TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በዜግነትና በማህበራዊ ፍትህ ዙሪያ እሰራለሁ ብሎ በቅርቡ የተቋቋመው “#ኢዜማ” ዛሬ በጉባኤ የተመረጡ አባላቱን ይፋ ያደርጋል ተባለ፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበር የሸዋስ አሰፋ ለሸገር ራድዮ እንደተናገሩት የፓርቲው ከፍተኛ መሪዎች ከአባላት ጋር ዛሬ የሚተዋወቁበትን ፕሮግራም አዘጋጅተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲ በቅርቡ የተመሰረተ ሲሆን የፓርቲውን ሊቀመንበርና መሪ መምረጡ ይታወቃል፡፡ በፓርቲው መሪና በፓርቲው ሊቀመንበር መሀከል ግልፅ ልዩነቶችን በማስቀመጥ የመንግስትና የፓርቲ ስራ እንዲለይ ተደርጎ የተመሰረተ ፓርቲ ነውም ተብሏል፡፡

Via #ሸገርራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ/#ኢዜማ/ በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በነገው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ አሳውቋል። መግለጫውን የሚሰጠው ከጠዋቱ 4 ሰዓት ጀምሮ በቅሎ ቤት አካባቢ በሚገኘው የኢዜማ ጽሕፈት ቤት እንደሆነ ነው ፓርቲው የገለፀው። በሚሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሁሉም የሀገር ውስጥ እና የውጭ መገናኛ ብዙሃን እንዲገኙም ጥሪ አስተላልፏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህብራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) በ16 መስኮች የመጀመሪያ ደረጃ ረቂቅ ፖሊሰዎችን ማዘጋጀቱን ይፋ አድርጓል።

የፓርቲው መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሰጡት መግለጫ፥ ፖሊሲዎቹ ከ70 በላይ በሚሆኑ ምሁራን መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ምሁራኑ መንግስት እየተመራባቸው ያሉ ፖሊሲዎችን በዝርዝር እና በጥልቀት በመገምገም፤ የመጀመሪያ ደረጃ ሪቅቅ ፖሊሲ አዘጋጅተው አቅርበዋል።

በግብርና፣ ኢንደስትሪ፣ቱሪዝም፣ ትምህርት፣ የውጭ ጉዳይ፣ ንግድ እና ሌሎች መሰኮች ላይ በተዘጋጀው ሪቂቅ ፖሊሲ ላይም የፓርቲው አመራሮች ከምሁራኑ ጋር ውይይት አካሂደዋል።

ረቂቅ ፖሊሲው በፓርቲው አመራሮች እና በአዘጋጅ ምሁራን በዝርዝር ከተመከረበት በኋላ፤ በፓርቲው የተለያዩ መዋቅሮች ደረጃ ውይይት እንደሚካሄድበትም ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ከፓርቲው አባላት ጋር ከሚደረግ ውይይ በኋላ ረቂቅ ፖሊስው ስልጣን ባለው የፓርቲው አካል ፀደቆ የኢዜማ የፖሊሲ ሰነድ እንደሚሆንም ተነግሯል።

የኢዜማ መሪ ፕሮፌስር ብርሃኑ የፖለሲ ዝግጅቱ የፓርቲው የምርጫ ዝግጅት አካል ይሆን ወይ ተብለው ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ፥ ምርጫው በየትኛውም ጊዜ ይካሄድ ፓርቲው ፖሊሲዎችን የማዘገጃት ግዴታውን እየተወጣ ነው ብለዋል።

ሰለቀጠዩ ምርጫም በሰነዘሩት ሃሳብም የምርጫው ማከናወኛ ወቅት ከጊዜ ይልቅ በሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ቢወሰን የተሻለ ነው ብለዋል።

በሀገሪቱ አስተማማኝ ሰላም እና መረጋጋት መስፈኑ፣ ፓርቲዎች በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል በነፃነት ለመንቀሳቀስ የሚችሉበት አውድ መኖር እና ምርጫ ቦርድ ትክክልኛ ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ማረጋገጫ መስጠቱ፤ የምርጫውን መከወኛ ጊዜን የመወሰን አቅም እንዳለቻውም ፕሮፌሰር ብርሃኑ ተናግረዋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቐለ⬆️

ዛሬ መስከረም 4/2012 ዓ.ም፣ #ኢዜማ በመቐለ ከተማ ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛል።

Via ኢዜማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SomaliPP

በሶማሌ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ምን ተፈጠረ ? ፓርቲው ለሁለት ተከፍሏል ?

የሶማሌ ክልል የኮሚኒኬሽን ምክትል ኃላፊ አቶ መሀመድ ሮብሌ ፦

" ... ከዚህ በፊት በተለያዩ ቦታ ተሰጥቷቸው በክልሉ በቢሮ ኃላፊ እና በምክትል ኃላፊነት ደረጃ የነበሩና ከዛ በኃላ በነበሩ ግድፈቶች እና ድክመቶች ስራቸውን በትክክል አለመስራት ፣ በሙስና፣ በተለያዩ ምክንያቶች ከስልጣን የተባረሩ ሰዎች ናቸው።

ተሰባስበው Issue ለመፍጠር ሲሉ ነው እንጂ በፓርቲው መሃል ምንም የተፈጠረ ችግር የለም።

እነዚህ Alredy ከሲስተም የወጡ ሰዎች ናቸው። ምናልባት አንዳንድ በትክክለኛ መንገድ ተገምግመው ያልተባረሩ ሰዎች እዛ ውስጥ ሊኖሩ ይችላሉ ፤ ሌላው ግን በትክክል ከሲስተም የወጡና ህብረተሰቡን ማገልገል ሳይችሉ ፣ የተሰጣቸውን ስራ መስራት ሳይችሉ ቀይርተው የተባረሩ ናቸው። "

የሶማሌ ክልል የብልፅግና ፓርቲ የፅ/ቤት ኃላፊ እንጂነር መሀመድ ሻሌ ፦

" ... እኛም በሶሻል ሚዲያ ያየነው ነገር አለ። የነበረ ነገር ግን ከለውጡ ወዲህ የተለያዩ እርምጃዎች ሲወሰዱ ነበር ከስነምግባር እና ከሙስና ጋር በተያያዘ በዚህም ከስልጣን የተነሱ ሰዎች አሉ።

ትላንትና መግለጫ አውጥተዋል ተብለው በሶሻል ሚዲያ ያየኃቸው ሰዎች ነበሩ። አብዛኛው የካቢኔ አባል የክልሉ ማዕከላዊ ኮሚቴ ያኔ የለውጡ ጅምር አካባቢ የነበሩ ሰዎች ናቸው ነገር ግን በስራ ከኃላፊነት እንዲነሱ እና እንዲታገዱ ተደርጎ ነበር። ከአንድ አመት ተኩል ይሆናል።

አንዳንዶቹ የ #ኢዜማ እጩ ነበሩ የምርጫ አካባቢ፤ አሁን ትላንት ብቻ ነው በድንገት ያየናቸው እኛ ፓርቲ አባል ነን ብለው ፤ ከእኛ ጋር ከታገዱ እና ከስራ ከተነሱ ግማሹ ሁለት ዓመት ሆኖታል ግማሹ አንድ አመት ተኩል ፣ አንዳንዶቹ የሌላ ፓርቲ ዕጩ የነበሩ ናቸው።

ጉባኤ ላይ ውሳኔ የሚጠብቁ አሉ፤ እገዳ የተጣለባቸውም አሉ፤ አንዳንዶቹ ግን ጭራሽ አይመለከቱንም የኢዜማ እጩ የነበሩትን ዛሬ ላይ አባል ነው አይደለም ማለት ተገቢም አይመስለኝም "

አቶ ሲራጅ አደን (የሶማሌ ክልል የብልፅግና ፓርቲ አባል ነኝ ያሉ ሲሆን ፓርቲው ለሁለት መከፈሉን ይናገራሉ ) ፦

" የተፈጠረው የፓርቲው ለሁለት ተከፍሏል። የዚህ ምክንያት ያለ ግምገማ እና በብዛት በዝምድና እና በጋብቻ የተሳሰረ ስለሆነ ብዙ ጊዜ ህግ እና ደንብ አይከተልም በዛ ምክንያት ፓርቲው በሁለት በኩል ተከፍሏል።

አንድ ሰው ላይ በፓርቲ እርምጃ መውሰድ የሚቻለው በህግ እና ደንብ አሰራሩ ነው። ያለ ጉባኤ አንድ የአስፈፃሚ ኮሚቴ ወይም አንድ የማዕከላዊ ኮሚቴ አንድ ሰው ውስኖ ከህግ ውጭ አንድን ሰው ከፓርቲ ውጭ ነው ማለት አይችልም በጉባኤ ነው የሚችለው።

የተፈጠረው የ12 አባላት የፓርቲው ማሀከለኛ እና ሁለት የአስፈፃሚ ኮሚቴ ለፌዴራል የፓርቲው ፅ/ቤት አዲስ አበባ ደብዳቤ በመፃፍ ጣልቃ እንዲገባ ጠይቋል።

... ረብሻ አይደለም ህግ እና ደንቡን መከተል ነው። "

NB : የሶማሌ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ዛሬ መግለጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

ሁሉም አካላት ለሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ከሰጡት ቃል የተወሰደ።

@tikvahethiopia
#EZEMA

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ ( #ኢዜማ ) በመጪው ሰኔ 11 እና 12 / 2014 ዓ/ም ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሂዳል በዚህም ፓርቲውን በመሪነት እና በሊቀመንበርነት የሚመሩ አመራሮችን እንደሚመርጥ አስታውቋል።

ፓርቲው ይህን ያሳውቀው ዛሬ በዋና ፅ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ ነው።

ዕጩ አመራሮቹ ከጠቅላላ ጉባኤው መዳረሻ በፊት ለ19 ቀናት የምረጡኝ ቅስቀሳ እንደሚያደርጉ ፓርቲው ገልጿል።

ኢዜማ ጠቅላላ ጉባኤ የጠራው የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ በሚደነግገው መሰረት በሶስት ዓመት አንዴ መደበኛ ጉባኤ ማከናወን ስለሚገባው መሆኑን አመልክቷል።

በመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው የኢዜማ መሪ፣ ምክትል መሪ፣ ሊቀመንበር፣ ምክትል ሊቀመንበር፣ ዋና ጸሐፊ እና የፓርቲው የፋይናንስ ክፍል ኃላፊ እንደሚመረጡ ፓርቲው ይፋ አድርጓል።

በግንቦት 2011 የተመሰረተው ኢዜማን ላለፉት ሶስት ዓመታት በመሪነት እያገለገሉ የሚገኙት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሲሆኑ የምክትል መሪነት ስልጣን ያላቸው ደግሞ አቶ አንዷለም አራጌ ናቸው።

የኢዜማን የዕለት ተዕለት ስራ በሙሉ ጊዜ የመምራት ኃላፊነት የተሰጠው ለፓርቲው ሊቀመንበር ነው።

አቶ የሺዋስ አሰፋ የኢዜማ ሊቀመንበርነት ኃላፊነትን ተረክበው ፓርቲውን እየመሩ የሚገኙ ሲሆን ዶ/ር ጫኔ ከበደ በበኩላቸው የምክትል ሊቀመንበርነት ቦታውን ይዘው ቆይተዋል።

ኢዜማን በአሁኑ ወቅት በዋና ጸሐፊነት በማገልገል ላይ የሚገኙት አቶ አበበ አካሉ ናቸው።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢዜማ የኢዜማ የአመራሮች ምርጫ ውጤት እስካሁን (ምሽት 4:18 ድረስ) ይፋ ያልሆነ ሲሆን ፓርቲው ቆጠራው እንደተጠናቀቀ ይፋ እንደሚያደርግ አሳውቋል። የጉባኤው አባላት የአመራሮችን ምርጫ ውጤት እየተጠባበቁ ይገኛሉ። ተከታትለን እናሳውቃለን ! @tikvahethiopia
#NewsAlert #ኢዜማ

ፕሮፌሰር ብርሃኑ መሪ ፤ አርክቴክት ዮሐንስ ደግሞ ምክትል መሪ ሆነው ተመረጡ።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ሰኔ 26 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው ምርጫ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋን እና አርክቴክት ዮሐንስ መኮንንን የኢዜማ #መሪ እና #ምክትል_መሪ አድርጎ መርጧል፡፡

በጉባኤው ላይ ወደ 900 ገደማ የፓርቲው አባላት ያተሳተፉ ሲሆን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ 549 ድምፅ ማግኘታቸው ተገልጿል።

ከፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር ለመሪነት የተወዳደሩት አቶ አንዱአለም አራጌ 326 ድምፅ ነው ያገኙት። አቶ አንዱአለም ከፓርቲው ምስረታ አንስቶ የፓርቲው ምክትል መሪ ሆነው ቆይተዋል።

ለምክትል መሪነት የተወዳደሩት አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን በጉባኤው የተመረጡ ሲሆን ለቦታው በተፎካካሪነት ቀርበው የነበሩት አቶ ሀብታሙ ኪታባ ነበሩ።

@tivahethiopia
#አብን #ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በሀገራዊ ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ የመጀመሪያ ዙር ገንቢ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፆቻቸው ላይ አስታውቀዋል።

በቀጣይም #በሚያግባቡ_ሀገራዊ_ጉዳዮች ላይ ውይይቶችን ለማድረግና #የጋራ_አቋም ለመያዝ ከስምምነት ላይ መደረሳቸውንም ገልፀዋል።

ሁለቱ ፓርቲዎች የ " ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ / ህወሓት " ን ከሽብርተኝነት መዝገብ መሰረዝን በቅድሚያ የተቃወሙ ፓርቲዎች ናቸው።

ፓርቲዎቹ ተቃውሟቸውን በየተናጠል ባወጡት በመግለጫ አሳውቀዋል።

ይህ ከተሰማ ከሰዓታት በኃላ ነው ሁለቱ ፓርቲዎች በሚያግባቡ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይቶችን ለማድረግና የጋራ አቋም ለመያዝ ከስምምነት ላይ እንደደረሱ የተነገረው።

@tikvahethiopia
#ኢዜማ

ጉምቱው ፖለቲከኛ ከፓርቲያቸው ለቀቁ።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) መስራቾች አንዱ የሆኑት ጉምቱው ፖለቲከኛ አቶ አንዱዓለም አራጌ ከፓርቲው መልቀቃቸውን አስታውቀዋል።

የመልቀቂያ ደብዳቤው በትላንትናው እለት ለሚመለከተው አካል ገቢ ማድረጋቸውንም ገልጸዋል።

አቶ አንዱዓለም አራጌ ፓርቲውን ለምን ለቀቁ ? የመልቀቂያ ደብዳቤያቸው ላይ በዝርዝር አስረድተዋል ፤ ከላይ ተያይዟል ያንብቡት !

ምንጭ፦ የተረጋገጠው የማህበራዊ ትስድር ገፃቸው

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እግድ " የማህበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ቴሌቪዥን ጣቢያ " በመንግስት #በጊዜያዊነት ታገደ። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዛሬ እሁድ በፃፈው ደብዳቤ " ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ " ን በጊዜያዊነት እንዳገደ አሳውቋል። ባለስልጣን መ/ቤቱ ፤ ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ጣቢያ ዛሬ በግንቦት 13 ቀን 2015 ዓ.ም " ሰበር ዜና " በሚል ባሰራጨው መግለጫ ከሐይማኖት መገናኛ ብዙኃን…
#ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ በላከው መግለጫ ፤ የመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን በማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ላይ ያሳለፈው የእግድ ውሳኔ ህጋዊ ግዴታውን የጣሰ ነው ሲል ገልጿል።

ኢዜማ ፤ " የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን ከተልዕኳቸው ውጪ የገዢው ፓርቲ ልሳን ሆነው የህዝብን በደል እና የመንግሥትን ብልሹ አሰራር ጆሯቸውን ደፍነው ዘወትር የውዳሴ ዘገባ ለገዢው ፓርቲ እና መንግሥት በማቅረብ ለተጠመዱት የህዝብ መገናኛ ብዙኋን ምንም አይነት #ተግሳጽ እንኳ ሳያቀርብ ባለፈው እሁድ ግንቦት 13/2015 ዓ.ም ለማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት በፃፈው የእግድ ደብዳቤ ብሮድካስት ባለፍቃዱን በጊዜያዊነት ማገዱን ገልጿል " ብሏል።

" ይህ የእግድ ውሳኔ ምክንያቱ ሕጋዊ ሆነም አልሆነ በመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣኑ በአዋጅ ቁጥር 1238/2021 አንቀጽ 73 ፣ 76 እና 81(2) የተጠቀሱትን በቅድሚያ #ማስጠንቀቂያ የመስጠትም ሆነ የሚዲያ ተቋሙ #ራሱን_እንዲከላከል ቀድሞ እድል የመስጠት ሕጋዊ ግዴታውን የጣሰ ነው " ሲል ኢዜማ ገልጿል።

" ተቋማት የሚወስዷቸው እርምጃዎች በእርግጥም ሕግን ከማስከበር መነሻነት ይልቅ በማን አለብኝነት ድርጅታዊ ፍላጎትን ብቻ ታሳቢ ያደረገ ነው " ያለው ኢዜማ የመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን በማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ላይ የወሰደው እርምጃ ይህን በግልፅ ያስረዳል ብሏል።

ተቋማት ከእንደዚህ አይነት ወጥነትና ገለልተኝነት የጎደለው ተግባር በአስቸኳይ እንዲወጡም አሳስቧል።

ፓርቲው ፦

- የመገናኛ ብዙኀንን ጨምሮ ገለልተኛ ሊሆኑ የሚገባቸው ተቋማት ከገዢው ፓርቲ አባላት ተጽዕኖ ነፃ ማውጣት፤

- የመንግሥት እና የፓርቲ አሠራር የተለያዩ መሆናቸውን በሕግም በተግባርም ማረጋገጥ፤

- የሚወሰዱ እርምጃዎች ሕግ እና ሕግ ላይ ብቻ መሠረት ያደረጉ ብቻ ሊሆኑ ይገባል ብሏል።

ኢዜማ ፤ የመገናኛ ብዙኀን ባለሥልጣን የወሰደው እርምጃ " በአዋጅ ከተሰጠው ሥልጣን ወሰን ተላልፎ የወሰደው " ነው ያለ ሲሆን ፓርቲው ሕገ ወጥ ነው ያለው ውሳኔ እንዲሽር፤ ባለስልጣኑ ይህን ውሳኔ ያሳለፉትን አካላት ተጠያቂ በማድረግ ለሕዝብ እንዲያሳውቅ ጥሪ አቅርቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ኢዜማ

ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ  / ኢዜማ  መስራቾች መካከል የሆኑት የፓርቲው አባላት በገዛ ፍቃዳቸው ከፓርቲው አባልነት ለቀቁ።

ፓርቲውን በገዛ ፍቃዳቸው የለቀቁት ፦
- አቶ የሽዋስ አሰፋ
- ወ/ሮ ናንሲ ውድነህ
- አቶ ሀብታሙ ኪታባ
- አቶ የጁአልጋው ጀመረ
- አቶ ተክሌ በቀለ
- አቶ ኑሪ ሙደሲር               
- አቶ ዳንኤል ሺበሺ ናቸው።

ለምን ከኢዜማ ለቀቁ ?

በመሠረቱት ኢዜማ ፓርቲ ውስጥ በአንዳንዶች መሀል መጠነኛ የአቋም ልዩነት እንደነበር ገልጸዋል።

ይህ ልዩነት ግን በሂደት በውይይት እና በስራ እየጠበበ እና እየተስተካከለ ይሄዳል በሚል እሳቤ አብረው መጓዣቸውን አመልክተዋል።

የኃላ ኃላ ግን የአቋም ልዩነቱ ላይ የአካሄድም ልዩነት ተጨምሮበት ትግሉ መስመር ስቶ ከፍተኛ በሆነ በውስጠ ፓርቲ ትግል  ተጠልፈው ለመዎየት መገደዳቸውን ገልጸዋል።

" የኢትዮጵያ አሁን ሕዝብ በታሪኩ ገጥሞት የማያውቅ እዚህ መከራ ውስጥ ከመግባቱ በፊት መንገዳችንን እንድናስተካክል በፓርቲው ውስጥም በብዙ ታግለናል፡፡  " ያሉት እኚህ የፓርቲው አባላት " ስህተቶች ይታረሙ ይሆናል በማለት የትግሉን መድረክ ለማስፋት ብንሞክርም በተለያዩ ውስጣዊ እና ውጫዊ ምክንያቶች ማሳካት አልተቻለም " ብለዋል።

ኢዜማን ጠግኖ ለማዳን ያደረግነው ትግልም ከንቱ ቀርቷል ሲሉ አሳውቀዋል።

የኢዜማ ከፍተኛ አመራር ሀገርን ለመታደግ ሕዝብንና ፓርቲዎችን አስተባብሮ ከማታገል ይልቅ አገዛዙ እየፈፀመ ላለው ሀገር አቀፍ ግፍ ድጋፍ እየሰጠ ይገኛል ሲሉ ወቅሰዋል።

" ለዚህ ሥርዓት ምሶሶ እና ማገር ሆኖ በማገልገል የአንድነት ኃይሉን አቅም አላባ በማድረግ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ለመሆኑ የአባላት ብቻ ሳይሆን የሕዝብም ቅሬታ ሆኖ በመሰማት ላይ ይገኛል " ያሉት የፓርቲው አባላት " ይህም ኢዜማ ከቆመላቸው መሠረታዊ አላማዎች፤ መርሆች እና እሴቶች በመውጣት የገዢውን ቡድን እሴቶች እና አላማዎች እያራመደ እንደሆነ ግልፅ ሆኗል " ብለዋል።

በዚህም ፤ ኢዜማ የተለየ ቁመና የሌለውና ተክለ ሰውነቱም ሆነ ህልውናው በየዕለቱ ለትውልድ የሚተላለፍ ጠባሳዎችን ጥሎ ከሚያልፈው አገዛዝ የተለየ እንዳይመስል ተደርጎ እየተሠራ እንደነበር ግልጽ ሆኗል ሲሉ አሳውቀዋል።

በዚህና በሌሎች በርካታ ምክንያቶች ፓርቲውን ማዳን በማይቻልበት ሁኔታ ላይ በመደረሱ ፤ እንዲሁም " አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በሂደት በምንገልጻቸው በርካታ ምክንያቶች " ፓርቲውን ወደ ሃዲዱ ለመመለስ ያደረግነው ትግል ግቡን ስላልመታ ራሳችንን ከኢዜማ አባልነት አግልለናል ብለዋል።

(ሙሉ መልዕክታቸው ከላይ ተያይዟል)

NB. ከዚህ ቀደም ጉምቱው ፖለቲከኛ እና ከኢዜማ መስራቾች አንዱ አቶ አንዱዓለም አራጌ ኢዜማን በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቃቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) አንድ ዓመት የሞላውን የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አስመልክቶ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ፤ የፕሪቶሪያው ስምምነት ለሁለት ዓመታት የቆየው እና ከፍተኛ ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት ያስከተለው ጦርነት እንዲቆም እንዲሁም እንደገና የሰላም ተስፋ እንድንሰንቅ ማድረጉ በበጎ ጎኑ እናስታውሰዋለን ብሏል።

ፓርቲው ፤ ምንጊዜም ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚደረግ ጥረትን እንደሚያበረታታ ገልጾ ሥምምነቱን መልካም ጅማሮ እንደሆነ ገልጿል።

መንግሥት ከዚህ ቀደም ቅራኔዎችን በውይይት ለመፍታት ከተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች ጋር ካደረጋቸው ስምምነቶችና የውይይት ሙከራዎች በተሻለ መልኩ የፕሪቶሪያው ስምምነት ለሕዝብ በይፋ የተገለጸ መሆኑ መልካም የሚባል ጅማሮ እንደሆነ አመልክቷል።

" ነገር ግን አፈጻጸሙ ላይ በመንግሥት በኩል በታየ ዳተኝነት እና ግልጸኝነት መጉደል እንደ፦
🔹ሥምምነቱ መፈጸም አለመፈፀሙን፣
🔹ከስምምነቱ ጋር ተያይዞ የተገኙ ውጤቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን የተመለከቱ ጉዳዮችን የሚያመላክቱ መረጃዎች በአግባቡ ሲቀርቡ አለመመልከታችን፤
🔹በተለያየ ጊዜ የሕወሓት አመራሮች በተለያዩ መድረኮች ላይ የሚያሰሙት ግጭት ቆስቋሽ እና ተጨማሪ ውጥረቶችን የሚያጭሩ ገለፃዎችን መንግሥት ዐይቶ እንዳላየ በዝምታ ማለፉንና ማብራሪያ አለመስጠቱ ስንመለከት ሥምምነቱ በተባለው መልኩ ከመፈጸም ይልቅ ' በተቃራኒው እየሄደ ይሆን? ' የሚያስብል ስጋት ውስጥ ይጥላል " ብሏል ፓርቲው።

" ይህ የመንግሥት ቸልተኝነት እና በተለያየ ጊዜ የሚሰጡ ምክረ ሀሳቦችን አልሰማ ባይነት ለሌሎች ችግሮችም ሆነ አሁን በአማራ ክልል ለተፈጠረው የሰላም መደፍረስ ድርሻው ቀላል የሚባል ካለመሆኑ በተጨማሪ በክልሉ ላይ ለተፈጠረው ችግር ምክንያትነት ተብለው ከሚጠቀሱት ጉዳዮች መካከል ቀዳሚው ነው ቢባል ስህተት አይሆንም " ሲል ገልጿል።

ኢዜማ ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ አሳስቢያለሁ እንዳለው መንግሥት ከስምምነቱ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን በተገቢው ወቅትና ሁኔታ ለሕዝብ የማድረስ ከፍተኛ ድክመቱን አርሞ የዚህን ሥምምነት የአፈጻጸም ሂደት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እና የገጠሙ ችግሮች ካሉም በይፋ ለሕዝብ እንዲያሳውቅ ጠይቋል።

(ፓርቲው የላከው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ፤ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ም/ቤት የህዝብ ተወካይ አባሉ ህግ ተጥሶ እንደታሰሩበት ገለጸ።

ፓርቲው አባሉ በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈቱ ጠይቋል።

ኢዜማ ፤ በ2013 ዓ.ም በተደረገው 6ኛ ሀገር አቀፉ ምርጫ #ካሸነፈባቸው የምርጫ ክልሎች መካከል አንዱ በሆነው " ዛይሴ ልዩ ምርጫ ክልል " በሚገኙ አባላት ላይ በተለያየ ጊዜ ልዮ ልዮ ጥቃቶች እየደረሱ እንደሆነ አመልክቷል።

ፓርቲው በጋሞ ዞን የሚገኙ የመንግሥት አካላት ፦
- ከሕግ አግባብ ውጪ የሚፈጽሟቸውን ተግባራት እንዲያቆሙ፣
- በእነዚህ ድርጊቶች የተሣተፉ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ፣ 
- ያለአግባብ የታሠሩ አባሎቹ እንዲፈቱና አስፈላጊው ካሣ እንዲፈጸምላቸው በተደጋጋሚ መጠየቁን ገልጾ ፤ የዞኑ አመራሮች ግን ከዚህ ተግባራቸው ለመቆጠብ ምንም አይነት ተነሣሽነት የሌላቸው መሆኑን እና ህገወጥ ድርጊቱም ተባብሶ መቀጠሉን  አረጋግጠናል ብሏል።

በዚህም የዛይሴ ልዩ ምርጫ ክልል የቀድሞው የደቡብ ብ/ብ/ክልል የአሁኑ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ም/ቤት ተወካይ እና የኢዜማ አባል የሆኑት አቶ አማንያስ ጉሹና መታሰራቸውን አሳውቋል።

እስሩ " በኢፌድሪ ሕገመንግስት አንቀጽ 54(6) የተጠቅሰውን ድንጋጌ የተላለፈ ነው  " ያለው ፓርቲው " ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፍንጅ ባልተያዙበት እና ያለመከሰስ መብታቸው በም/ቤቱ ባልተነሳበት ሁኔታ ከታህሳስ 09 ጀምሮ በጋሞ ዞን አሰተዳደር ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው በአርባምንጭ ዙርያ ወረዳ ፖሊስ ጣብያ ይገኛሉ ፤ ፍ/ቤት ያለመቅረባቸውን አረጋግጠናል ብሏል።

ህግ ተስጥሶ የተሳሩት አባሉ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ም/ቤት ተወካይ የሆኑት አቶ አማንያስ ጉሹና በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል።

በሌላ በኩል . . .

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ኢዜማ ሰብሳቢ ኢንጂነር መልካሙ ሼጌቶ በፖሊስ ተይዘው መታሠራቸውን ፓርቲው አሳውቋል።

የክልሉ የፖርቲው ምክትል ሰብሳቢ አቶ አስቻለው ገ/ሚካኤል ለዶቼ ቨለ ሬድዮ በሰጡት ቃል ፤ ኢንጂነር መልካሙ በከፋ ዞን ፖሊስ አባላት የተያዙት በሥራ ገበታቸው ላይ እንዳሉ መሆኑና ፖሊስ #የፍርድ_ቤት ማስረጃ እንዳላቀረበ ገልጸዋል።

ፓርቲው እስሩን ህግን ያልተከተለ መሆኑ በመግለፅ ለካፋ ዞን ፍትሕ ቢሮ በፃፈው ደብዳቤ የአባሉ ጉዳይ በህግ እንዲታይ ጠይቋል። የተፈፀመውን ተግባራም አውግዟል።

የከፋ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኢ/ር መኮንን ገ/መድኅን ሰብሳቢው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰራጩት ጹሑፍ ተጠርጥረው መታሰራቸውን አረጋግጠዋል።

" መታሰሩ ትክክል ነው በሶሻል ሚዲያ የተላለፈ ነገር አለ። በዚህ በሶሻል ሚዲያ እርስ በእርሱ ህዝቡን የሚያጋጭ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ አንተ ተነስ እከሌ ተነስ  የእከሌ ዘር ብሎ ማስተላለፍ ይሄ የተከለከለ ነው። ይሄንን እያጣራን ስለሆነ በዚህ ጉዳይ ላይ የተጠረጠረ ነው።" ሲሉ ምላሻቸውን ለሬድዮ ጣቢያው ሰጥተዋል።

የፓርቲው የካፋ ዞን ኢዜማ ማስተባበሪያ በበኩሉ ፤ " እኛ እንደ ፖርቲ በግለሰቡ ሶሻል ሚዲያ አካውንት ህዝብን ከህዝብ ብሔርን ከብሔር የሚያጋጭ መልዕክት ፖስት ተደርጎ አላገኝንም " ብሏል።

በ24 ሰዓት ውስጥ  ቃል መስጠት እና በ48 ሰዓት ውስጥ ፍርድ ቤት መቅረብ ሲገባቸው ሁለቱም ሳያደረጉ እስከ አሁን እስር ላይ ይገኛሉ ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopia