TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢራቅ

የኢራቅ ፓርላማ #ግብረሰዶም / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን ከ10 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስር የሚቀጣ አዲስ ሕግ አርቅቋል።

በአዲሱ ሕግ መሠረት ጾታቸውን የቀየሩ ሰዎች ከ1 እስከ 3 ዓመት ሊታሰሩ ይችላሉ።

በአዲሱ ሕግ ፦

➡️ የግብረሰዶም / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚያበረታቱ፣ የሚያስተዋውቁ፤

➡️ ሴተኛ አዳሪነትን የሚያራምዱ፤

➡️ ጾታ ለመቀየር ቀዶ ህክምና የሚያደርጉ ዶክተሮችን፤

➡️ " ሆን ብለው " እንደ #ሴት የሚሆኑ ወንዶች እና " በሚስት መለዋወጥ " ላይ የተሠማሩ ሰዎች እስራት ይጠብቃቸዋል ፤ ዘብጥያም ይወርዳሉ።

የሕጉ ዓለማ ፥ " የኢራቅን ማህበረሰብ ከሞራል ዝቅጠትና ግብረ ሰዶማዊነት ከሚያደርሰው አደጋ ለመጠበቅ ነው " ተብሏል።

ረቂቁ መጀመሪያ ላይ ግብረሰዶማውያን #በሞት እንዲቀጡ የሚል የነበረው ቢሆንም በአሜሪካ እና በአውሮፓ ሀገራት ከፍተኛ ተቃውሞ መሻሻሉ ነው የተሰማው።

የኢራቅ ፓርላማ አባል የሆኑት አሚር አል-ማሙሪ ፥ " አዲሱ ሕግ #ኢስላማዊ እና ማህበረሰባዊ እሴቶችን የሚቃረኑ ልዩ ጉዳዮችን ለመዋጋት ትልቅ እርምጃ ነው " ብለዋል።

#አሜሪካ በውጭ ጉዳይ መ/ ቤቷ በኩል ሕጉን ፤ " ለሰብአዊ መብትና ነፃነት ጠንቅ ነው " በማለት ሕጉን ተቃውማለች።

" ሕጉ የኢራቅን ኢኮኖሚ የሚያቀዛቅዝ እና የውጭ ኢንቨስትመንትን የመሳብ አቅምን ያዳክማል" ብላለች።

የምዕራቡ ዓለም ሀገራት ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችም ሕጉን ተቃውመዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመረጃው ምንጮች #ቢቢሲ እና #ሮይተርስ መሆናቸውን ይገልጸል።

@tikvahethiopia