TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈#የነዋሪዎችድምጽ

" የምንኖረው በኮንሶና አካባቢው ነው።

የመብራት ለቀናት መጥፋት እና መቆራረጥ ከፍተኛ ችግር በስራችን እና በህይወታችን ላይ እያደረሰ ነው።

ለቀናት ሲጠፋ ችግሩን ለመንግስት እንዳንናገር ድንገት ይመጣል መጣ ስንል ደግሞ በአንድ ሰአት ውስጥ ሁለት ሶስቴ ይቆራረጣል።

አሁን ላይ ስራ መስራት አስቸጋሪ ሆኗል።

በመብራት የሚሰሩ ስራዎች በተለይም ጸጉር ቤቶች ፣ ብየዳና የማሽነሪ ስራዎች እንዲሁም የእንጨት ቤቶች ላይ የሚሰሩ ሰዎች ተስፋ ቆርጠዋል።

እባካችሁ የሚመለከታችሁ አካላት ድምጻችንን ሰሙንና ችግሩን ፍቱልን።

ሌላው መንግስት በዚህ ሀኔታ እያለን እና አቅማችን በተዳከመበት ወቅት የግብር ማሰባሰብ እንቅስቃሴ ላይ መሆኑ አሳስቦናል። ነባራዊዉ ሁኔታ ካልተገናዘበና ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ ሙሉ በሙሉ ከስራ ውጭ ልንሆን እንችላለን " -
የኮንሶና አካባቢው ማህበረሰብ

#TikvahEthiopiaFamilyKonso

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
" ሁለት ወራት ከ18 ቀናት ነው መተከል የቆየሁት አንድም ቀን መብራት አልበራም " - ዶክተር መብራቱ አለሙ የኢትዮጵያ ፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሥራ አስፈፃሚ ፣ የቦሮ ዲሞክራሲ ፓርቲ (ቦሮ) የውጪ እና ዓለም አቀፍ ዘርፍ ኃላፊ ፣ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር መብራቱ አለሙ የቦሮ ዲሞክራሲ ፓርቲን ወክለው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በዚህ ቆይታቸው…
🔈#የነዋሪዎችድምጽ

• “ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚተገበረው ግን መቼ ነው ? ” - የቡለን ወረዳ ነዋሪዎች

• “ ‘ለምን አልመርጣችሁኝም ’ በማለት በበቀል ህዝብን መጉዳት ተገቢ አይደለም ” - ዶ/ር መብራቱ አለሙ


በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ ‘ ለምን ፓርቲውን መረጣችሁ ’ በሚል ሰበብ በደል እየደረሰባቸው መሆኑን የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አባላት እና ፓርቲው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

በአካባቢው ከዚህ ቀደም በነበረው የጸጥታ ችግር ሳይካሄድ ቀርቶ የነበረው ምርጫ በቅርቡ መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን፣ ምርጫውን ያሸነፈው የፓርቲው አባላት ላይ የ ' ቡለን ወረዳ አስተዳደር ' እስራትን ጨምሮ ድብደባ እያደረሰባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

“ እኛ የፈለግነውን የመምረጥ መብት አለን። ቦሮን መረጣችሁ በማለት እንዴት እንግልት ይደርስብናል ? ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚተገበረው ግን መቼ ነው ? ” ሲሉ ጠይቀዋል።

የፓርቲው የውጪና አለም ዓቀፍ ዘርፍ ኃላፊ፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ከፍተኛ አመራር ዶ/ር መብራቱ አለሙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ “ በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ አመራሮች ከምርጫ በኋላ ‘ለምን ቦዴፓን መርጣችሁ’ በሚል ሰበብ ” የሚከተሉትን ድርጊቶች በአባላቱ ላይ እየፈጸሙ መሆኑን ገልጸዋል።

➡️ ከቀበሌ ሚሊሻ አርሶ አደሮች ትጥቅ ማስፈታት
➡️ ነጋዴዎች ላይ ከፍተኛ ግብር መጫን
➡️ የመንግስት ሠራተኞችን ማዋከብና ፣ ማስፈራራት፣ ማሰርና ማዘዋወር
➡️ ነዋሪዎችን ‘በልማት ስራ አልተገኛችሁም’ በማለት በገንዘብ መቅጣት
➡️ መንግስታዊ አገልግሎት መንፈግ ለአብነት የመታወቂያ እድሳት፣ አዲስ የመታወቂያ ጥያቄ አለማስተናገድ፣
➡️ የድጋፍ ደብዳቤ መከልከል ተጀምሯል ሲሉ ድርጊቶቹን አስረድተዋል።

“ ከነበሩት ቦታ ያለአግባብ የተዘዋወሩ ሁለት የግብርና ባለሙያዎች ቅሬታ በጽሑፍ ሲያቀርቡ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ ወርቀቱን ተቀብሎ ቀዶ ከጣለ በኋላ ባለጉዳዮች እንዲታሰሩ አድርጓል ” ሲሉም ወቅሰዋል።

“ የባለጉዳዮችን አቤቱታ ቀዶ የጣለውን ትተው ባለጉዳዮችን አስረዋል ” ነው ያሉት።

“ ህዝቡ የፈለገውን ፓርቲ የመምረጥ መብት አለው። የፈለገውንም መርጧል ” ያሉት ዶ/ር መብራቱ ፥ “ መንግስት ደግሞ የመርጠውንም ያልመርጠውን እኩል የማገልገል ግዴታ አለበት ” ብለዋል።

“ ‘ ለምን እኔን አልመርጣችሁኝም ’ በማለት በበቀል ህዝብን መጉዳት ተገቢ አይደለም። ይህ አካሄድ መልሶ መንግስትን ይጎዳል። ይህ ድርጊት የወንጀል ተጠያቂነትን ያስከትላል ” ሲሉ አክለዋል።

“ በአጠቃላይ በወረዳው ላይ እየተካሄደ የሚገኘው ህገወጥ ወከባ የማይቆም ከሆነ በወረዳው ግጭት ሊፈጠር ይችላል ” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

ቅሬታ ለፈጠረው የመብት ጥሰት ቅሬታ የወረዳውን ምላሽ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈#የነዋሪዎችድምጽ

“ ከሆስፒታሉ ውጪ በ3 እጥፍ ዋጋ መድኃኒት እየገዛን ነው ” - ታካሚዎች

“ የአቅርቦት እጥረት አለ ” - የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል 

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል በመድኃኒት እጥረት ሳቢያ ታካሚዎች ከ3 እጥፍ በላይ በሆነ ዋጋ ከግል መድኃኒት ቤቶች መድኃኒት ለመግዛት እየተገደዱ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አማረሩ።

በርካታ ታካሚዎች ዋጋው ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ ህክምናቸውን እያቋረጡ መሆኑን፣ ችግሩ መቀረፍ ሲገባው ተባብሶ እንደቀጠለ አስረድተዋል።

በተለይ እንደ ሴፍትሪያክዞን፣ ዲ40% የመሳሰሉ መድኃኒቶች ከሆስፒታሉ ከጠፉ ወራት እንደተቆጠሩ ተናግረዋል።

“ ከሆስፒታል ውጪ በ3 እጥፍ ዋጋ መድኃኒት እየገዛን ነው” ያሉት ታካሚዎቹ፣ የላብራቶሪ ምርመራዎች ‘በተደጋጋሚ ተበላሽተዋል’ እየተባለ የምርመራ ከሆስፒታል ውጪ ለማሰራት እየተገደዱ መሆኑን ተናግረዋል።

ችግሩ ለምን ተፈጠረ ? ሲል ቲክቫህ የጠየቃቸው የጎንደር ዩኒቨርሲቲው ሆስፒታል ቺፍ ክሊኒካል ዳይሬክተር ዶ/ር መኳንንት መለሰ፣ “ አሁን ባለው የበጀት Ristriction፣ የፋይናንስ እጥረት ምክንያት አንዳንድ መድኃኒቶች አይኖሩም ” የሚል ምላሽ ተሰጥተዋል።

“ በወቅታዊ ችግር አሁን በወቅታዊ ችግር መንገድ ዝግ ነው። መድኃኒት ቀጥታ ከአዲስ አበባ በደጀን በኩል ነበር የሚመጣው አሁን በአፋር ክልል ነው የሚመጣው። የአቅርቦት እጥረት አለ ” ብለዋል።

➡️ ዲ 40% የተሰኘው መድኃኒት ያልነበረው “ትራውማ ካዡዋሊቲ” በዝቶ ስለነበር እንደሆነ፣
➡️ ይሁን እንጂ አሁን የመድኃኒት አቅርቦቱ እንዳለ፣ 
➡️ የላብራቶሪ ማሽኑ በመብራት መቆራረጥ ሳቢያ በመቆሙ ለሳምንት የተመላላሽ ታካሚዎች ህክምና ተቋርጦ እንደነበርና ማሽኑም እየተጠገነ መሆኑን አስረድተዋል። 

ሆስፒታሉ በቀን ከ3,000 በላይ፣ በአጠቃላይ ደግሞ 13 ሚሊዮን ለሚሆኑ ሰዎች የተለያዩ የህክምና አገልሎቶች እንደሚሰጥ ተገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ አሶሳ ከተማና ወምበራ ወረዳ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በመቋረጡ ችግር ላይ መውደቃቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ።

በተለይም በወምበራ ወረዳ አገልግሎቱ ከተቋረጠ አራት ወራት እንዳስቆጠረ ገልጸው፣ እስካሁን (ይህ ዘገባ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ) መፍትሄ እንዳልተገኙ ተናግረዋል።

ሞባይል በጀነሬተር ቻርጅ ለማድረግ እንኳ በየቀኑ 20 ብር እንደሚያወጡ አስረድተው፣ " ይህ ማለት አንድ ሰው በ4 ወራት ከ2,000 ብር በላይ ላልተፈለገ ወጪ ተዳርጓል ማለት ነው " ሲሉ የችግሩን አስከፊነት ገልጸዋል።

በተለይ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን የሚሰሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ችግሩ የከፋ አሉታዊ የሆነ ተፅዕኖ እንዳሳደረባቸው፣ የውሃ አገልግሎትም እንደተቋረጠ አክለው ገልጸዋል።

በወረዳው መብራት ከተቋረጠ ከሶስት ወራት በላይ እንዳስቆጠረ ባሳለፍነው ወር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ከዚያ ወዲህ አንድም ቀን መብራት እንዳልበራ ተናግረው፣ ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል።

የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው  ፤ በከተማው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ከተቋረጠ አንድ ሳምንት በማስቆጠሩ እየተቸገሩ መሆኑን ተናግረዋል።

አገልግሎቱ ከዚህ ቀደምም ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ እንደነበር አስታውሰው፣ አሁንም መጥቶ ትንሽ ከቆዬ በኋላ ተመልሶ በመጥፋቱ የሚመለከታቸው አካላት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ አሳስበዋል።

አንድ የአሶሳ ነዋሪ የሆነ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፥ " የአሶሳ ማብራት ይኸው አሁንም መፍትሄ አላገኘም። በመሃል ለትንሽ ቀናት መጥቶ መልሶ ጠፍቷል " ብለዋል።

የሚመለከታቸው አካላት በዚህ ጉዳይ ላይ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኞች ያልሆኑ ሲሆን፣ በቀጣይ ፈቃደኞች ከሆኑ ምላሻቸውን የምናቀርብ ይሆናል።

ከዚህ ቀደም ስለወንበራ ወረዳ ቅሬታ የጠየቅነው የኤሌክትሪክ አገልግሎት የደብረ ዘይት ማዕከል፣ "እንደ ወንበራ ደብረ ዘይት ቅድሚያ የቡለን ማዕከል ራሱን የቻለ አለ። እሱ ከበራ በኋላ ነው እኛ ማብራት የምንችለው" ብሎ ነበር።

ችግሩን ለመቅረፍም፣ " ከወረዳው መንግስት ጋር እየተየጋገርን ነው፤ በቅርቡ እንሰራዋለን " ነበር ያለው።

በወቅቱ ስለጉዳዩ የጠየቅነው የክልሉ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበኩሉ፣ "የተቋረጠው ኤሌክትሪክ ኃይል እንዲቀጠል እየተከታተልን ነው" ማለቱ ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ አሶሳ ከተማና ወምበራ ወረዳ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በመቋረጡ ችግር ላይ መውደቃቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ። በተለይም በወምበራ ወረዳ አገልግሎቱ ከተቋረጠ አራት ወራት እንዳስቆጠረ ገልጸው፣ እስካሁን (ይህ ዘገባ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ) መፍትሄ እንዳልተገኙ ተናግረዋል። ሞባይል በጀነሬተር ቻርጅ ለማድረግ እንኳ በየቀኑ 20 ብር እንደሚያወጡ…
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ

በቤንሻንጉል ጉሙዝ የተለያዩ ቦታዎች ኤሌክትሪክ እንደተቋረጠ፤ በተለይም በአንዳንዶቹ አካባቢዎች ከተቋረጠ ከ3 ወራት በላይ እንዳስቆጠረ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቤት ማለታቸው ይታወሳል፡፡

አሁንም ድረስ ችግሩ መቀጠሉን መብራት እንደሌለ ክረምቱን እጅግ እንዳከበደባቸው፣ ህይወታቸውንም ማመሰቃቀሉን እንደቀጠለ ተናግረዋል።

እኛም የወገኖቻችንን ጥያቄ ይዘን ' ይመለከታቸዋል ' የሚባሉትን አነጋግረናል።

ለምን ኃይል ተቋረጠ ? ችግሩን ለመፍታት ምን እየተሰራ ነው ?

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮሚኒኬሽን " እኛ እኮ ኃይል ማቅረብ ነው ከዚያ የዘለለ የስርጭት ሥራ አንሰራም፡፡ ስለዚህም የሥርጭት ሥራን የሚሰሩትን ብትጠይቁ ነው የተሻለ የሚሆነው " አለን።

እሺ ብለን፣  የኤሌክትሪክ አገልግሎት ኮሚኒኬሽን ጠየቅን ፥ " እኛ አይደለንም የምንሰራው፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ነው፤ ከተማ ውስጥ አይደለም የተቋረጠው የከፍተኛ መስመር ላይ ነው " ሲል መለሰልን።

" ከፍተኛ መስመር ላይ ጉዳት ደርሶ ኃይል እየደረሰን አይደለም ለኛም፡፡ ኃይል ከእነርሱ ነው የምንገዛው። ስለዚህ እነርሱ ኃይል እያደረሱን አይደለም፡፡ ችግሩ ምን እንደሆነ እነርሱ ናቸው ባለቤቶቹ የሚያውቁት " ሲል አክለልን።

እሺ የኤሌክትሪክ ኃይልን እንጠይቅ ብለን ደወልን " ከኛ ጋር የሚገናኝ ነገር ስለሌለው ነው " ተባልን።

ቆይ ታዲያ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥን ማንን ነው የሚመለከተው ? የት ብለን እንጠይቅ አልን ፥  " ኃይል በተለያዬ ምክንያት ሊቆራረጥ ይችላል፡፡ መቋረጥ ሁሉ ወደ እኛ አይመጣም ። አጠቃላይ ክልሉ ላይ አይደለም ችግሩ አለ ያላችሁት የተወሰኑ አካባቢዎች ላይ ነው፡፡ የተወሰኑ አካባቢዎች ደግሞ ችግር ካለ ከስርጭት ሊሆን እንደሚችል ነው እኛ የምንገምተው። " ብሎናል።

እስከዛሬ ድረስ ችግሩን አልዳሰሳችሁትም ? ወንበራ ላይ ለምሳሌ አራት ወራት ሊሆነው ነው፤ የመተከል ደግሞ አመታት አስቆጥሯል፤ ብለን ጠየቅን ፥ " መተከል ወደ 2 ዓመት ይስለኛል፡፡ እርሱ ላይ እርግጠኛ አይደለሁም " ብሏል።

አጣርታችሁ ምላሽ እስከምትሰጡን እንጠብቅ ? ስንል ላቀረብነው ጥያቄ " ይሄ እኛን የሚመለከት ስላልሆነ ምንም የተለዬ የማጣራው ነገር የለም " የሚል ምላሽ ተሰጥቶናል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈#የነዋሪዎችድምጽ

" ተስፋ ቆርጠናል " - ቆጣቢዎች

በአዲስ አበባ የነዋሪውን የቤት ችግር ለመፍታት በሚል መንግስት የጋራ መኖሪያ ቤት ወይም የኮንዶሚንየም ቤት ምዝገባን በ1997 እና 2005 ያደረገ ሲሆን እጣው የዘገየባቸው ነዋሪዎች " ተስፋ ቆርጠናል " ሲሉ ገለጹ።

ነዋሪዎቹ ቃላቸውን የሰጡት #ለአሃዱ ነው።

ከተመዘገቡ 19 እና 11 ዓመታት እንዳለፋቸው የተናገሩት ተመዝጋቢዎች " ከወደ መንግስትም ምንም አይነት መረጃ እየወጣ አለመሆኑ ጥያቄ ፈጥሮብናል " ብለዋል።

" የሚመለከተው አካል በአፋጣኝ ምላሽ ይስጠን " የሚሉት ተመዝጋቢዎቹ " በመንግስት በኩል ቅድሚያ እየተሰጣቸው ያሉ ነገሮች ተመዝጋቢዎቹ ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ ከግንዛቤ ያስገባ አይደለም " ሲሉ ተናግረዋን።

ለአብነትም ከወራት በፊት የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን 3 ሺህ የሚሆኑ ቤቶችን በመግንባት ለሽያጭ ማቅረቡን በማስታወስ " ለምን እንዲህ ይደረጋል ? የሚል ጥያቄ ብናቀርብም ሰሚ አልነበረም " ብለዋል።

የአዲስ አበባ ቤቶች ኮርፖሬሽን ምን አለ ?

ኮርፖሬሽኑ " አትቆጥቡ ያለ አካል የለም ከመንግስት በሚቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ግንባታዎች እየተካሄዱ ነው " ብሏል።

" ተመዝጋቢዎች በትዕግስት እንዲጠብቁ " ሲልም ጠይቋል።

ለኮንዶሚኒየም ቤት ፈላጊ ተመዝጋቢዎች የት ቦታ ምን እየተሰራ እንደሆነ መግለጽ ከተቻለ በሚል ለቀረበው ጥያቄ ፤ " እየተሰራ መሆኑን መግለጽ በቂ ነው " የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለኮንዶሚንየም ተመዝጋቢዎች ምን ስራዎችን እየከወነ ይገኛል ? በሚል ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት ጥያቄ ቢቀርብም ጽ/ቤቱ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም።

ሁለት አስርት ዓመታትን ሊደፍን ጥቂት ወራት የቀረው ተመዝጋቢ ለሌሎች ዓመታት በትዕግስት እንዲጠብቅ ተገልጾለታል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የአሃዱ ነው።

#AddisAbaba #AhaduRadioFM

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ

በመቐለ የተለያዩ ክፍሎች ጨምሮ በሌሎች የትግራይ ከተሞች ተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ እያጋጠመ ነው።

ይህን ተከትሎ ነዋሪዎች ለከፋ ችግር ተጋልጠለዋል።

የመቐለ የተወሰነ ክፍል የኤሌክትሪክ ሐይል ከተቋረጠ ከ40 ቀናት በላይ ተቆጥረዋል።

ትላልቅ ኢንዳስትሪዎች ጨምሮ በኃይል እጦትና መቋረጥ እየተፈተኑ ነው።

በተለይ በተያዘው የክረምት ወቅት በስፋት እየታየ ያለው እና መቐለ ከተማ ጨምሮ በርካታ የትግራይ ክልል አካባቢዎች የሚሸፍነው ተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ ሐይል መቋረጥ በነዋሪዎች ዘንድ የከፋ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ፈጥሮ ይገኛል።

በመቐለ በተለምዶ ሰብዓ ካሬ ተብሎ በሚታወቅ አካባቢ የኤሌክትሪክ ሐይል አገልግሎት ከተቋረጠ ከ40 ቀናት በላይ ሆኗል።

ከመቐለ ውጪም ቢሆን በሀገረሰላም እና ወጀራት አካባቢዎች ከወር በላይ ለሚሆን ግዜ የኤሌክትሪክ ኃይል ተስተጓጉሎባቸው ቆይቷል።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሰሜን ሪጅን የትራንስሚሽንና ሳብስቴሽን ኦፕሬሽን ዳይሬክተር አቶ ሮቤል ገብረእግዚአብሔር፥ " የኃይል መቋረጡ ዋነኛ ምክንያት በኃይል ማስተላለፊያ ላይ የደረሰ ጉዳት ነው " ብለዋል።

ችግሩ በግዚያዊነት እስከ መጪው ነሐሴ 5 ቀን 2016 ድረስ ለመፍታት ይሰራል። በዘላቂነት ደግሞ ተጨማሪ ጥረቶች ይደረጋሉ ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የዶቼ ቨለ ሬድዮ ነው።

#DWAmharic

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ

በአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ነዋሪዎች እጅግ እያማረረ ነው።

በርካቶች የኃይል የመቆራረጡ ስራቸውን በአግባቡ እንዳይሰሩ ፈተና ሆኖባቸዋል።

" የሚሰሩት የመንገድ ስራዎች እየተጠናቀቂ ሲመጡ የኃይል የመቋራረጥ ነገሩ ይቃለለል ብለን ብናስብም አሁንም ያው ነው " ብለዋል ቃላቸውን የሰጡን ነዋሪዎች።

በተለያዩ ቦታዎች ላይም የኃይል መቆራረጡ ንብረት እስከማቃጠል የደረሰ ጭምር ነው።

ከኤሌክትሪክ ኃይል ችግር ባለፈ ውሃም ፈተና እንደሆነ መቀጠሉን ጠቁመዋል።

በተለይ ብዙ ነዋሪዎች ባሉባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ውሃ አለመኖር የሚፈጥረው ችግር ይታወቃል።

" በየጊዜው ያለው ከፍተኛ የሆነ የውሃ ችግር ተደጋግሞ ቢነሳም ዛሬም ድረስ ይኸው ጥያቄ ቀጥሏል ፤ ዘላቂ መፍትሄ መቼ እንደሚመጣ ግራ ነው የገባን !! " ብለዋል።

#AddisAbaba #TikvahFamily

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈#የነዋሪዎችድምጽ

ሰሞኑን " ዶላር በጣም ጨምሯል " በሚል የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ የሚገኙ የንግዱ አካላት እጅግ እያማረሯቸዉ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቤት ብለዋል።

" አሁን ላይ ነጋዴው እቃውን በሌሎች ነጋዴዎች ሱቅና በራሱ መጋዘን ሲያስቀምጥ አይናችን እያዬ እቃዉ የለም በሚል ዋጋ ሊጨምር ሲሞክር ማየት ያማል " ሲሉ ገልጸዋል።

ነዋሪዎቹ ፥ " እስከ 1,080 ብር የነበረዉ ዘይት 1380 ብር ሲገባ ዶላር ነው " አሉን " እሺ የቲማቲምና ሽንኩርቱስ ዋጋ መናር ከየት መጣ ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

1 ኪሎ ሽንኩርት ከ40 ብር ተነስቶ 90 ብር ቲማቲም 20 ብር የነበረው 40 እና 45 መግባቱን ጤፍም በኪሎ ከ10 ብር በላይ እንደጨመረ ጠቁመዋል።

ስሚንቶ ላለፉት ወራት ጥሩ ቢሆንም አሁን ላይ " የለም " እየተባለ እንደሆነ ገልጸዋል።

የነዳጅ ጉዳይ ግን በፊትም አንስቶ ፈተና ነበር አሁን ብሶበት ራስ ምታት ሆኖ ቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።

ሀዋሳ ላይ የገበያውን ሁኔታ ስርአት ለማስያዝ የተቋቋመ ግብረሀይል መኖሩን በመስማታችን  የነዋሪዎችን ቅሬታ ይዘን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዡ ኢንስፔክተር መልካሙ አየለን አነጋግረናል።

እሳቸውም ፥  " አሁን ላይ እቃ በሚደብቁ እና አላግባብ ዋጋ በሚጨምሩ ህገወጥ ነጋዴዎች ላይ ግብረሀይሉ  ጠንካራ እርምጃ እየወሰደ ነው " ብለዋል

ግብረሀይሉ  በሰራዉ ስራ ሁለት ማደያዎች እና 62 የሸቀጣሸቀጥ ሱቆች የምግብ ግብአትና የብረታብረት አቅራቢዎች በ8ቱ ክፍለ ከተሞች  መታሸጋቸዉንና እቃዎችም ተወርሰዉ ህገወጦቹ ግለሰቦች  በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ገልጸዋል።

ክትትሉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሚገልጹት አዛዡ ማህበረሰቡም ህገወጦችን በመጠቆም የፖሊስን ስራ እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ አሶሳ ከተማና ወምበራ ወረዳ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በመቋረጡ ችግር ላይ መውደቃቸውን ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ። በተለይም በወምበራ ወረዳ አገልግሎቱ ከተቋረጠ አራት ወራት እንዳስቆጠረ ገልጸው፣ እስካሁን (ይህ ዘገባ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ድረስ) መፍትሄ እንዳልተገኙ ተናግረዋል። ሞባይል በጀነሬተር ቻርጅ ለማድረግ እንኳ በየቀኑ 20 ብር እንደሚያወጡ…
🔈 #የነዋሪዎችድምጽ

" አሶሳ ላይ ያለው የመብራት ጉዳይ አሁንም መፍትሄ ሊያገኝ አልቻለም። በየጊዜው እየተቆራረጠ ነው።

ማህበረሰቡ እጅጉን ተቸግሮ ነው ያለው።

በተለይም ዉሃ ፣ ወፍጮ እንዲሁም ከመብራት ጋር የተያያዘ የስራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች በጣም ችግር ላይ ናቸው። ምንም ስራ ሳይሰሩ የቤት ኪራይ እየከፈሉ ነው።

የመብራት አለምኖር በአጠቃላይ የከተማውን የንግድ እንቅስቃሴን አቀዛቅዞዋል። በጄነሬተር ሞባይል ቻርጅ ለማድረግ 40 ብር  ነው። ኑሮን የበለጠ ከባድ እያደረገብን ነው።

በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ቦታ ብልሽት አጋጥሞታል ይባላል። ጠንካራን እና ዘላቂ የሆነ መፍትሄ እንፈልጋለን። "

#TikvahEthiopiaFamilyAssosa

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM