TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የቅዱስ_ገብርኤል_ንግስ_በዓል_በሀዋሳ

በሲዳማ ክልላዊ መንግስት ሀዋሳ ከተማ የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል በደመቀ ሁኔታ ለማክበር በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንግዶችን መቀበል የሚያስችል ልዩ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተገልጿል።

ለበዓሉ ለሚመጡ እንግዶች በፆምና ፃም ባልሆኑ የምግብ አይነት ለማስተናገድ የሰራተኛ ቁጥር በመጨመር በቂ ዝግጅት እንዳደረጉ አሳውቀዋል።

በዓሉን ምክንያት በማድረግ ምንም አይነት የዋጋ ጭማሪ እንደማይደረግ የሀዋሳ ንግድና ገበያ ልማት አሳውቋል።

ድንገት ዋጋ የሚጨምር ነጋዴ ከተገኘ በህግ አግባብ ወዲያውኑ በማሸግም ሆነ በመቅጣት እርምጃ ይወሰድበታል ተብሏል።

በሌላ በኩል የሀዋሳ ከተማ የትራፊክ አደጋ መከላከል እና ቁጥጥር ዋና ስራ ሂደት በበዓሉ የትራፊክ አደጋ አንዳይከሰት እና የተሳለጠ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲኖር የተሸከርካሪና የእግረኛ መንገዶች መለየታቸውን አሳውቋል።

የህዝብና የመንግስት ትራንስፖርት በተገቢው ሁኔታ መዘጋጀቱ የተነገረ ሲሆን ምንም አይነት የትራንስፖርት ዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር ከወትሮው የተለየ ቁጥጥር ይደረጋል መባሉ ከሀዋሳ ከተማ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia