TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#State_of_Emergency የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ባወጣው መግለጫ ፤ በ " መጀመሪያ ምዕራፍ " ዕቅድ በትልልቆቹ የአማራ ክልል ከተሞች ፦ - ባሕር ዳር፣ - ደብረ ማርቆስ፣ - ደብረ ብርሃን፣ - ላሊበላ፣ - ጎንደር - ሸዋ ሮቢት ላይ አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ " የሕግ የበላይነት እንዲከበር አስደርጌያለሁ " ብሏል። በእነዚህ ከተሞች " በዘረፋ እና በጥፋት የተሰማራ ቡድንን…
#State_of_Emergency

ሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ።

በባሕር ዳር ፣ ጎንደር እና ደብረ ብርሃን ጨምሮ በሌሎች ከተሞች የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ።

የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ትዕዛዝና ክልከላ አውጥቷል።

በዚህም ፤ ባሕር ዳር ፣ ጎንደር ፣ ደብረ ብርሃን ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ሸዋ ሮቢትና ላሊበላ እስከ ነሐሴ 17/2015 የሚቆይ የሠዓት እላፊ ገደብ ጥሏል።

- የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት ከሚሰጡ ተሽከርካሪዎች፣
- የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት ሰጪ ባለሞያዎች
- የፀጥታ አስከባሪ ተቋማት ባልደረቦች ውጪ ለማንኛውም ሰው እና ተሽከርካሪ ከምሽቱ #አንድ_ሰዐት_በኋላ መንቀሳቀስ በጥብቅ ተከልክሏል።

የባጃጅ እና የሞተር ሳይክል እንቅስቃሴ ከነሐሴ 4 እስከ ነሐሴ 17 2015 ድረስ ፈጽሞ መከልከሉ ተገልጿል።

ከባጃጆችና ከሞተር ሳይክሎች በስተቀር ሌሎች የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ከነሐሴ 4 ጀምሮ ወደ ሥራ የመመለስ እና አገልግሎት የመስጠት ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

ከዚህ ባለፈ ፤ በባሕርዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ፣ ሸዋ ሮቢትና ላሊበላ የሕዝብ የአገልግሎት ሰጪ፣ የመንግሥት፣ የማኅበረሰብና የንግድ ተቋማት ከነሐሴ 4/2015 ጀምሮ ክፍት እንዲሆኑ ታዟል።

የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ ከፈቃዴ ውጪ በአማራ ብሔራዊ ክልል ከተሞች የአደባባይ ስብሰባ፣ ሰልፍና መሰል እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ፈጽሞ የተከለከለ ነው ብሏል።

በማንኛውም መልኩ የህዝብ እንቅስቃሴን የሚያስተጓጉል እና የትራንስፖርት አገልግሎትን የሚያሰናክል ድርጊትም በጥብቅ የተከለከለ ነው ሲል አስጠንቅቋል።

በተጨማሪ ፤ በክልሉ ለጸጥታ ሥራ ከሚንቀሳቀሱ የህግ አስከባሪ አካላት እና ከነዚህ አካላት ፈቃድ ውጭ የጦር መሣሪያ ይዞ መዘዋወር ፈጽሞ ተከልክሏል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሽፋን ከአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ትእዛዝ ውጭ ወቅታዊ ሁኔታን ሰበብ በማድረግ ግለሰቦችን ከመደበኛው ህግ አግባብ ውጪ ማሰር እና ማቆየት፣ የንግድ ቤቶችን ማሸግ እና መሰል እርምጃዎችን መውሰድ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia