TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ዓለምአቀፍ #ሀንጋሪ

ሀንጋሪያዊያን የመንግስት ሚዲያን ' ፕሮፓጋንዳ ' ለመቃወም ሰልፍ መውጣታቸው ተሰማ።

በሀንጋሪ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በአደባባይ በመውጣት በመንግስት ስር በሚተዳደረው የ ' MTVA ' ቴሌቪዥን ጣቢያ ዋና መሥሪያ ቤት አከባቢ በመገኘት መንግስት ቴሌቪዥኑን ለፕሮፓጋንዳ መጠቀሙን እንዲያቆም እና ጣቢያው ገለልተኛ የህዝብ ሚዲያ እንዲሆን ጠይቀዋል።

የተቃውሞ ሰልፉን ያስተባበረው ' TISZA ' የተሰኘው የተቃዋሚ ፓርቲ ሲሆን በሰልፉ ላይ የተገኙ ተቃዋሚዎች " ፕሮፓጋንዳ ይቁም !! " በሚል የሀገሪቱን ባንዲራ በመያዝ ድምጻቸውን አሰምተዋል።

የተቃዋሚ ፖርቲው መሪ የሆኑት ፒተር ማጂር ለተቃውሞ ለወጣው ተሳታፊ ንግግር ሲያደርጉ፥ " ክፋት፣ ውሸት፣ ፕሮፓጋንዳን ከበቂ በላይ ሰምተናል፤ ትዕግሥታችን አብቅቷል፣ አሁን በሀንጋሪ ያለው የመንግስት ሚዲያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተዋረድንበት ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ጣቢያው ሰልፉን ያለምንም መቆራረጥ እንዲያስተላልፈውም ጠይቀዋል።

የሀገሪቱ ገዢ ፖርቲ መሪ የሆኑት ቪክቶር ኦርባን መንግስትን የሚደግፉ ሚዲያዎችን ለማብዛት ከመንግስት ጋር ቅርበት ባላቸው #ባለሀብቶች ሚዲያዎች እንዲገዙ አድርገዋል በሚል ቅሬታ ይቀርብባቸዋል።

ድንበር የለሽ የሪፖርተሮች ቡድን ግምት እንደሚያሳየው 80 በመቶ የሚሆነው የሃንጋሪ የሚዲያ ገበያ በዚሁ መንገድ በገዢው መንግስት ቁጥጥር ሥር ወድቋል።

በዚህ የተነሳ እ.ኤ.አ በ2021 ቡድኑ ቪክቶር ኦርባንን " ሚዲያ አዳኝ " ዝርዝር ውስጥ ያስቀመጠው ሲሆን ይህንን ስያሜ የተቀበለ የመጀመሪያው የአውሮፓ ህብረት መሪ አድርጎታል።

ባላዝ ቶምፔ የተባሉ አንድ ተቃዋሚ በሰልፉ ላይ ለመሳተፍ ለብዙ ሰዓታት መጓዛቸውን ጠቅሰው ጣቢያውን " የውሸት ፋብሪካ " ሲሉ አጥላልተውታል።

አግነስ ጌራ የተባሉ ጡረታ የወጡ መምህር በበኩላቸው ፥ " የሚዲያ ሥርዓቱ በዚህ መንገድ መሆኑ ህዝቡ ከአንድ ወገን ብቻ ያለውን እንዲሰማ እና ስለሌላኛው ወገን እንኳን በማያውቅበት መንገድ መስራቱ በጣም ከባድ እና አሳዛኝ ነው" ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከሮይተርስ እና ኤፒ ማሰስባሰቡን ይገልጻል።

@tikvahethmagazine @tikvahethiopia