TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Telegram

ባለፉት ቀናት ከ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ ሲገደብ የነበረው ቴሌግራም ዛሬ የ12ኛ ክፍል ፈተና መጠናቀቁን ተከትሎ ሙሉ አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጓል።

የ " ቴሌግራም " መገደብ ከፈተናው ጋር በተያያዘ የሀሰተኛ መረጃዎችን ስርጭት በመግታትና ተፈታኝ ተማሪዎች እና ወላጆች #እንዳይረበሹ በማድረግ በኩል ትልቅ የሆነ አስተዋጽኦ እንደነበረው መመልከት ተችሏል።

ባለፉት ዓመታት በነበሩ የብሄራዊ ፈተናዎች ላይ ከየትኛውም የማህበራዊ ሚዲያዎች በበለጠ በ " ቴሌግራም " በኩል ነበር የፈተና ወረቀቶች ከፈተና ቀን ቀደም ብሎ ሲሰራጭ የነበረው።

በአሁኑ የ2014 ዓ/ም ብሄራዊ ፈተና ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርሲቲ አስገብቶ ማስፈተኑ የፈተና ስርቆትን እና ቀድሞ ማሰራጨትን መከላከል ያስቻለ ሲሆን በአንዳንድ ተቋማት ስልክ ይዘው የገቡ ተማሪዎች ከፈተና ክፍል ሆነው የፈተና ወረቀት እያነሱ በቴሌግራም ግሩፖች እና ቻናሎች ላይ ሲያሰራጩ ነበር።

ነገር ግን በአብዛኛው ተማሪ ስልክ ይዞ እንዳይገባ በመደረጉ እና " ቴሌግራም " ም ሲገደብ ስለነበር ተፅእኖውን መቋቋም እንደተቻለ ይታመናል።

በቀጣዩ የ2015 ዓ/ም ብሄራዊ ፈተና ላይ መሰል ክፍተቶች እንዳይኖሩ ለማድረግ ከአሁኑ ፈተና ትምህርት በመውሰድ አስፈላጊ ማስተካከያ ማድረግ ይገባል።

@tikvahethiopia