TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Gambella , #Akobo📍

" የኔትወርክና የመንገድ መሠረተ ልማት ባለመሟላቱ የሚፈጠሩ የፀጥታ ችግሮችን በፍጥነት ለመፍታት አዳጋች ሆኗል " - አቶ ኮንግ ጋትዮቴ

በጋምቤላ ክልል በአኮቦ ወረዳ ከደቡብ ሱዳን በሚነሱ የሙርሌ ታጣቂዎች ድንበር አቋርጠው ህብረተሰቡ ላይ ጉዳት እንዳያደርሱ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን የወረዳዉ አስተዳደር አስታውቋል።

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኮንግ ጋትዮቴ እንዳሉት ከደቡብ ሱዳን የሚነሱ የሙሩሌ ጎሳ ታጣቂዎች በተለያዩ ጊዜያት ድንበር አቋርጠዉ በመግባት ጥቃት ሲፈፅሙ ቆይተዋል ብለዋል።

ታጣቂ ቡድኑ በሰዉ ህይወት ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት ባለፈ ህፃናትንና የቁም እንስሳትን ሲዘርፉ እንደነበር ጠቅሰዉ በአሁኑ ወቅት ከክልሉ የጠጥታ አካላት ጋር በመቀኛጀትና የስጋት ቀጠናዎችን በመለየት መሰል ጥቃት እንዳይፈፀም እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በወረዳዉ የኔትወርክና የመንገድ መሠረተ ልማት ባለመሟላቱ የሚፈጠሩ የፀጥታ ችግሮችን በፍጥነት ለመፍታት አዳጋች እንደሆነባቸዉ ገልፀዉ መንግስት እነዚህ መሠረተ ልማቶች ላይ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በሌላ በኩል የክልሉ መንግስት በጥቃቱ ለተጎዱ እና ለተፈናቀሉ ከ2,500 በላይ ወገኖች በ2 ሚሊዮን ብር 600 ኩንታል በቆሎ በመግዛት ድጋፍ ማድረግ መቻሉን የክልሉ አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ መግለፁን ከጋምቤላ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ያገኘነው መረጃ ያሳያል

@tikvahethiopia