#DrAbiyAhmed
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በሆስፒታል በህክምና ላይ የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላትን መጎብኘታቸውን በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ “ዛሬ ጠዋት ኢትዮጵያን ከራስ በላይ ያስቀመጡ በሆስፒታል የሚገኙ ሴት እና ወንድ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጀግኖቻችንን ጎብኝቻለሁ! አገልግሎታችሁን እናከብራለን” ብለዋል፡፡
ይሁንና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ስላደረጉበት ሆስፒታል የገለጹት ነገር የለም፡፡
Via AlAin News
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

#AntonioGuterres #DrAbiyAhmed
የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በዛሬው ዕለት ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጋር መነጋገራቸውን የዋና ፀኃፊው ቃል አቀባይ ስቴፋን ጁዣሪች ገልጸዋል፡፡
አንቶኒዮ ጉተሬዝ :
- የህግ የበላይነትን በፍጥነት ማስፈን፣
- ለሰብአዊ መብቶች ሙሉ በሙሉ እንዲከበሩ ማድረግ ፣
- ማህበራዊ ትስስርን ማስፈን ፣
- ሁሉን አቀፍ እርቅ መፈጸም ፣
- የህዝብ አገልግሎቶችን አቅርቦት እንደገና መጀመር እና ያልተገደበ ሰብዓዊ ተደራሽነት ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ አንስተዋል፡፡
ተመድ የአፍሪካ ህብረትን ተነሳሽነት ለመደገፍ ሙሉ በሙሉ ቁርጠኛ መሆኑንም ነው ዋና ጸኃፊው ገልፀዋል፡፡
በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ እንዳሳሰባቸው የገለጹ ሲሆን ድርጅቱ ለስደተኞች ፣ ለተፈናቀሉ ዜጎች እና በችግር ላይ ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ ሰብአዊ ድጋፍ ለመስጠት ሙሉ ቁርጠኛ መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡ (AlAIN)

ዛሬ መጋቢት 24 ዶ/ር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሰየሙበት ቀን ነው።
ልክ በዛሬው ቀን የዛሬ 3 ዓመት ነው የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዶክተር አብይ አህመድን (በዛን ወቅት የኢህአዴግ ሊቀመንበር) ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ የሰየመው።
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እንደሚታየው ጠ/ሚሩ ወደስልጣን ከመጡበት ጊዜ ያሳኳቸውን፣ የተገበሯቸውን ተግባራት በማንሳት የሚደግፏቸው ፤ በአንፃሩ ያሉ ጉድለቶችን በማንሳትም የሚቃወሟቸው በርካቶች ናቸው።
@tikvahethiopia

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DrAbiyAhmed
ጠ/ሚር ዶክተር አብይ አህመድ ፥ "ኢትዮጵያ ዓባይ ወንዝን ለልማቷ ስታውል ፣ በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት የማስከተል ፍላጎትም ዕቅድም የላትም" ብለዋል።
ዶክተር አብይ ይህን ያሉት ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ላይ ባሰራጩት መልዕክት ነው።
ጠ/ሚኒስትሩ ባለፈው ዓመት የተገኘው ከፍተኛ የዝናብ መጠን የሕዳሴውን ግድብ የመጀመሪያ ዙር ሙሌት እውን ያደረገ መሆኑን አስታውሰው ፥ "የግድቡ መኖር በራሱ ጎረቤት ሀገራችን ሱዳን በጎርፍ እንዳትጥለቀለቅ በአስተማማኝ ሁኔታ ተከላክሎላታል" ሲሉ ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ ሁለተኛው የውኃ ሙሌት ከመቀጠሉ በፊት ፣ አዲስ በተጠናቀቁት የውኃ መውረጃዎች አማካኝነት ባለፈው ዓመት ከተገደበው ተጨማሪ ውኃን የምትለቅቅ መሆኑን እና መረጃንም እንደምታጋራ ገልፀዋል።
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ "ሁለተኛው ሙሌት የሚከናወነው ከፍተኛ የዝናብ መጠን በሚገኝባቸው የሐምሌ/ነሐሴ ወራት በመሆኑ፣ ሱዳን በጎርፍ እንዳትጥለቀለቅ ለመከላከል ይጠቅማታል" ብለዋል።

TIKVAH-ETHIOPIA
* Update ከአዲስ አበባ ሞያሌ - ከናይሮቢ ሞንባሳ የመንገድ ኮሊደር የሆነው የሞጆ - ሀዋሳ መንገድ በኮንትራት 1 እና 2 ያሉት ወደ 90 ኪሎሜትር ግንባታ ተጠናቋል፤ መንገዱ ዛሬ እንደሚመረቅም ከetv የተገኘው መረጃ ያሳያል። አጭር መረጃ፦ - ከሞጆ - ሀዋሳ ድረስ እየተገነባ ያለው የፍጥነት መንገድ አጠቃላይ 13.7 ቢሊዮን ብር የተበጀተለት ሲሆን ውጪው ከዓለም ባንክ፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክ፣…
#DrAbiyAhmed
የሞጆ-ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ አካል የሆነው የሞጆ-መቂ-ባቱ የመንገድ ግንባታ በዛሬው ዕለት በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተመርቋል።
ቀድም ብለን በሰጠነው መረጃ ይህ የፍጥነት መንገድ 92 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው።
መንገዱ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል።
ፎቶ : አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ
@tikvahethiopuaBOT @tikvahethiopia

በዛሬው ዕለት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድና ልዑካን ቡድናቸው ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ጅቡቲ ገብተዋል።
የጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዚደንት በዓለ ሲመትን እንደሚታደሙም የጠ/ሚ ፅ/ቤት አስታውቋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ነገ ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ነገ ክፍት ሆነው አገልግሎት እንዲሰጡ አሳስበዋል።
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፥ ባለፈው ሳምንት ለ6ኛው ብሔራዊ ምርጫ ሰኞ በሚዘጉ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ምትክ ቅዳሜ የሥራ ቀን እንደሚሆን አሳውቀው እንደነበር አስታውሰዋል።
በዚህም #ነገ ሰኔ 19/2013 ሁሉም መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ክፍት ሆነው አገልግሎት እንዲሰጡ ማሳሰቢያ አስተላልፈዋል።

ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ብልጽግና ፓርቲ በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ የሚያሸንፍ ከሆነ በምርጫ የተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ ተሳትፏቸው ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ የመንግስት መዋቅር ውስጥ ውክልና ወይም ተሳትፎ እንዲኖራቸው እንደሚያደርግ ገለጹ፡፡
ብልጽግና ፓርቲ የሚሸነፍ ከሆነ የኢትዮጵያን አሸናፊነት ለማረጋገጥ መንግስት ለአሸናፊው የፖለቲካ ፓርቲ ስልጣኑን በሰላማዊ መንገድ ያስረክባል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሳወቁት የኢትዮጵያ ሲቭል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ባዘጋጀው የምስጋና ፕሮግራም ላይ መሆኑን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግቧል።

የጀርመኗ መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ዛሬ ከሰዓቱን በጠሩት የጂ-20 ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ የተሰኘ ጉባዔ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በበይነ መረብ በመታገዝ ተሳትፈዋል።
“ለንግድ እና ለኢንቨስትመንት ማሕቀፋዊ ሁኔታዎች” በሚል ርዕስ የሚካሄደው ጉባዔ የስምምነቱ ፈራሚ የሆኑ ሀገራት ተጨማሪ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን እንዲያገኙ በሚያስችል ሁኔታ ማሕቀፋዊ ሁኔታዎችን ወደ ቀጣይ ርምጃዎች ለመውሰድ የታለመ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ንግግር፣ ለሙዐለ ነዋይ ፍሰት ምቹ ነባራዊ ሁኔታ እንዲኖር ለማስቻል በኢትዮጵያ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አማካኝነት ማክሮ ኢኮኖሚያ፣ መዋቅር እና የዘርፍ ማሻሻያዎች መደረጋቸውን ገልጸዋል።
#PMofficeEthiopia

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል አዘዙ። የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከትግራይ ክልል ቀውስ ጋር በተገናኘ ተጠያቂ ባደረጓቸው ፦ - የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት - የአማራ ክልል ባለስልጣናት - የህወሓት አመራሮች - የኤርትራ መንግስት አመራሮች ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል አዘዙ። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዛሬ በፈረሙት የስራ አስፈጻሚ አካል ትዕዛዝ (executive order) የትግራይ…
#DrAbiyAhmed #JoBiden
የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ግልፅ ደብዳቤ ✉️ ፃፉ።
ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በፃፉላቸው ግልፅ ደብዳቤ በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ 🇪🇹 ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ፥ ሕወሓት በአፋርና አማራ ያፈናቀላቸው ንፁሃን ዜጎች በከፋ ችግር ውስጥ ወድቀው እንደሚገኙ የገለፁ ሲሆን ቡድኑ ቤተሰቦቻቸውን እንደገደለባቸው እንዲሁም የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን ጨምሮ ንብረት እንዳወደመ አስረድተዋል።
በኢትዮጵያ ላይ እየደረሱ ያሉ የውጭ ጫናዎች ተገቢ አለመሆናቸውንም አሳውቀዋል።
ዶ/ር ዐቢይ ፥ በቅርቡ የተመሰረተው አዲሱ የባይደን አስተዳደር ከዚህ ቀደም ከነበረው የተሻለ እንደሚሆን ኢትጵያውያን ተስፋ እንደነበራቸው አውስተዋል።
አሜሪካ ሌሎች ሃገራት ላይ በነበራት የተሳሳተ የውጭ ፖሊሲ በሃገራቱ ላይ ያስከተለውን ቀውስ አስታውሰዋል፡፡
ኢትዮጵያ 🇪🇹 ተስፋ በቆረጡ እና ስልጣን ከሚሊዮኖች ደህንነት በላይ በሚያሳስባቸው ግለሰቦች አትሸነፍም ሲሉም ገልጸዋል፡፡ #ኢትዮጵያዊ እንዲሁም #አፍሪካዊ ማንነታችን እንዚህ ግለሰቦች እንዲያሸንፉ አይፈቅድልንም ብለዋል፡፡

#Update በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በዓለ ሲመት ላይ የተገኙ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ንግግር አድርገዋል። ለጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ የ "እንኳን ደስ አልዎት!" መልዕክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን መሪዎቹ በንግግሮቻቸው ያነሷቸውን ጉዳዮች በዚህ ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-10-04 @tikvahethiopia
#DrAbiyAhmed
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ "አካታች ብሔራዊ ውይይት" እንደሚካሄድ ገለፁ።
ይህን የገለፁት በበዓለ ሲመታቸው ላይ ባደረጉት ባሰሙት ንግግር ነው።
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፥ ብሔራዊ ውይይቱ "ችግሮቻችንን በጠረጴዛ ዙሪያ ይፈታሉ ብለው የሚያምኑትን" የሚያካትት እና በኢትዮጵያውያን የሚመራ እንደሚሆን ጥቆማ ሰጥተዋል።
በትግራይ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ተቀስቅሶ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች የተዛመተው እና "በክህደት እና በእብሪት የተጠነሰሰ" ያሉት ግጭት "እንደ ሀገር እጅግ ከባድ ዋጋ" ማስከፈሉንም ተናግረዋል።
" ጠላት ብረት አንስቶ እንደ ብሌናችን የምናየውን የሰሜን እዝ አጠቃ፤ የጥሞና ጊዜ እንስጥ ባልንብት ጊዜም ህጻናትን እያስታጠቀ በርካታ ዜጎቻችንን አጠቃ፤ ንብረትም አወደመ" ሲሉም ተደምጠዋል።
“እኛ ኢትዮጵያውያን ሰልፍ ይዘን ስንዘምትም ሆነ ሰይፍ ይዘን ስነነሳ ጠባችን ኢትዮጵያ ጠል ከሆኑት ጋር ብቻ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፤ ኢትዮጵያ የተማሏ አቅም እና አቋም ያለው የፀጥታ ሀይል ታደራጃለች” ሲሉም ተናግረዋል።
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፥ "በመጪው ዘመን ብዝኃነታችንን በጌጥነት ተቀብለን መታረቅ የሚችል ሐሳባችንን አስታርቀን መከበር የሚገባው ልዩነቶቻችችን አክብረን ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን አጠንክረን ወደ ከፍታ የምንተምበት ጊዜ ይሆናል" ያሉ ሲሆን "ይኸም እንዲሳካ የፖለቲካ ልዩነቶቻችንን ለማጥበብ አካታች ብሔራዊ የውይይት መድረክ እናካሂዳለን" ብለዋል።
መረጃው ከዶቼቨለ እና አል ዓይን የተውጣጣ ነው።

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የ "እንኳን ደስ አለዎት! " መልዕክት አስተላለፉ። ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቱን ዶ/ር አቢይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መሰየማቸውን ተከትሎ የ "እንኳን ደስ አለዎት" ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው ፥ የሩሲያ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት በመልካም የወዳጅነት እና እርስ በርስ መከባበር ላይ የተመሠረተ…
#DrAbiyAhmed
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለቀጣይ 5 ዓመታት ኢትዮጵያን እንዲመሩ ከተሾሙ በኃላ የተለያዩ ሀገራት የደስታ መግለጫ እያስተላለፉ ይገኛሉ።
ኬንያ፣ ሱማሊያ ፣ ዩጋንዳ፣ ደ/ሱዳን፣ ጁቡቲ ፣ ናይጄሪያ፣ ሴኔጋል ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፣ አልጄሪያ መሪዎቻቸው እና ከፍተኛ ባለስልጣኖቻቸው እዚህ ኢትዮጵያ ተገኝተው መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
የኤርትራ በፕሬዘዳንቷ ፣ የዩኤኢ መሪዎች ፣ ቬትናምም በጠቅለይ ሚኒስትሯ የመልካም ምኞት መግለጫቸውን የላኩ ሲሆን ዛሬም ሩሲያ በፕሬዜዳንቷ ለ5 ዓመታት የኢትዮጵያ መሪ እንዲሆኑ ለተሾሙት ዶ/ር ዐቢይ "እንኳን ደስ አልዎት" መልዕክት ልካለች።
ማምሻውን ደግሞ የኳታር አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አልታኒ ጨምሮ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።