TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EuropeanUnion

የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሦስት ሃገራት የ23 ነጥብ 3 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

ከኢትዮጵያ በተጨማሪ የተደረገው ድጋፍ ሱዳን እና ኬንያን እንደሚያካትት ህብረቱ ባወጣው መግለጫ ገልጿል፡፡

ከ23 ነጥብ 7 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ውስጥ 18 ነጥብ 8 ሚሊየን ዩሮው በኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች የሚውል መሆኑን ነው የጠቀሰው፡፡

እንዲሁም ሁለት ሚሊየን ዩሮው ደግሞ ለሱዳን የተደረገ ድጋፍ መሆኑን ጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም 2 ነጥብ 9 ሚሊየን ዮሮ የሚሆነው ደግሞ በኬንያ የምግብ ዋስትና ለተጋረጠው አደጋ የሚውል መሆኑ ነው የገለጸው፡፡

የአውሮፓ ህብረት በፈረንጆቹ 2020 ለኢትዮጵያ ያደረገው ድጋፍ 63 ነጥብ 2 ሚሊየን ዩሮ መድረሱን ገልጿል፡፡

@tikvahethiopiaBot
#EuropeanUnion

የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ከተወያዩ በኋላ በሁሉም የትግራይ ክልል አካባቢዎች የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መስመር እንዲመቻች ጠየቁ።

የእርዳታ ድርጅቶች ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ የክልሉን አንዳንድ አካባቢዎች አንዲጎበኙ የተፈቀደላቸው ቢሆንም ይህ ከህወሓት ጋር ውጊያዎች የተካሄዱባቸውን ሁሉንም የክልሉን አካባቢዎች የሚያካትት አይደለም ተብሏል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ በምግብ አቅርቦት እጥረትና በዘረፋ ሳቢያ አሳሳቢ ነው ሲል ገልጾታል።

የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊው ጆሴፍ ቦሬል በትግራይ ክልል ውስጥ ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መስመር መመቻቸት አለበት ብለዋል።

ኃላፊው ጨምረውም ይህ ለኢትዮጵያ መንግሥት የቀረበ ጥያቄ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት መፈጸም ያለበት አስፈላጊ እርምጃ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

More : https://telegra.ph/BBC-01-10

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#EuropeanUnion

የአውሮፓ ህብረት ኢንተርናሽናል ፓርትነርሺፕ ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይን ከህብረቱ የቀውስ አስተዳደር ኮሚሽነር ጃኔዝ ሌናርቺች ጋር በመሆን ከአሜሪካ ልዩ መልዕከተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ጋር መነጋገራቸውን በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው ላይ ገልፀዋል።

ውይይታቸው ትኩረቱን በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ያለው ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እንዳደረገ ገልፀዋል።

ገንቢና ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ያሉት ኮሚሽነሯ፥ በትግራይ ያለውን ቀውስ ለማቆም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ትብብርና የተቀናጀ አካሄድ አስፈላጊ መሆኑን ከአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ጋር ተስማምተንበታል ብለዋል።

አሜሪካ በኢትዮጵያ፣ ኤርትራ ባለስልጣናት፣ በአማራ ክልል አስተዳደር እና የፀጥታ መዋቅር መሪዎች፣ በወንጀል የተሳተፉ የTPLF መሪዎች ላይ የጉዞ ማዕቀብ እና ለኢትዮጵያ መንግስት በምትሰጠው የምጣኔ ሃብትና የደህንነት ድጋፍ ዕቀባ መጣሏ ይታወሳል።

አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ የያዘችው አቋም ሌሎችም እንዳይከተሉ ስጋት ያደረባቸው አካላት በተለያየ አጋጣሚ ስጋታቸውን እያገለፁ ነው።

ኢትዮጵያ የአሜሪካ ማዕቀብ ለማንም ጠቃሚ እንዳልሆነና በማገናዘብ የተወሰነ እንዳልሆነ፣ በቀጠናው ሽብርተኞችን በመከላከል ረገድ አሉታዊ ተፅእኖ እንደሚኖረው ጉዳቱም ለአሜሪካም ጭምር የሚተርፍ እንደሆነ አስገንዝባለች።

ኢትዮጵያ አማሪካ ውሳኔዋን ታጤነዋለች ብላ ተስፋ እንደምታደርግም አሳውቃለች።

በተጨማሪ የአገር ነፃነት እንዲሁም ሉአላዊት የማይታለፍ ቀይ መስመር መሆኑንና በገንዘብም የማይቀየር የህልውና ጉዳይ መሆኑም አስረግጣ ተናግራለች።

@tikvahethiopia