TIKVAH-ETHIOPIA
#WoalitaSodo በዎላይታ ሶዶ በተከሰተዉ የእሳት አደጋ ለተጎዱ ነጋዴዎች ጊዜያዊ አማራጭ የገበያ ቦታ እየተዘጋጀ ነዉ፡፡ በተለምዶ መናፈሻ ተብሎ የሚጠራዉ የቀድሞ የዎላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ምድረ ግቢ ነዉ በአማራጭ ገበያ ቦታነት እየተዘጋጀ የሚገኘዉ፡፡ የከተማ አስተዳደሩ እና የዞኑ መንግስት ከተጎጂዎቹ ጋር ተወያይተው በተስማሙት መሰረት ነው ስራው የተጀመረው። ነጋዴዎቹ በሚዘጋጅላቸዉ ጊዜያዊ…
#UPDATEWolaitaSodo
1. የጊዜያዊ ገበያዉ ሥራ መጀመር ፦
በዎላይታ ሶዶ ከተማ መርካቶ ገበያ ቃጠሎን ተከትሎ ጊዜያዊ አማራጭ የገበያ ቦታ መዘጋጀቱ ተገልጾ ነበር።
በጊዜያዊ ገበያዉ ከ1,200 በላይ ቦታ ተዘጋጅቶ ከ1,000 በላይ የሚሆኑ ነጋዴዎች ቦታቸዉን ተረክበዉ ሥራቸዉን ጀምረዋል፡፡
ቦታቸዉን የተረከቡ ነጋዴዎች ለጊዜያዊ ጥላነት /ሼድ/ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን በራሳቸዉ እያቀረቡ እየሠሩ ነው።
2. የፌደራል አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ድጋፍ ፦
በመርካቶ ገበያ በደረሰው አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የፌደራል አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን 2 ሺህ 4 መቶ 93.6 ኩንታል ስንዴ እና ሌሎች አልሚ ምግቦች እርዳታ አደርጓል።
በተደረገው እርዳታ በቤተሰብ ደረጃ 16 ሺህ 626 ሰዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል።
3. የዞኑ አመራሮች ድጋፍ ፦
በመርካቶ በደረሰው የእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም አጠቃላይ የወላይታ ዞን አመራሮች የ1 ወር ደመወዝ ድገፍ አደረጉ።
በአጠቃላይ ቃል የተገባው የአንድ ወር የአጠቃላይ አመራር ደመወዝ 12 ሚሊዮን 97 ሺህ 519 ብር ነው ተብሏል።
ምንጭ፦ የወላይታ ዞን እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት መምሪያ፣ ፌዴራል ስጋት አመራር ኮሚሽን፣ የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT