TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#WorldBank

የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ለሚተገበሩ ሶስት ፕሮጀክቶች የሚውል የ907 ሚሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ አድርጓል።

ዛሬ አርብ በገንዘብ ሚኒሰቴር በተደረገ የፊርማ ስነ-ሰርዓት በኢትዮጰያ መንግስት እና በዓለም ባንክ የ907 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈርሟል።

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ እና የዓለም ባንክ ግሩፕ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ሚ/ር ኦስማን ዲዮን ናቸው የፈረሙት።

ስምምነቱ ሶስት ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ ይወላል ተብሏል ፦

- የ200 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት በኢትዮጵያ ውስጥ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የሚውል ነው።

- የ500 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት በሀገሪቱ ለሚከናወን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽነት እንዲሁም የግሉ ዘርፍ ካፒታል ተሳትፎንና ዘላቂ የፋይናንስ አማራጮችን ለማምጣት የሚያስችል ነው ፤ ከዚህ ውስጥ 100 ሚሊዮን ዶላር የሚውለው የግሉ ዘርፍ በኤሌክትሪክ አገልግሎት አሰጣጥ እና አቅርቦት ተሳትፎ እንዲኖረው ለማስቻል ነው፡፡

- የ207 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት በኢትዮጵያ ውስጥ የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ የሚያስከተለውን ጉዳት ለመቀነስ እና የበሽታው መከላከያ ክትባቶችን ውጤታማ እና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ እንዲዳረስ ለማድረግ የሚውል ነው።

Via Ministry of Finance -Ethiopia
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#WorldBank #Ethiopia

ኢትዮጵያና የአለም ባንክ የ10 ነጥብ 89 ቢሊየን ብር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ኢትዮጵያና የአለም ባንክ የ10 ነጥብ 89 ቢሊየን ብር የብድር ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የብድር ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ እና የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ የሱዳን፣ የደቡብ ሱዳንና የኤርትራ ተጠሪ ኦስማን ዲዮን ማፈራረማቸውን ኤፍ ቢ ሲ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#WorldBank

የምሥራቅ አፍሪካ አገራት በአስርት ዓመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት እንደተጋረጠባቸው የዓለም ባንክ ከሰሞኑ አስታውቋል።

የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እንዲሁም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጫና ተደማምሮ አንዳንድ አገራት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ድቀት እያጋጠማቸው መሆኑን ባንኩ ገልጿል።

ከዚህም ጋር ተያይዞ ዓመታዊ ትንበያውን ቀንሷል።

ባንኩ በተለይም የምሥራቅ አፍሪካ አገራት እና አንዳንድ የአውሮፓ ክፍሎች ተጎጂ ሆነዋል ብሏል።

ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት እና ዝቅተኛ የምጣኔ ሀብረት ዕድገት ጥምረት ከ1970ዎቹ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊመለስ እንደሚችልም ጠቁሟል።

አገራቱ በምግብ እና በነዳጅ ዋጋ መጨመር ምክንያት ቀውስ እያጋጠማቸው መሆኑም ተገልጿል።

የዓለም ባንክ ኃላፊ ዴቪድ ማልፓስስ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ የቀውሱን ሌላ ጎን ማየት ከባድ ነው ብለዋል።

አንዳንድ በማደግ ላይ ያሉ አገራት መንግሥታት እቃዎችን መግዛት አለመቻላቸውን እንዲሁም የብድር ዕዳ ውስጥ እየተዘፈቁ ነው ብለዋል ።

የባንኩ አዲስ የዓለም አቀፍ እድገት ትንበያ ከዜሮ በታች 2.9 በመቶ ሲሆን፣ ይህም በ80 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛው መቀነስ የታየበት መሆኑን ቢቢሲ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#WorldBank #Ethiopia

የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር የ600 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍና የብድር ስምምነት መፈራረሙን አገለፀ።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ፥ ከ600 ሚሊየን ዶላሩ ውስጥ 200 ሚሊየን ዶላሩ በድጋፍ መልክ ሲሆን 400 ሚሊየን ዶላሩ በብድር መልክ መሆኑን ገልጿል።

ስምምነቱ በኢትዮጵያ ያለውን የስርአተ ምግብ ለማሻሻል እና የምግብ እጥረት አደጋን ለመቀነስ የሚውል መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ፦ የገንዘብ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#WorldBank #Ethiopia

የዓለም ባንክ ግሩፕ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን አጋርነት አጠናክሮ ለማስቀጠል ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።

የዓለም ባንክ ግሩፕ ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ያለው ግጭት በእጅጉ እንደሚያስበው አመልክቷል።

በርካታ ግጭቶች እንዲሁም በታሪክ የታየው አስከፊ ድርቅና ሌሎች ሁኔታዎች ጋር ተዳምረው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ክፉኛ በመጎዳታቸው ሀገሪቱ ባለፉት አመታት ያስመዘገበችውን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገት አደጋ ላይ ጥሏል ሲል ገልጿል።

የዓለም ባንክ ግሩፕ የኢትዮጵያ ህዝብ የበለጠ የመቋቋም አቅምን ለመደገፍ እና በግጭት ሁኔታዎች ውስጥ ድጋፉን ለመቀጠል ካለው ስትራቴጂ ጋር በሚስማማ መልኩ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጥቅም ሲል ከኢትዮጵያ ጋር ያለው አጋርነት አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል ቁርጠኝነቱን አረጋግጧል።

በዚህም መሰረት የዓለም ባንክ ቡድን ኢትዮጵያ በመላ ሀገሪቱ የዜጎቿን መሰረታዊ አገልግሎቶች ማለትም የትምህርት፣ የምግብ ዋስትና፣ የጤና፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ የሴቶች አቅም በማጎልበት፣  የማህበራዊ እና የአካባቢ ጥበቃን ለማሟላት በምታደርገው ጥረት ድጋፉን እያደረገ መሆኑን አሳውቋል።

የዓለም ባንክ ግሩፕ ልማት ላይ ያተኮረ ድርጅት እንደመሆኑ መጠን በአባል ሀገራቱ የውስጥ አስተዳደር ጉዳዮች ላይ የመሳተፍ ሥልጣን ባይኖረውም የልማት ተራድኦ ቡድን አባል እንደመሆኑ መጠን ደግሞ የሁሉንም ኢትዮጵያውያን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መወያየቱን እንደሚቀጥል ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

(ተጨማሪ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
በዲጂታል እና ፋይናንሻል አካታችነት ሴቶችን ማብቃት!

ኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል ስርዓተ-ፆታ ልዩነትን ለማጥበብ እና የሴቶችን የዲጂታል ተካታችነት ለማሳደግ የሚያስችል ስምምነት “Connected Women” ኢኒሼቲቭ- ከ GSMA ጋር በባርሴሎና ስፔን ተፈራርሟል::

ስምምነቱ በሀገራችን የሴቶችን የሞባይል ኢንተርኔት እና የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት /ቴሌብር/ ተጠቃሚ ቁጥር እ.ኤ.አ እስከ 2026 በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ ያለመ ሲሆን ኩባንያው ለተግባራዊነቱ የተለያዩ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ እና በመተግበር እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ሴቶች የሚያጋጥሟቸውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መፍታት ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት አካታች የሞባይል ኢንተርኔት እና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎቶች ማቅረብን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡

በስምምነቱ ወቅት የኩባንያው ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ “ሴቶች በሀገራችን ልማት ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ኩባንያችን አሁን የሚታየውን የዲጂታል ስርዓተ-ፆታ ክፍተት ለማጥበብ የሞባይል ኢንተርኔትና የሞባይል ፋይናንሺያል አገልግሎቶችን ለሴቶች ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ሴቶች በዲጂታል ኢኮኖሚው ንቁ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል፡፡” ብለዋል፡፡

#DigitalEthiopia #DigitalAfrica #DigitalEconomy #EthiopianCommunicationAuthority #GSMA #AU #ITU #WorldBank #OECD #G6countries #SmartAfrica #HOPR #HOF
#ኢትዮ_ቴሌኮም

የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ በኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ማዕከላት መጀመሩን በይፋ ማብሰራችን ይታወቃል።

በማስከተል ምዝገባ በተጀመረባቸው ማዕከላት የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ተገኝተው አተገባበሩን ተመልክተዋል።

በዚህም ወቅት ለምዝገባው አስፈላጊ ግብአቶች መሟላታቸው እና የምዝገባ አገልግሎቱ በላቀ ፍጥነት መስጠት መቻሉን በተግባር መመልከት ችለዋል፡፡

አገልግሎቱ በሌሎች ተጨማሪ ማዕከላት የሚስፋፋ መሆኑም የተገለጸ ሲሆን ተገልጋዮች ስለዲጂታል መታወቂያ ጠቀሜታ እንዲረዱ የማድረግ ሥራ በስፋት እንደሚከናወን ተነግሯል።

ዜጎች በአቅራቢያቸው የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ የሚከናወንበትን የኢትዮ ቴሌኮም የአገልግሎት ማዕከል ለማወቅ ቴሌብር ሱፐርአፕ https://onelink.to/fpgu4m ውስጥ የተካተተውን አዲስ የአቅጣጫ ጠቋሚ መተግበሪያ ዳታ በማብራት ብቻ በነጻ መጠቀም ይችላሉ።

ተጨማሪ መረጃ ፦
https://t.iss.one/telebirr
https://t.iss.one/ethio_telecom

#Ethiotelecom #telebirr #DigitalAfrica #DigitalEthiopia #SmartAfrica #GSMA #ITU #WorldBank #NIDP
#CPPI #WorldBank

የዓለም ባንክ ከኤስ ኤንድ ፒ ግሎባል ማርኬት ኢንተለጀንስ ጋር የሚያዘጋጀው የኮንቴይነር ወደብ የአፈጻጸም መለኪያ (Container Port Performance Index - CPPI) የ2023 ደረጃ ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ አድርጓል።

ይህ መለኪያ ወደቦች የመረከብ አቀባበላቸውንና እንዴት እንደሚያስተናግዱ በአጠቃላይ ያላቸውን የስራ ቅልጥፍና እና አፈጻጸም የሚለካ ነው።

በዚህም ከ409 ወደቦች የራስ ገዟ #ሶማሌላንድ " #በርበራ " ወደብ 106ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የሶማሊያ ፤ " #ሞቃዲሾ " ወደብ ደግሞ 166ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የ " #ጅቡቲ " ወደብ ከመጨረሻ ተርታ 379ኛ ደረጃ ላይ ነው የተቀመጠው።

በዚህ የዓለም ባንክ የአፈጻጸም መለኪያ የበርበራ ወደብ ከሞቃዲሾ እና ጅቡቲ ወደቦች የተሻለ ደረጃ ተሰጥቶታል።

በአጠቃላይ ዓለም አቀፍ ደረጃ ከተሰጣቸው ከ405 ወደቦች በመጨረሻ ተርታ ማለትም 379 ላይ የተቀመጠው የጅቡቲ ወደብ በሀገሪቱ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል።

የጅቡቲ ወደብ በ2022 ከዓለም የተሰጠው ደረጃ 26ኛ ሲሆን በ2023 መለኪያ 379ኛ ላይ መቀመጡ ጅቡቲን አላስደሰተም።

ሀገሪቱ " የ2023 ደረጃ አሰጣጥ ምክንያታዊነት የጎደለው በመሆኑ ያሳስበናል " ያለች ሲሆን " ምን አይነት ሳይንስ ነው የሚያብራራው በዓለም ደረጃ ከ350 በላይ ነጥብ መጣል ? " ስትል ጠይቃለች።

በአንድ ዓመት ውስጥ እንዲህ ያለው ደረጃ መሰጠቱ በመለኪያው ላይ የተዓማኒነት ጥያቄ እንደሚያስነሳ ገልጻለች።

ጅቡቲ ፥ " ደረጃ አሰጣጡ ነጻ እና ከተእጽኖ የጸዳ ነው ወይ ? " ስትል ጠይቃ " ለማንኛውም አድሏዊም ሆነ አልሆነ ጅቡቲ ከሰሃራ በታች እና ምስራቅ አፍሪካ ትልቁ እና ቀልጣፋ ማዕከል ናት " ብላለች።

ሙሉ ዶክመንቱን በዚህ ያግኙ ➡️ CPPI 2023

#WorldBank

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የዓለም ባንክ የፕሬስ መግለጫ ፦ ዛሬ የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ እና ብድር አጽድቋል። 1 ቢሊየን ዶላሩ ድጋፍ ነው። 500 ሚሊየን ዶላሩ ብድር ነው።

#Ethiopia #WorldBank

@tikvahethiopia