#GreatEthiopianRun
የ20ኛው የ2013 ዓ.ም የታላቁ ሩጫ የወንዶች አሸናፊዎች ፦
1ኛ. አቤ ጋሻሁን - ከአማራ ማረሚያ
2ኛ. ታደሰ ወርቁ - ደቡብ ፓሊስ
3ኛ. ሚልኬሳ መንገሻ - ከሰበታ ክለብ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የ20ኛው የ2013 ዓ.ም የታላቁ ሩጫ የወንዶች አሸናፊዎች ፦
1ኛ. አቤ ጋሻሁን - ከአማራ ማረሚያ
2ኛ. ታደሰ ወርቁ - ደቡብ ፓሊስ
3ኛ. ሚልኬሳ መንገሻ - ከሰበታ ክለብ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#GreatEthiopianRun
የ20ኛው የ2013 ዓ.ም የታላቁ ሩጫ የሴቶች አሸናፊዎች ፦
1ኛ. ፅጌ ገ/ሰላማ - ከኢትዮ አትሌትክስ
2ኛ. መድን ገ/ስላሴ - ከንግድ ባንክ
3ኛ. ገበያነሽ አያሌው - ከመከላከያ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የ20ኛው የ2013 ዓ.ም የታላቁ ሩጫ የሴቶች አሸናፊዎች ፦
1ኛ. ፅጌ ገ/ሰላማ - ከኢትዮ አትሌትክስ
2ኛ. መድን ገ/ስላሴ - ከንግድ ባንክ
3ኛ. ገበያነሽ አያሌው - ከመከላከያ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#AddisAbabaPoliceCommission
የ2013 ቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
የ2013 ታላቁ ሩጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ነው የተጠናቀቀው።
ለውድድሩ በሰላም መጠናቀቅ የአ/አ ከተማ ነዋሪዎች፣ የፌዴራል ፖሊስ እና ሌሎች የፀጥታ አካላት፤ የፕሮግራሙ አዘጋጆች እና የተሳታፊዎች ላደረጉት ቀና ትብብር ኮሚሽኑ ምስጋና አቅርቧል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#update የኢንዶኔዢያ ባለስልጣናት የመንገደኞች አውሮፕላኑ ወድቆበታል ብለው ያመኑትን ቦታ ባሕር ላይ መለየታቸውን አስታውቀዋል። ዛሬ ከባሕር ውስጥ የአውሮፕላኑ የበረራ መመዝገቢያ ሳጥን ሳይሆን አይቀርም የተባለ ምልክት በፍለጋ ላይ በተሰማሩ ሠራተኞች ተገኝቷል። አውሮፕላኑ ወድቆበታል ወደተባለው የባሕሩ ክፍል ከ10 በላይ መርከቦች ከባሕር ኃይል ጠላቂ ባለሙያዎች ጋር ተሰማርተዋል። "በሁለት ቦታዎች…
#SriwijayaAirBoeing737
ጥቁር ሳጥኑ (የበረራ መረጃ መመዝገቢያው) ተገኘ።
ከጃካርታ ከተማ በተነሳ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ እንደተከሰከሰ የሚታመነው የኢንዶኔዢያ የመንገደኞች አውሮፕላን (Sriwijaya Air Boeing 737) ጥቁር ሳጥን መገኘቱን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጥቁር ሳጥኑ (የበረራ መረጃ መመዝገቢያው) ተገኘ።
ከጃካርታ ከተማ በተነሳ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ እንደተከሰከሰ የሚታመነው የኢንዶኔዢያ የመንገደኞች አውሮፕላን (Sriwijaya Air Boeing 737) ጥቁር ሳጥን መገኘቱን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EuropeanUnion
የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ከተወያዩ በኋላ በሁሉም የትግራይ ክልል አካባቢዎች የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መስመር እንዲመቻች ጠየቁ።
የእርዳታ ድርጅቶች ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ የክልሉን አንዳንድ አካባቢዎች አንዲጎበኙ የተፈቀደላቸው ቢሆንም ይህ ከህወሓት ጋር ውጊያዎች የተካሄዱባቸውን ሁሉንም የክልሉን አካባቢዎች የሚያካትት አይደለም ተብሏል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በትግራይ ክልል ያለውን ሁኔታ በምግብ አቅርቦት እጥረትና በዘረፋ ሳቢያ አሳሳቢ ነው ሲል ገልጾታል።
የአውሮፓ ሕብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊው ጆሴፍ ቦሬል በትግራይ ክልል ውስጥ ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መስመር መመቻቸት አለበት ብለዋል።
ኃላፊው ጨምረውም ይህ ለኢትዮጵያ መንግሥት የቀረበ ጥያቄ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት መፈጸም ያለበት አስፈላጊ እርምጃ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
More : https://telegra.ph/BBC-01-10

የማሌ ብሔረሰብ “የዶኦማ” ዘመን መለወጫ ክብረ በዓል ትላንት ተከበረ።
በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የማሌ ብሔረሰብ ለ7ኛ ጊዜ “የዶኦማ” ዘመን መለወጫ ክብረ በዓል ትላንት ተከብሯል።
በዓሉ ጥር መባቻ በየዓመቱ የሚከበር ነው።
በአንድ ንጉስ ስር 13 ባላባቶች በሚከውኑት ባህላዊ ስነ ሰርዓት ዓመቱ የሰላም፣ የጥጋብ፣ የአንድነት፣ የፍቅርና የብልጽግና እንዲሆን “ዖፃ” ወይም ፀሎት በማድረግ ዓመቱን የሚያስጀምሩት ልዩ ስፍራ ያለው ክብረ በዓል ነው።
የማሌ ብሔረሰብ ንጉስ አቶ እርባኖ ድልቦ ይህንን ስነ ስርዓት በበላይነት እንደመሩት ተገልጿል።
በበዓሉ ከዞኑ ከሁሉም ወረዳዎች፣ ከአጎራባች ዞኖች እና ወረዳዎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተገኝተው አጋርነታቸውን ለማሌ ልማት ማህበር በገንዘብ እና በተለያየ መንገድ ገልፀዋል። ~ SRTA

ከ3,500 በላይ ኢትዮጵያውያን ከሱዳን ተመለሱ።
ከ3500 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከሱዳን ወደኢትዮጵያ መግባታቸውን የመተማ ዮሐንስ አካባቢ የመንግስት ኃላፊዎች እና የኢሚግሬሽን ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ማስታወቁን ናሁ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
የመተማ ከተማ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ባለሞያ የሆኑት አቶ ስጦታው ጫኔ ፥ ኢትዮጵያውያኑ ሱዳን ውስጥ በተፈጠረው የኢኮኖሚ ቀውስ ምክንያት መመለሳቸውን ገልፀዋል።
ሱዳን (ገዳሪፍ አካባቢ) በግብርና እና በቀን ስራ ይተዳደሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል ብለዋል።
ከ80% በላይ የሚሆኑት ከካርቱም ነው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት።
ከሰሞኑ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አካባቢ በነበረው ውጥረት እና በሱዳን ባለው የኢኮኖሚ ቀውስ ኢትዮጵያውያኑ መመለሳቸውን ገልፀል።
አሁንም ከሱዳን ወደኢትዮጵያ የሚመለሱ ዜጎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል የኮሚኒኬሽን ባለሞያው ጠቁመዋል።
ከጥቅምት መጨረሻ ጀምሮ የሱዳን ጦር ምዕራብ ጎንደር አካባቢዎች የፈፀመውን ትንኮሳ የከትሎ አካባቢው ውጥረት ስፍኖበት መቆየቱን ቴሌቪዥን ጣቢያው በዘገባው አስታውሷል።

👆ኢትዮጵያ ፣ ሱዳን እና ግብፅ የሶስትዮሽ ስብሰባ የፕሬስ መግለጫ።
የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች በዛሬው ዕለት በበይነ-መረብ ስብሰባ አካሂደዋል።
ሱዳን የባለሙያዎቹ የተጨማሪ ሃላፊነት ቢጋር ካልተዘጋጀ በቀር ውይይት መካሄድ አይችልም የሚል አቋም መያዟ ተገልጿል።
ኢትዮጵያ የሱዳንን ጥያቄዎች ለመመለስ እንዲቻል በግድብ ደህንነት ፣ በመረጃ ልውውጥ እንዲሁም በሌሎች ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ መፍትሄ ለመስጠት ዝግጁነቷን ገልጣለች።
* ዝርዝር መረጃውን ከላይ ከተያያዘው መግለጫ ይመልከቱ።
Via Ministry of Water,Irrigation and Energy - Ethiopia

#SriwijayaAirBoeing737 ጥቁር ሳጥኑ (የበረራ መረጃ መመዝገቢያው) ተገኘ። ከጃካርታ ከተማ በተነሳ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ እንደተከሰከሰ የሚታመነው የኢንዶኔዢያ የመንገደኞች አውሮፕላን (Sriwijaya Air Boeing 737) ጥቁር ሳጥን መገኘቱን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"...በህይወት የሚገኝ ሰው ስለመኖሩ አጠራጣሪ ነው" - የኢንዶኔዥያ ጦር ጠ/አዛዥ
የኢንዶኔዥያ ጦር ጠቅላይ አዛዥ ትላንት ከጃካርታ ከተነሳ በደቂቃዎች ውስጥ ባህር ላይ ከወደቀው የመንገደኞች አውሮፕላን በህይወት የሚገኝ ሰው ስለመኖሩ አጠራጣሪ መሆኑ አሳውቀዋል።
ባህር ላይም የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች መገኘታቸውን ገልጸዋል።
አሁንም በርካታ የሰውነት ክፍል አካላት በባህር ላይ እየተገኘ መሆኑ ተገልጿል።
የመንገደኞቹ ቤተሰቦች እና ጓደኞች ይፋዊ መረጃ እየጠበቁ ነው።
ምንም እንኳን ከአደጋው የተረፈ ሊኖር እንደማይችል ቢነገርም አንዳንድ ቤተስቦች የሚወዷቸውን በህይወት ለማግኘት 'በተስፋ' ይፋዊ መረጃ እየተጠባበቁ ይገኛሉ።
አውሮፕላኑ በውስጡ 56 መንገደኞች (7 ህፃናትን ጨምሮ) ፥ 6 የበረራ ሰራተኞችን ይዞ ነበር ይበር የነበረው።

#COVID19Ethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,381
• በበሽታው የተያዙ - 524
• ህይወታቸው ያለፈ - 9
• ከበሽታው ያገገሙ - 79
አጠቃላይ 128,316 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,994 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 113,374 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
202 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።