TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"የፌደራል ስርዓት ጉዳይ ለድርድር አይቀርብም" --- ኦዲፒ
.
.
በፌደራል ስርዓቱ ላይ ከማንም ጋር #ለድርድር እንደማይቀመጥ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) አስታወቀ። ፓርቲው በትናነትናው እለት ባወጣው መግለጫው፥ ኦዲፒ በአጀንዳነት ይዞ ከሚታገልባቸው ጉዳዮች ውስጥ ዋነኛው የፌደራል ስርዓቱ ነው ብሏል።

ለፌደራል ስርዓቱ መምጣት ከፍተኛ ዋጋ ተከፍሎበታል ያለው ፓርቲው፥ ስርዓቱ ለድርድር የማይቀርብ መሆኑንም አስታውቋል በመግለጫው። በፌደራል ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ #የሀሰት_ፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑንም ኦዲፒ በመግለጫው አስታውቋል።

በአሁኑ ወቅትም በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የፌደራል ስርዓቱን ሊያፈርስ እንደሆነ እንዲሁም ህብረተሰቡ በፌደራል ስርዓት ላይ ያለውን እምነት እና ተስፋ እንዲቀንስ ከፍተኛ የሆነ የሀሰት ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑንም ገልጿል።

የሀሰት ዘመቻው ሁለት ዓላማ ያለው ነው ያለው ኦዲፒ፥ ከእነዚህም አንደኛው የኢትዮጵያ ብሄሮችና ብሄረሰቦች አሁን ያለውን ለውጥ በጥርጣሬ እንደሚመለከቱ ማድረግ ነው ብሏል።

በዚህም የራሳቸውን ባህል፣ ቋንቋ፣ ማንነት እና ታሪክ ማሳደግን በትግል እና በመስዋእትነት ያገኙ ብሄሮችና ብሄረሰቦች የፌደራል ስርዓቱ ሊፈርስ ነው በሚል በጥርጣሬ ተቃውሞ እንዲያስነሱ ታስቦ የሚደረግ ሴራ መሆኑንም ገልጿል።

በተጨማሪም የኦሮሞን ህዝብ “ተጨማሪ መብት ማግኘትህ ቀርቶ ከዚህ ቀደም የተገኘውን መብት ልታጣ ነው” በሚል በማደናበር እርስ በርስ ለማጋጨት ያለመ መሆኑንም አስታውቋል።

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄን ለመመለስ እንደሚሰራ በመግለጽ፥ የአዲስ አበባ እና የአፋን ኦሮሞ ጉዳይም እየተሰራበት ያለ መሆኑን ገልጿል።

ከፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጥያቄዎች ላይም ትኩረት በመስጠት እየሰራበት መሆኑን ፓርቲው በመግለጫው አስታውቋል።

ኦዲፒ ለተጨማሪ ድል ይሰራል እንጂ ከዚህ ቀደም የተገኙ ድሎችን አያከሽፍም ያለው ፓርቲው፥ በፌደራል ስርዓት ጉዳይ ላይ ከማንም ጋር ለድርድር እንደማይቀመጥም ገልጿል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞የካቲት 12/2011 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ ሰማዕታት ቀን 82ኛ ዓመት የመታሰቢያ ስነ ስርዓት በዛሬው እለት ተካሂዷል። መታሰቢያ ስነ ስርዓቱ በተለይ 6 ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሰማእታት አደባባይ ከማለዳው ጀምሮ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ነው የተካሄደው።
.
.
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጣልያኑ ትጥቅ አምራች ኩባንያ ኤሬአ ጋር የነበረውን ስምምነት ቀይሮ ከእንግሊዙ አምብሮ ኩባንያ ጋር የአራት አመት የትጥቅ ልብስ ማቅረብ ስምምነት ተፈራርሟል።
.
.
በአማራ ክልል የተፈናቀሉ ወገኖችን ለማቋቋም የክልሉ መንግስት ያደረገውን ጥሪ ተከትሎ #ጥረት_ኮርፖሬሽን የ10 ሚሊዮን ብር የመጀመሪያ ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።
.
.
ግሎባል አልያንስ ከምዕራብና ማዕከላዊ ጎንደር #ለተፈናቀሉ 46ሺ ለሚሆኑ ዜጎች 20ሺ የአሜሪካን ዶላር ወይንም በኢትዮጵያ 6 መቶ ሺ ብር #መለገሱን አስታውቋል።
.
.
በፌደራል ስርዓቱ ላይ ከማንም ጋር #ለድርድር እንደማይቀመጥ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) አስታውቋል። ፓርቲው በትናነትናው እለት ባወጣው መግለጫው፥ ኦዲፒ በአጀንዳነት ይዞ ከሚታገልባቸው ጉዳዮች ውስጥ ዋነኛው የፌደራል ስርዓቱ ነው ብሏል።
.
.
በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን #ያአበሎ_ወረዳ በደረሰ #የትራፊክ_አደጋ ከ15 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።
.
.
“ጉዞ ሉሲ ለሰላምና ለፍቅር” የሽኝት መርሃ ግብር ከነገ በስቲያ በይፋ እንደሚካሄድ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቋል።
.
.
ከነገ በስቲያ/ሀሙስ የካቲት 14/2011 ዓ.ም. የሲዳማ ሪፈረንደም ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ በሀዋሳ ከተማ የጠራው #ሰላማዊ_ሰልፍ በመንግስት ፍቃድ አግኝቷል።
.
.
ጥቅምት 4/2011 ዓ/ም ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (#ቴዲ_አፍሮ) በሚሊኒየም አዳራሽ ያቀረበው የሙዚቃ ዝግጅት ደረጃውን በጠበቀ የድምፅ እና የምስል ጥራት #በዲቪዲ የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 16 ለገበያ ይቀርባል ተብሏል።
.
.
#የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲና የባህል ልኡክ አባላት #ከሀዋሳ_ከተማ ነዋሪዎች ጋር #ተወያይተዋል
.
.
ድሬዳዋ ውስጥ በዓመት 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን ማዳበሪያ የሚያመርት ፋብሪካ #ሊገነባ መሆኑን የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ተገልጿል።
.
.
#ቂሊንጦ_ማረሚያ_ቤት ላይ በደረሰው ቃጠሎ በተነሳው ረብሻ ምክንያት የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈፅመዋል በሚል የተጠረጠሩ የማረሚያ ቤት የፖሊስ አባላት ላይ ክስ ተመስርቷል።
.
.
በኢፌዲሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የሁለተኛ ዙር የ100 ቀን ዕቅድ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተርሩ አቶ #ዝናቡ_ቱኑ አስታውቀዋል።
.
.
የሱማሊያ ጫት ነጋዴዎች ከኬንያ ጫት ማስገባታቸውን ትተው #የኢትዮጵያን_ጫት ለመግዛት መወሰናቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኻን ዘግበዋል፡፡
.
.
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ_ገበየሁ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባደሳደር ዶ/ር #አላስቴይር_ዲቪድ ማክፌይል በዛሬው ዕለት የካቲት 12 ቀን 2011 ዓ.ም በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
.
.
በምዕራብ ወለጋ ዞን በነበረው #አለመረጋጋት የተዘረፉ የጦር መሣሪያዎችና ንብረቶች #ተመለሱ። በዞኑ ሁሉም የመንግሥት መዋቅሮችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸውም ተገልጿል።
.
.
የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር በህገወጥ መንገድ ተገንብተዋል ያላቸውን መኖሪያቤቶች ማፍረስ ጀምሯል።
.
.
በምዕራብ ወለጋ ዞን የኦነግ አባላት ህዝቡን #እየተቀላቀሉ ሲሆን፣ በዞኑ፣ መነ ሲቡ ወረዳ አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል።
.
.
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ብሄራዊ አስተባባሪ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት እና በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጋራ የተዘጋጀው የእግር ኳስ ውድድር ከየካቲት 22 እስከ 24 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ምንጭ፦ ኢዜአ፣ ኢ.ፕ.ድ፣ fbc፣ etv፣ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት፣ wazemaradio፣ የጀርመን ራድዮ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለገጣፎ ለገዳዲ‼️

(አቶ አዲሱ አረጋ)

ሰሞኑን በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ህገ ወጥ ግንባታዎች ላይ ህግን ለማስከበር በተደረገ እንቅስቃሴ በመንግስት ይዞታ ስር ባሉ በትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ፣ በአረንጓዴ ቦታዎች፣ በወንዝ ዳር እና የመሰረተ ልማት መገንቢያ ቦታዎች ላይ የተገነቡ እና ከከተማዉ የመሬት አጠቃቃም ፕላን ጋር የሚቃረኑ 347 ቤቶች እና በአጥር የተከለሉ ቦታዎች ላይ እርምጃ መወሰዱ ይታወቃል። የተወሰደዉን እርምጃ ተከትሎ ሰፊ #ቅሬታ በመቅረብ ላይ ይገኛል፡፡

ህገ ወጥነት መከላከል #ለድርድር የማይቀርብ ጉዳይ ባይሆንም በአፈጻጸሙ ሂደት የተፈጠሩ #ግድፈቶች እና #ስህተቶች ካሉ ለይቶ ማረም አስፈላጊ በመሆኑ ይህንን ጉዳይ የሚያጣራ አንድ ግብረ ሀይል ተደራጅቶ ወደ አካባቢዉ እንዲሰማራ ክቡር ፕረዚዳንት #ለማ_መገርሳ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡ በዚህም መሰረት ግብረሃይሉ በጥቂት ቀናት ዉስጥ ወደማጣራት ስራ የሚገባ ይሆናል፡፡ ግብረሃይሉ አጣርቶ በሚያቀርበዉ ሪፖርት መሰረትህገወጥ ግንባታን በማፍረስ ሂደት የተፈጸሙ ስህተቶች ካሉ ህግን ተከትለዉ የሚታረሙ ይሆናል።

ህገ ወጥ ግንባታ የፈረሰባቸዉ የደሃ ደሃ የሆኑ ወገኖቻችን ያለ #መጠለያ እንዳይቀሩ ግብረሃይሉ አጣርቶ በሚያቀርበዉ መሰረት ህግና ስርኣትን በተከተለ መንገድ በአጭር ጊዜ ዉስጥ መፍትሄ እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡

የተወሰደዉ ዕርምጃ #አንድ_ብሄር ላይ ያተኮረ ጥቃት አስመስሎ በማህበራዊ ሚዲያ እና በሌሎች ሚዲያዎች እየቀረበ ያለዉ ዘገባ #ሀሰት መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

#Addisu_Arega_Kitessa
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የአፋን ኦሮሞ ትምህርት #ለድርድር የሚቀርብ አይደለም" የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአፋን ኦሮሞ ትምህርት ለድርድር የማይቀርብና ለቋንቋው እድገት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያን ስርዓተ ትምህርት አስመልክቶ በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠው መግለጫ የአፋን ኦሮሞን  ተጨባጭ  ሁኔታ የማይገልጽ መሆኑንና የክልሉ መንግስት በቋንቋ ጉዳይ ላይ የማያወላዳ አቋም እንዳለው  ህዝቡ ሊረዳ እንደሚገባም ተናግረዋል።

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤትን የማስተዳደር፣ የትምህርት ስርዓትን ማዘጋጀት፣ የስምንተኛ ክፍል ፈተና ማዘጋጀትና አርሞ ውጤት መወሰን  ለክልል የተሰጠ ስልጣን በመሆኑ በዚህ ላይ ጫና የሚያሳድር  ማንም ሊኖር እንደማይገባ ገልጸው፤ እንደ ከዚህ በፊቱ ሁሉ በአፋን ኦሮሞ የሚሰጥ ትምህር እንደሚቀጥልም ነው ያሳወቁት።

የክልሉ መንግስት የአፋን ኦሮሞ ቋንቋን ለማሳደግ ከዚህ በፊት በቋንቋው ትምህርት በማይሰጥባቸው አካባቢዎች ጭምር መማሪያ እንዲሆን እየሰራ በመሆኑ ሁሉም ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ነው አቶ ሽመልስ የገለጹት።

በተጨማሪም በክልሉ ውስጥ ከክልሉ ስርዓተ ትምህርት ውጪ የሚያስተምሩ የግል  ትምህርት ቤቶች ላይም በዚህ ዓመት የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወሰድ ተጠቅሷል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#OROMIA #PEACE

" የመንግሥት ወታደሮች ፣ ሌላም ፣ ንጹሃንም ዋጋ መክፈል የለባቸውም፤ ... ለሰላም ክፍት ነን ድርድሮችም እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን " - የኦሮሚያ ክልል መንግሥት

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አሁንም ቢሆን ያሉ ችግሮች #በሰላም እንዲፈቱ መንግሥት #ለድርድር ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል።

የክልሉ መንግሥት አመራሮች ከኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጋር በአዲስ አበባ እንደመከሩ ተነግሯል።

በምክክሩ ላይ የተገኙት የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ፕሬዜዳንት እና የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ታፈሰ ውይይቱ ልማትና ጸጥታ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ሲሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

በውይይቱ ፦

- የልማት ስራ ያለ ሰላም ውጤት አልባ እንደሆነ / ሰላም ለሁሉም ነገር መሰረት እንደሆነ ፤

- ሰው ሰርቶ የሚበላው ፣ ወልዶ የሚስመው ሰላም ሲኖር እንደሆነ አጽንኦተ ተሰጥቶበታል ብለዋል።

" ሰላም ለመንግሥት ብቻ የተተወ ስላልሆነ እንዴት ነው አብሮ መስራት የሚቻለው ? " የሚለውም መነሳቱን አስረድተዋል።

" መንግሥት እና ሸኔ የጀመሩት ድርድር ፤ በተለያየ ምክንያት አኩርፈው ጫካ የገቡ ነፍጥ ያነገቡ ጓዶች አሉ ፤ መንግሥት በሆደ ሰፊነት ዛሬ ነገ ሳይል እነዚህን አካላት ጠርቶ በጠረጴዛ ዙሪያ መነጋገር አለበት ይህ ሲደረግ ደግሞ ለሰዎቹ እውቅና ተሰጥቶ የህግ ከለላ ተሰጥቶ ነው ውይይት መደረግ ያለበት " የሚለውም መነሳቱን ገልጸዋል።

" በመንግሥት በኩል ' ዛሬም ቢሆን ክፍት ነው እንነጋገራለን ፣ ችግሮችን በጋራ ተነጋግረን እንፈታለን ' የሚል ምላሽ ነው የተሰጠን " ሲሉ ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ አሁንም ቢሆን የክልሉ መንግሥት በውይይት ያምናል ብለዋል።

" የመንግሥት ወታደሮች ፣ ሌላም ፣ ንጹሃንም ዋጋ መክፈል የለባቸውም፤ ሙሉ ትኩረታችን ወደ ሰላም ማምጣት ነው ያለብን። የፈለግነውን ነገር በአዳራሽ መወያይት ይቻላል። ጥረቶች ብዙ ነው ያደረግነው አሁንም ለሰላም ክፍት ነን እኛ 3ኛ ዙር ይሁን፣ 5ኛ ዙር ይሁን ፣ 10ኛ ዙር ድርድሮች እንዲቀጥሉ እንፈልጋለን " ብለዋል።

#Ethiopia
#Oromia #VOA

@tikvahethiopia