TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ለሊት በዚያው በተኙበት ነው የገደሏቸው..."

በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ቦርደዴ ወረዳ ጉምቢ በተባለ ቦታ በተፈጸመ ጥቃት በትንሹ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን #የቦርደዴ ጤና ጣቢያ ባልደረባ ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል። የኦሮሚያ ኮምዩንኬሽን ቢሮ ጥቃቱ መፈጸሙን በፌስቡክ ገጹ ባወጣው አጭር መረጃ አረጋግጧል።

#የአፋር እና #የኦሮሚያ ክልሎች በሚዋሰኑበት አካባቢ በምትገኘው ጉምቢ በተፈጸመው ጥቃት ከሞቱ ሰዎች መካከል አንዲት እንስት እንደሚገኙበት እና ሌሎች ሁለት ሰዎች መቁሰላቸውን የቦርደዴ ጤና ጣቢያ ባልደረባ የሆኑስት ሲስተር ሐይማኖት ተስፋዬ አስረድተዋል። ሲስተር ሐይማኖት «ለሊት በዚያው በተኙበት ነው የገደሏቸው። ሰባት ሰው ሞቷል። አሁን ሰባት እሬሳ አለ። እየተፈለጉም ያሉ አሉ» ብለዋል።

የኦሮሚያ ክልል የኮምዩንኬሽን ቢሮ ከአንድ ሰዓት ገደማ በፊት በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መረጃ በቦርደዴ ወረዳ በተፈጸመው ጥቃት ሰባት ሰዎች መገደላቸውን ገልጿል።

ሲስተር ሐይማኖት ከሞቱት ሰባት ሰዎች ባሻገር ሌሎች ሁለት ሴቶች መቁሰላቸውን ተናግረዋል። «ሁለት የቆሰሉ ሴቶች ነበሩ። ወደ አሰቦት ሆስፒታል ልከናቸዋል» ብለዋል።

ሲስተር ሐይማኖት እንዳሉት ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ የገቡበት ያልታወቀ ሰዎች በመኖራቸው #ፍለጋ እየተካሔደ ይገኛል። ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ ከአዲስ አበባ ወደ ሐረር እና ድሬዳዋ የሚወስደው መንገድ ለረዥም ሰዓታት ተዘግቷል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ከረጅም ርቀት በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ 2 ህፃናት ልጆቿን ያጣች እናት አለች " - ዶ/ር ሁሴን አደም የህወሓት ኃይሎች በአፋር ያሎ በኩል በሰነዘሩት የከባድ መሳሪያ ጥቃት በአካባቢው ንፁሃን ነዋሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱንና በርካቶች በያሎ አካባቢ በሚገኘው የህክምና ጣቢያ ህክምና እየተከታተሉ መሆኑ ተገልጿል። ከባድ ጉዳት ከደረሰባቸውም ውስጥ ወደ ዱብቲ ጠቅላላ ሆስፒታል መጥተው ህክምና የተከታተሉ…
" የህፃናት ህይወት ተቀጥፏል " - UNICEF

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ህፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) ፤" አሁንም በድጋሚ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ያገረሸው ግጭት የህፃናትን ህይወት ቀጥፏል " ብሏል።

ባለፉት ጥቂት ቀናት በትግራይ ክልል አዋሳኝ በሆነ #የአፋር_ክልል መንደር የተፈፀመ የከባድ መሳሪያ ጥቃት ህፃናትን ገድሏል ፤ በርካቶችንም ቁስለኛ አድርጓል ሲል ድርጅቱ አሳውቋል።

UNICEF በኢትዮጵያ ላሉ ህፃናትና ለወደፊት ህይወታቸው ሲባል ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆም ሁሉም ወገኖች እንዲስማሙ ተማፅኗል።

UNICEF በመግለጫው ላይ ጥቃት የደረሰበትን የአፋር ክልል መንደር በግልፅ ባይሳውቅም ከቀናት በፊት የህወሓት ኃይሎች በአፋር " ያሎ " በኩል በሰነዘሩት የከባድ መሳሪያ ጥቃት በአካባቢው ንፁሃን ነዋሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱንና በርካቶች በያሎ አካባቢ በሚገኘው የህክምና ጣቢያ ህክምና እየተከታተሉ መሆኑ መገለፁ አይዘነጋም።

በጦርነቱ በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዱ ዜጎች ለተሻለ ህክምና ዱብቲ ሆስፒታሉ እንደገቡና ሆስፒታል ከገቡት ውስጥ 2 ህፃናት ልጆቿን ከረጅም ርቀት በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ የተገደሉባት እናት እንደምትገኝ መገለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia