዝርዝር ፦

1. አትላስ ኮሌጅ - ሀዋሳ
2. ፊሪላድ ኮሌጅ - ሀዋሳ
3. ራድካል ኮሌጅ - ሀዋሳ
4. ስፓርታክ አፍሪካ ኮሌጅ - አለታ ጩኮ
5. ዩኒክ ስታር ኮሌጅ - አለታ ጩኮ
6. ዛክቦን ኮሌጅ - በንሳ ዳዬ
7. ሪፍት ቫሊ - ሀዋሳ
8. ዩንክ ስታር ኮሌጅ - ዳዬ
9. ኦሞ ቨሊ ኮሌጅ - ሞሮቾ
10. አፍን ፎር አፍሪካ - አለታ ወንዶ
11. ዩኤስ ኮሌጅ - ዳዬ
12. ዩኒክ ስታር ኮሌጅ - አርቤጎና
13. ፋርማ ኮሌጅ - ለኩ
14. ሮሜክ ኮሌጅ - ሀዋሳ
15. ካይዘን ዲዲ - ሁላ
16, ዩኒክ ስታር - ለኩ
17. ሄሊከን ኮሌጅ - ጭሬ

ኮሌጆቹ ለመዘጋታቸው የቀረበዉ ምክኒያት ምንድን ነዉ ?

* የኮሌጆቹ መምህራን የሲኦሲ ሰርተፊኬት አለመኖር
* የተማሪ ቁጥር ከስታንዳርድ በላይ መሆን
* ቋሚ መመህራን አለመኖር
* በአንድ ግቢ ድግሪና ቲቪቲ ማስተማር
* የመማር ማስተማር ቁሳቁስ አለመሟላት
* በቂ የሆነ የአስተዳደር መዋቅር አለመኖር
* ከተፈቀደላቸዉ ፕሮግራም ዉጭ ማስተማር የሚሉት ጉዳዮች ቀርበዋል።

መረጃውን የሀዋሳ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው ያደረሰን።

@tikvahethiopia