TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ደሴ ከደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ጀርባ የሚኖሩ ነዋሪዎች ህዝብ መኃል በሚገኘው በሆስፒታሉ የቆሻሻ ማስወገጃ ምክንያት እየተሰቃቁ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል። ቆሻሻው በሚወገድበት ጊዜ እስከ ቤታቸው እንደሚገባ ጠቁመዋል። ይህ ሁኔታ የህፃናት ልጆቻቸውን ጤና እንዲሁም የራሳቸውን ጤና አደጋ ላይ እንደጣለውና እስከ ዛሬ ድረስ በተደጋጋሚ ቅሬታቸውን ለሆስፒታሉ ቢያቀርቡም መፍትሄ እንዳላገኙ ገልጸዋል።…
#ደሴ

“ አንድ ቀን ውሳኔ ተሰጥቶባቸው ከአካባቢ ብክለት ነጻ እንዲሆኑ ፣ ከቦታው እንዲነሱ የከተማ አስተዳደርን ውሳኔ ነው የምንጠብቀው ” - ደሴ ሆስፒታል

በአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ሆስፒታል ጀርባ የሚኖሩ ነዋሪዎች ፣ በሆስፒታሉ በኩል የሚቃጠለው ቆሻሻ ወደ ቤታቸው እየገባ እንደተቸገሩ ፣ መጀመሪያ ዝም ብሎ ሜዳ ላይ ሲቃጠል እንደነበር ፣ ዘመናዊ ማስወገጃ ከተሰራ በኋላ ግን ሙሉ ወደ ግቢዎች ውስጥ እንደሚገባ ፣ በተደጋጋሚ ለችግሩ መፍትሄ ቢጠይቁም መፍትሄ እንዳላገኙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አማረዋል።

መንደሮቹ በተለይም ህፃናት ልጆች ያሉባቸው እንደሆኑ የገለጹት ቅሬታ አቅራቢዎቹ ፣ አሁን ባሉበት ሁኔታ ከመኖር ለቤታቸው የሚመጥን ካሳ ከተከፈላቸው ቦታውን ለቀው መሄድም እንደሚሻላቸው ገልጸዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩት #ቪዲዮም በቃጠሎው ወቅት ቆሻሻው ወደ ቤት እንደሚገባ ያስገነዝባል።

ነዋሪዎቹ ላነሱት ቅሬታ ምን ምላሽ እንዳላቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው  የሆስፒታሉ ባለስልጣን ፤ “ አሁን ያ ሁሉ አልፎ በዘመናዊ መንገድ ተሰርቶ፣ ሕጋዊ ማስወገጃ ተሰርቶለት፣ ድሮ ከነበረው ችግር የወጣበት ቀን ነው ” ብለው፣ “ ከነበረው ችግር ወጣ ነው እንጂ ችግሩ ብሶ ቀጥሏል አልልም ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ በእርግጥ #ከሕዝብ_መኖሪያ ሊወጣ ተቋሙ ግድ ነው። አሁን ግን ያለው የቆሻሻ አወጋገድ በአዎሮፓ ህብረት እና በፈረንሳይ መንግሥት ተደግፎ Almost ሰባት ወሩ ከነሐሴ መጨረሻ ጀምሮ ዘመናዊ የሆነ፣ ስታንዳርዱን የጠበቀ ማቃጠያ ተሰርቶለታል ” ነው ያሉት።

እኚሁ ባለስልጣን አክለውም ፣ “ ግን ከሰው መሀል ነው። ያ በሕጋዊ መንገድ ሲቃጠል እንደድሮው እንኳ ብናኝ እንኳ አያርፍባቸውም። ጭሱ ግን ሊሸት ይችላል ” ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በበኩሉ ዘመናዊ ማቀጠያ ቢሰራም ቆሻሻው እየገባ መሆኑን ቅሬታ አቅራቢዎቹ ባቀረቡት መሠረት ማብራሪያ እንዲሰጡ ለባለስልጣኗ ጥያቄ አቅርቧል።

እሳቸውም ፤ “ ጭሱ ታካሚንም ይረብሻል፣ ከሕዝብ መሀል መሆናችን ነውና ዋናው ትልቁ ችግር። ጭሱማ እንዴት ይቀራል ? ተኔሬተር ነውኮ ግን የሚጨሰው ” ነው ያሉት።

“ እነዚህ አሁን የሚጨስባቸው ጠቅላላ በካዳስከርና በከተማ ማስተር ፕላን የሆስፒታሉ ቦታዎች ናቸው ” ብለው ፣ “ አንድ ቀን ውሳኔ ተሰጥቶባቸው ከአካባቢ ብክለት ነጻ እንዲሆኑ፣ ከቦታው እንዲነሱ የከተማ አስተዳደርን ውሳኔ ነው የምንጠብቀው ፣ እንጂ አሁን ላይ እጅግ የተሻለ ነገር ነው ያለው ” ሲሉ ገልጸዋል።

አክለውም፣ “ ለምን ብትል በጣም ብዙ ተሰቃይተው አልፈዋል፣ ከዚህ አሁን ካለው በላይ። ግን ከጎኑ ያለው ሰው አይሸተውም አልልህም። ግን ከፍታው ከአራት ሜትር በላይ ሆኖ፣ ከአምስት፣ ከስድስት ሜትር በላይ ከፍ ብሎ የሚጨስ የተሰራበት ዘመን ላይ ነው ያለነው ” ብለዋል። 

“ አሁን ላይ ራሱ ሞዲፋይ አለው ተነሬተሩ። የተሰራው ማቃጠያ #ሞዲፋይ አድርገው አሁንም እዛው ላይ የሰሩት ከፍታውን ካለው ጨምረው ሊሰሩት እያሰቡ ነው። በቅርብ ቀንም ይሰራል። ሁለተኛ ደግሞ ከውጪ ያልገባ ጭስ አልባ ማቃጠያ ማሽን አለን። በቅርብ ጊዜ (ከወር በኋላ) ይደርሳል። ብዙ ነገሮችን የሚቀንስልን ” ሲሉም ተናግረዋል።

ደሴ ሆስፒታል ጀርባ የሚኖሩ በርካታ ነዋሪዎች ግን ፤ በሆስፒታሉ የቆሻሻ ማስወገጃ በየዕለቱ ስቃያቸውን እያዩ እንደሆነ ፣ ከምንም በላይ ደግሞ የትንንሽ ልጆቻቸው ጤና አደጋ ላይ በመሆኑ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጥሪ አቅርቧል።

#TikvahFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia