TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ከ3 ሳምንት ያላነሰ ጊዜ የሚፈልገውን ሥራ  በአንድ ሳምንት ነው ያጠናቀቁት " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው ጦርነት ጉዳት ደርሶበት የነበረው የወልዲያ አላማጣ የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ መደረጉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳውቋል። ያለዕረፍት በተሰራ ሥራ የማስተላለፊያ መስመሮች ጥገና እና የተሰበሩ ኢንሱሌተሮች…
#Update

ከአላማጣ እስከ ቆቦ የሚገኙ አካባቢዎች ዳግም #የኤሌክትሪክ_ኃይል ማግኘታቸው ተገልጿል።

የኤሌክትሪክ ኃይል ያገኙት ፦

- አላማጣ፣
- ኮረም፣
- ዋጃ፣
- ጥሙጋ እና ቆቦ ከተሞች ናቸው።

ከአላማጣ እስከ ላሊበላ የተዘረጋውን የ66 ኬ.ቪ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ በአካባቢው ያሉ ከተሞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#ሲዳማ

የ " በላይነህ ክንዴ ግሩፕ "  በሲዳማ ክልል በሎካ አባያ ወረዳ 550 ሔክታር መሬት ተረክቦ በፍራፍሬ እና በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በመመደብ ልማት መጀመሩን የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የእርሻ ዘርፍ አስፈጻሚ ዶ/ር አንተነህ አብዋ ለሪፖርተር ጋዜጣ  በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

ዶ/ር አንተነህ አብዋ ምን አሉ ?

- በሲዳማ ክልል ሎካ አባያ ወረዳ 550 ሔክታር መሬት ተረክበረን 380 ሔክታር መሬት ላይ አትክልት ከማልማት አስቀድሞ የበጋ ስንዴ እያለማን እንገኛለን ፤ ምርታችንን ለውጭ ገበያ ለማቅረብም አቅደናል።

- በሔክታር ከ30 እስከ 50 ኩንታል ለምግብ ፍጆታ የሚውል ስንዴ ለማልማትና ከዚህም በጥቂቱ ከ11,400 በላይ ኩንታል ስንዴ ለመሰብስብ ታቅዷል። ለዚህም ከ600 በላይ ኩንታል ስንዴ ለዘር ተጠቅመናል።

- ለስንዴና ማዳበሪያ ግዥ ከ300 እስከ 400 ሚሊዮን ብር ወጪ አድርገናል። 400 ኩንታል ኤንቲኤስ፣ እንዲሁም 400 ኩንታል ዩሪያ መሬቱን ለማሰናዳት ማዳበሪያ ተጠቅመናል።

- የእርሻ ልማቱን ለማከናወን በአጠቃላይ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል፤ ከ20 ኪሎ ሜትር መንገድ እንዲሁም ወደ እርሻው የሚፈሰውን የወንዝ ውኃ ለመቆጣጠር 4 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ግድብ ተገንብቷል።

-  የአባያ ሐይቅና የብላቴ ወንዝን ለእርሻው በዋነኛነት እንጠቀማለን፤ ለዚህም ዘመናዊ ፓምፖችን ለመጠቀም ተሰናድተናል።

- በአካባቢው የዝናብ እጥረት ያለበት አካባቢ በመሆኑ ከአባያ ሐይቅ እስከ እርሻው መዳረሻ ድረስ ሦስት ኪሎ ሜትር ያለውን ርቀት በፓምፕ ስቦ ለማምጣት መሠረተ ልማት ተዘርግቷል።

- የበጋ ስንዴ ማልማቱ ሲጠናቀቅ የአትክልትና የፍራፍሬ ልማቱ ይቀጥላል ፤ አቮካዶ፣ ሙዝና ፓፓዬ ለማልማት የችግኝ ግዥ ተፈጽሞ ለመትከል ዝግጅት ላይ ነን።

- መሬቱን ከተረከብን 4 ወራት ብቻ  ሲሆን አትክልትና ፍራፍሬ ማልማቱንም ለማስቀጠል ከ40 ሔክታር መሬት በላይ አቮካዶ ተተክሏል። በቀሪዎቹ ሙዝ፣ ብርቱካን፣ ሎሚ፣ እንዲሁም ፓፓዬ ለማልማት ታቅዷል። በዚህ መሬት ላይ ተጨማሪ ፍራፍሬዎችን ለማሰናዳት የችግኝ ማፍላት ሥራ እየተሰራ ነው። ለጊዜው ለ200 የአካባቢው ሠራተኞች፣ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፤ ይኼም ቁጥር ወደ 500 ለማሳደግ ታቅዷል።

በሌላ በኩል ፤ በላይነህ ክንዴ ግሩፕ ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጋር በመተባበር በአካባቢው ለምትገኘው #መራሬ_ከተማ #የውኃ እና #የኤሌክትሪክ_ኃይል ለመዘርጋት የኮንክሪትና የእንጨት ፖል ዝርጋታ በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ተሰምቷል።

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ

@tikvahethiopia