TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጅንካ⬇️

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በ60 ሚሊየን ብር ወጪ በጅንካ ከተማ ያስገነባው የከረጢት ፋብሪካ የምርት ስራው #ቆሟል

5 የኦሞ ኩራዝ ስኳር ፕሮጀክቶች በደቡብ ኦሞ ዞን መገንባታቸውን ተከትሎ በጂንካ ከተማ በ18 ነጥብ 2 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው የከረጢት ፋብሪካው "ኮርፖሬት ኒው ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት” በተሰኘ ተቋም ግንባታው ተጠናቆ የሙከራ ምርት ማምረት ችሎ ነበር።

ሆኖም ፋብሪካውን የሚያስተዳድረው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አምርቶ መሸጥ ለሚችል 3ኛ ወገን ሳያስተላልፍ በመቆየቱና ለሙከራ የቀረበው ግብዓትም በማለቁ አሁን ፋብሪካው ምርት ማቆሙን fbc በስፍራው ባደረገው ቅኝት #አረጋግጧል

የጅንካ ከረጢት ፋብሪካ በሙከራ ወቅት ከ400 ሺህ በላይ ከረጢት ያመረተ ሲሆን፥ ፍብሪካው ለሚመለከተው አካል አለመተላለፉን ተከትሎ የገበያ ትስስር ሊፈጠርለት አልቻለም።

ከዚህ ባሻገርም ፋብሪካው በራሱ በብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የውስጥ ስምምነት መሰረት 130 ሰራተኞችን ቀጥሮ እንዲንቀሳቀስ ሲያደርግ ቢቆይም፤ በተጠቀሱት ምክንያቶች ስራ እንዲያቆም ሲደረግ 89 ሰራተኞች ከስራ እንዲሰናበቱ መደረጉ እና በበረሃ አበል ክፍያ ላይ ችግሮች መኖራቸው ቅሬታ እንዲፈጠር አድርጓል።

የጅንካ ከረጢት ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ ሺህ አለቃ ቀረብህ ህብስቱ እንደተናገሩት፤ ፋብሪካውን ተረክቦ ምርት እያመረተ መሸጥ ለሚችል አካል ለማስተላለፍ እና የሙከራ ምርቶቹንም ለመሸጥ የጨረታ ማስታወቂያ ወጥቶ ክትትል እየተደረገ ነው።

የፋብሪካው የሰው ሃይል አስተዳደር አና ልማት ሃላፊው ሺህ አለቃ ማጆር ተሰማ በበኩላቸው ከስራ ገበታቸው የተሰናበቱ ሰራተኞች ፍብሪካው እስኪተላለፍ ድረስም ቢሆን እንዲመለሱ እና የክፍያ ቅሬታቸውም ውይይት እንዲደረግበት መወሰኑን ገልፀዋል።

የጅንካ ከረጢት ፋብሪካ በሙሉ አቅሙ መስራት ሲጀምር በአመት 30 ሚሊየን ከረጢት የማምረት አቅም ያለው ሲሆን በሙከራ ወቅት በቀን ከ1 መቶ ሺህ በላይ ከረጢት የማምረት ብቃት እንዳለው ተረጋግጧል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሁኔታው አሁንም አሳሳቢ ነው...

በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል ያለው #የፀጥታ ሁኔታ አሁንም #አሳሳቢ መሆኑን አብመድ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እየገለጹ ነው፡፡ ከፓዊ ወረዳ ሕዳሴ ቀበሌ አባወረኛ አካባቢ ነዋሪዎች ለአብመድ እንደተናሩት ከትናንት ከሰዓት በኋላ ጀምሮ የተኩስ ልውውጥ #ቆሟል፤ ቀስት #የሚያስወነጭፍም የለም፡፡ ጥቃት አድራሾቹ በከፊል ወደ #ጫካ ውስጥ #ሸሽተዋል፤ በከፊልም በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ ‹‹በዚህም ግልጽ የሚታይ ግጭት የለም፤ የሰላም ድባብ ግን #አይታይም›› ብለዋል፡፡

ሌላኛው ነዋሪ ደግሞ ከትናንት ምሽት 12፡00 አካባቢ ጀምሮ እስካሁን ግጨት አለመኖሩን ገልጸው ያንዣበበ #ስጋት መኖሩን አመልክተዋል፡፡ ትናንት ቤቶች መቃጠላቸውንና የተናገሩት እኚሁ አስተያየት ሰጪ ዛሬ ከሰዓት በኋላ #የአፀፋ እርምጃ ለመውሰድ ቅድመ ዝግጅት እንዳለ በመጠቆም መንግሥት #ጥፋት እንዳይደርስ እንዲቆጣጠር #አሳስበዋል፡፡ ‹‹ወንዶች ሚስቶቻቸውንና ልጆቻቸውን እያሸሹ ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ ነው፡፡ ትናንት ሙሉ በሙሉ ቤተሰባቸውን ከአካባቢው ያሸሹ ሰዎችም አሉ፤ የትናንቱ ጥቃት አድራሽ ቡድንም ዛሬም ለሌላ ጥፋት እየተንቀሳቀሰ በከፊል በቁጥጥር ሥር ሲውል ተመልክቻለሁ፡፡ ቀስትና የጦር መሣሪያ የያዙ ቡድኖች ወደ መንደር 49 እየተንቀሳቀሱ አባት በለስ ወንዝ ድልድይ ላይ መከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ይዘዋቸዋል›› ብለዋል አስተያየት ሰጪው።

በበለስ ከተማ መንደር ሁለት ነዋሪ የሆኑ አስተያየት ሰጪም የጦር መሣሪያና ቀስት የያዙ ከ30 በላይ ሰዎች በለስ ወንዝ አካባቢ መከላከያ ሠራዊትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ዛሬ ረፋድ 3፡30 አካባቢ #ተይዘው መመለሳቸውን ተናግረዋል፡፡ ‹‹አባወረኛ ላይ ብዙ ነገር ወድሟል፤ የክልሉ መንግሥት ምን እንደሚያደርግ #አናውቅም፤ እንዲያውም የመንግሥት ባለስልጣናት ሴራ እንዳለበት እናምናለን፡፡ የምናደርገው ግራ ገብቶናል›› ብለዋል ነዋሪው፡፡

መንግሥት ግጭቶችን ከማብረድ በውጥን ላይ ማስቀረትን ትኩረት እንዲሰጥ ያሳሰቡት ነዋሪዎቹ የመከላከያና የፌዴራል ፖሊስ ኃይል በብዛት ወደ አካባቢው እንዲገቡና ለረዥም ጊዜ ቁጥጥር እንዲያደርጉ በተለይም ዛሬ ከሰዓት በኋላ እንደሚኖር የሚሰጋውን ጥቃት እንዲያከሽፉም ጠይቀዋል፡፡ ‹‹አሁን ግጭቱ ያለው ቀይና ጥቁር በሚል ነው፤ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የፌዴራል መንግሥት ዘላቂ መፍትሔ ካልፈለገ ሁኔታው አሳሳቢ ነው›› ብለዋል አስተያዬት ሰጭዎቹ፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia