TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አቶ ሌንጮ ለታ⬇️

#ኦነግ ትጥቅ አልፈታም በማለት ለተጀመረው ሰላማዊ የፖለቲካ ሂደት እንቅፋት መሆን የለበትም መንግስትም በጉዳዩ ላይ ግልፅ መረጃ ማቅረብ አለበት ሲሉ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ሊቀመንበር አቶ ሌንጮ ለታ ተናገሩ።

አዲስ አበባ በሚገኘው አሐዱ በተባለው ሬድዮ ከአቶ #በቀለ_ገርባ ጋር እንግዳ ሆነው የቀረቡት አቶ #ሌንጮ_ለታ በሀገሪቱ የተጀመረው ለውጥ ሁሉን አካታችና የማይቀለበስ እንዲሆን ሁሉም አካል በሀላፊነት መንቀሳቀስ አለበት ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ከኦነግ ጋር የደረሰበትን ስምምነት ይፋ ማድረግ አለበት ያሉት አቶ ሌንጮ ለታ የኦነግ መሪ አቶ ዳውድ ኢብሳ ከምን ተነስተው ትጥቅ አንፈታም እንዳሉ መረዳት ይቸግረኛል ብለዋል።" ወጣቶች ባዶ እጃቸውን ወጥተው ታንክ ፊት ቆመው ሲታገሉ የኦነግ ሰራዊት የት ነበረ? አሁንስ ትጥቅ አልፈታም ማለት ማንን ለመውጋት ነው?" ሲሉ ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሶሳ🔝በቤኒሻንጉል ጉመዝ ክልል በአሶሳ ከተማ በክልሉ መስተዳድር ም/ቤት ትላንት በቀን 7/03/2011 ዓ/ም አክቲቪስት #ጃዋር_መሀመድና አቶ #በቀለ_ገርባ ክክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ አሻዲል ሀስን፣ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ከአሶሳ ከተማ እና አካባቢዋ ማሀበረስብ ጋር በምዕራብ ኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉመዝ ክልል ድንበር አካበቢዎች በሚከሰቱ #ግጭቶች ዙሪያ መፍትሄ በሚያገኘበት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በፍቅር ልቃችሁ ተገኙ! በመደማመጥ ልቃችሁ ተገኙ! ሰውን በመጥላት ሳይሆን ሰውን በመውደድ በልጣችሁ ተገኙ።" ኦቦ #በቀለ_ገርባ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በምዕራብ ወለጋ ዞን የኦነግ አባላት ህዝቡን #እየተቀላቀሉ ሲሆን፣ በዞኑ፣ መነ ሲቡ ወረዳ አቀባበል እየተደረገላቸው ነው፡፡ በቅርቡ ከተቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ውስጥ ወደ ምዕራብ የተላኩት የአባገዳዎች ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ #በየነ_ሰንበቶና አቶ #በቀለ_ገርባ ከህዝቡ ጋር በመሆን ለኦነግ አባላት አቀባበል እያደረጉላቸው ነው፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በምዕራብ ኦሮሚያ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የጦር መሪ የሆነው ኩምሳ ዲሪባ ወይም መሮ፤ በምዕራቡ ክፍል የሚገኘው የኦነግ ጦር የትጥቅ ትግል ማድረጉን እንደሚቀጥል ተናገረ።

መንግሥትን እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን ለማስታረቅ ተዋቅሮ የነበረው ኮሚቴ ትናንት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን ባቀረበበት መድረክ ላይ የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከአሁን በኋላ ኦነግ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ የጦር ኃይል አይኖረውም ማለታቸውን ተከትሎ ነው የጦሩ መሪ ይህን የተናገረው።በምዕራብ ኦሮሚያ የጦር መሪ የሆነው ኩምሳ ዲሪባ ወይም መሮ፤ ''የተለወጠ ነገር የለም'' በማለት ከኦነግ ሊቀ መንበር በተለየ መልኩ የኦነግ ጦር የትጥቅ ትግል ማድረጉን እንደሚቀጥል ለቢቢሲ ተናግሯል።

መሮ መከላከያው፣ ፖሊስ እና የደህንነት አካሉ ሙሉ በሙሉ የፓርቲ ወገንተኝነቱን አቁሞ የሕዝብ ወገንተኝነቱን እስካላረጋገጠ ድረስ የመንግሥትን ጥሪ አንቀበልም ብሏል። ''እኛ ለፓርቲ ወግኖ ህዝብን የሚጎዳ የመከላከያ አካል መሆን አንሻም'' ሲል ከዚህ በፊት ከመንግሥት ጋር በተደረሰው ስምምነት የግንባሩ ታጣቂዎች ከመንግሥት የጸጥታና የመከላከያ ኃይል ጋር ለማካተት የቀረበውን ሃሳብ መሮ ውድቅ አድርጎታል።

ጨምሮም ''ለጊዜያዊ ጥቅም ተብሎ በንግግር ተሸፋፍኖ የሚያልፍ ነገር አያዛልቅም። ነገ እሳት መነሳቱ አይቀርም። ዘላቂ መፍትሄ በሚሰጡ ምክክሮች ላይ ለመወያየት ግን ዝግጁ ነን'' በማለት ለድርድር ዝግጁ መሆኑን ጠቁሟል።መንግሥትን እና ኦነግን ለማስታረቅ ተዋቅሮ የነበረው ኮሚቴም ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት መሳሪያ አንገበው ጫካ ገብተው የነበሩ የኦነግ ወታደሮች በሰላማዊ መንገድ ትግላቸውን እንዲቀጥሉ ወይም ወደሚዘጋጅላቸው ስፍራ ለስልጠና እንዲገቡ ጥረት ሲያደርግ እንደቆየ አስታውሷል።

ኮሚቴው የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በተገኙበት ነው ሪፖርቱን ያቀረበው። ሪፖርቱ በቀረበበት ወቅት የኦነግ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኦነግ ከአሁን በኋላ ጦር አንግቦ የሚንቀሳቀስ ሠራዊት አይኖረውም፤ መንግሥት ሕግ ለማስከበር የሚወስደውን እርምጃም እንደግፋለን ብለዋል።

የአስታራቂ ኮሚቴውን ሪፖርት ያቀረቡት አቶ #በቀለ_ገርባ ሲሆኑ ባቀረቡት ሪፖርት ውስጥ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አንስተዋል። ኦነግ ከአሁን በኋላ #ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ጦር ስለማይኖረው ኮሚቴው የተቋቋመበትን ዓላማ ማሳካቱን ጠቅሰው፤ ኮሚቴው በኦነግ እና በመንግሥት መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ምክንያት ታስረው የነበሩ ሰዎች ከእስር እንዲለቀቁ ጠይቋል። በተጨማሪውም ኮሚቴው ኦነግ በሰላማዊ መንገድ ፖለቲካዊ ትግሉን ለመቀጠል በሚያደርገው እንቅስቃሴ የመንግሥት ድጋፍ እንዳይለይ እና የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ወደተዘጋጀላቸው ስፍራ የገቡ የኦነግ ጦር አባላት ቃል የተገባላቸው ሁሉ ተፈጻሚነት እንዲኖረው ኮሚቴው ጠይቋል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦቦ #በቀለ_ገርባ ~~ #መቐለ_ዩኒቨርሲቲ

የፌደራል ሥርዓት አወቃቀር #ለቋንቋዎች እድገት መሠረት ከመጣሉ ባለፈ ኅብረተሰቡም ባደገበት ቋንቋ የመንግሥት አገልግሎት ለማግኘት እንደሚያስችለው የቋንቋ ምሁሩና ፖለቲከኛው አቶ #በቀለ_ገርባ ገለጹ። "የኢዮጵያ ቋንቋዎችና ጠቀሜታዎች" በሚል የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ያዘጋጀው መድረክ ዛሬ ተካሂዷል።

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/Mekelle-07-25
"ምን አይነት ሀገር ነው ልንመሰርት የምንፈልገው? እዚህ ላይ እስካሁን መግባባት #ባይኖርም መግባባት ግን ይገባናል ግድ ነው፤ እኛም ያንኑ ነው መልሰን የምንጠይቀው፤ ዜጎች ቋንቋቸውን፣ ባህላቸውን፣ ማንነታቸውን ጠብቀው በአንድነት በእኩልነት የሚኖሩባትን #ዴሞክራሲያዊ ሀገር መገንባት እንፈልጋለን" አቶ #በቀለ_ገርባ

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማዕከላዊ እስር ቤት⬆️

"ዛሬ ጠዋት ጀምሮ እስከ ረፋድ ድረስ በርካታ ሰዎች ማዕከላዊ እስር ቤትን እየጎበኙ የሚገኝ ሲሆን ከነዚህም መካከል አቶ #ጃዋር_መሀመድ የተገኙ ሲሆን ኦቦ #በቀለ_ገርባ ለOMN ሚዲያ ሠዎች እና በቦታው ለተገኙ ጎብኚዎች ስለ ቦታውና በዚያ ስላሳለፉአቸው አስከፊ ጊዜያት ገለፃ ሲያደርጉና ሲያስጎበኙ ነበር።"

📸በርካታ የTIKVAH-ETH የቤተሰብ አባላት ማዕከላዊን በመጎብኘት የሚያዩትን ነገር በፎቶ እያስቀሩ እየላኩን ይገኛሉ!


Via #Fasil/TIKVAH-ETH/

@tsegabwolde @tikvahethiopia