TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ጊፋታ2012

በመስከረም 18/2012 ዓ.ም የሚከበረውን የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ ግፋታ በዓል በደማቅ ሁኔታ ለማክበር በቅድመ ዝግጅት ዙሪያ በወላይታ ሶዶ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱ የዞን አመራሮች፣ የዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ባለሙያዎች፣ የ16 ወረዳዎችና 6 የከተማ አስተዳደሮች የገጠር ዘርፍ፣ የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የወላይታ ብሔር ቅርስ ተንከባካቢ ማህበር እና የወላይታ የሀገር ሽማግሌዎች ምክር ቤት አባላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ውይይት መደረጉ ህብረተሰቡ በበዓሉ ዙሪያ ግልጽነት ፈጥሮ ተገቢ ጥበቃና እንክብካቤ በማድረግ ሳይበረዝ ትውልድ እንዲሻገር ያስችላል ተብሏል፡፡ በዓሉን የሀይማኖት በዓል አድርጎ የማሰብ የተሳሳተ አመለካከትን ለመቅረፍ በቀጣይ የተጠናከረ ውይይት እስከ ቀበሌ ድረስ የሚቀጥል ሲሆን ከሀይማኖት አባቶችና ሀገር ሽማግሌዎች ጋርም ውይይት የሚደረግ ይሆናል፡፡

ከበዓሉ አስቀድሞ የወላይታ ብሔር የባህል፣ ታሪክና ቋንቋ ሲምፖዚየም እና የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች የፎቶ ግራፍ ኤግዝቢሽን እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡
ከአጎራባች ህዝቦች ጋር የነበረውና ረጅም ዘመናት የዘለቀው ታሪካዊና ዘመን ተሻጋሪ ግንኙነት ለማጠናከር አጎራባች ህዝቦች እንዲሳተፉ እንደሚደረግም ተጠቅሷል፡፡

©Wolaita Zone Administration Public Relation Office
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጊፋታ2012

የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ ግፋታ በዓል በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ቅድመ-ዝግጅት መጠናቀቁን የወላይታ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ፡፡ በበዓሉ አከባበር የህዝብ ለህዝብ ትስስር ለማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

የወላይታ ህዝብ ከሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር የነበረውን አንድነት በይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችል በዞኑ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ የጉዞ ግፋታ ልዑካን ቡድን ወደተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች መጓዛቸውን ተነግሯል፡፡

በዚህም የጉዞ ግፋታ አባላት ለትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚኤልና ለአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ላቀ አያሌው ግብዣ አቅርበዋል፡፡

’የጉዞ ጊፋታ’’ ልዑካን ቡድን እንቅስቃሴ ዋና ዓላማው የዘንድሮውን የወላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ ግፋታ በዓል ከመላው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ጋር በጋራ ለማክበር ያለመ ነው ተብሏል፡፡

በመስከረም 15 ቀን በወላይታ ጉተራ አዳራሽ በሚካሄደው ሲምፖዚየም የብሔሩ ባህል፣ ታሪክና ቋንቋ አስመልክቶ በምሁራን የተዘጋጀው ጥናታዊ ጽሑፍ እንደሚቀርብ ደሬቴድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በዓሉ በዞኑ ማዕከል በመስከረም 18 ቀን 2012 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታዲየም እንደሚከበር ተጠቁሟል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጊፋታ2012

የዘንድሮ የወላይታ ዘመን መለወጫ በዓል ጊፋታ በተለያዩ ፕሮግራሞች ለማክበር ዝግጅቱን እንዳጣናቀቀ የዞኑ ባህልና ቱሪዝም እሴት መምርያ ኃላፊ አቶ ፀጋው ስምኦን ገልፀዋል። እንደ አቶ ፀጋው ገለፃ ከሆነ የወላይታ ዞን መለወጫ በዓል የብሔሩን ባህልና እሴትን ለትውልድ በማስተላለፍ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልጸው የዘንድሮ የጊፋታ በዓልን በተለያየ መልኩ ለማክበርም ዝግጅቶች መደረጋቸውንም ሃላፊው ገልፀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/TIKVAH-09-26

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጊፋታ2012

በወላይታ ሶዶ ከተማ የጊፋታ በዓል በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችም ትላንት ምሽት ወ/ሶዶ ገብተው አድረዋል። ትላንት ምሽት በሌዊ ሪዞርት የእራት ግብዣ ተደርጎ ነበር።

PHOTO: FB
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ጊፋታ2012

አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ዶ/ር ጌታሁን ጋረደው፣ አቶ ዳገቶ ኩምቤ ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ትላንት ምሽት በወላይታ ሶዶ ሌዊ ሪዞርት በነበረው የእራት ግብዣ ላይ በወላይታ ባህላዊ ሙዚቃ ሲወዛወዙ...

VIDEO: FB
@tsegabwolde @tikvahethioia
#ጊፋታ2012

የወላይታ ብሄር የዘመን መለወጫ ጊፋታ በዓል በወላይታ ዞን በሶዶ ከተማ ላለፉት ሳምንታት በደመቀ መልኩ በመከበር ላይ የሚገኝ ሲሆን ዛሬም ከተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ አመራሮችና የብሄሩ ተወካዮች በተገኙበት በመከበር ላይ ነው፡፡

Via #SRTA
@tsegabwolde @tikvahethiopia