TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AyatollahAliKhamenei

የኢራን መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ሃሚኒ በአሜሪካ እና ዩናይትድ ኪንግደም የተመረቱ ክትባቶች ኢራን ውስጥ እንደታገዱ በይፋ ተናገሩ።

አል ካሚኒ በክትባቶቹ ውጤታማነት ላይ እምነት እንደሌላቸው ተናግረዋል።

በUK እና US ክትባት ላይ ያላቸውን ስጋት ለኢራን ከፍተኛ ባለስልጣናት ካሳወቁ በኃላ በይፋ እንደተናገሩ ገልፀዋል።

አሊ ሃሚኒ "የነዚህ ሀገራት (US እና UK ማለታቸው ነው) ክትባቶች አላምናቸውም፤ ብዙ ጊዜ ውጤታማነታቸውን ለመሞከር በሌላ ሀገራት ሰዎች ላይ ነው የሚሞክሩት" ብለዋል።

በተጨማሪም ኣሊ ሃሚኒ ለፈረንሳይ ክትባትም በጎ ነገር እንደሌላቸው ገልፀዋል።

ከውጭ ሀገራት ከሚገቡት ይልቅ በሀገር ውስጥ የሚዘጋጅውን ክትባት እንደሚመርጡም አሳውቀዋል።

የኢራን መንግስት ከውጭ ክትባት ለማስገባት ጥረት እያደረገ ባለበት ውቅት ነው መንፈሳዊ መሪው ይህን ያሉት።

ባለፈው ወር የኢራን ማዕከላዊ ባንክ ገዥ አብዶለሳር ሃማቲ ክትባት ለመግዛት የመጀመሪያ ስምምነት እና ገንዘብ ለማዘዋወር ስምምነት መደረጉን ተናግረዋል፤ የክትባቱን ምንጭ ግን አልገለፁም።

ፕሬዝዳንት ሃሰን ሮሃኒ፥ "የኢራን የመጀመሪያ ምርጫ የሀገር ውስጥ ክትባት ሲሆን ቀጥሎ ደግሞ ከሌሎች ሀገራት ጋር በትብብር ለማዘጋጅት በመጨረሻም ከWHO መግዛት ነው" ብለው ነበር።

ኢራን ባለፈው ሳምንት በሰው ላይ የመጀመሪያው ምዕራፍ የክትባት ሙከራ ጀምራለች ፥ ለ3 ሰዎች ክትባቱ የተሰጠ ሲሆን 20 ሺህ ሰዎች ለሙከራው ተመዝግበዋል።

ኣናዱል የዜና ማሰራጫ ያነጋገራቸው ጤና ባለሞዎች ኢራን ካሳተናገደችው የወረርሽኙ ተፅእኖ እና ሀገሪቱ ላይ ከሚፈጠረው ጫ ጫ አንፃር የውጭ ክትባቶች ወደሀገር ውስጥ እንዲገቡ እና ጥቅም ላይ እንዲውሉ መክረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia