TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሱማሌ ክልል⬇️

አቶ #ሙስጠፋ_ሞሐመድ_ዑመር ጊዜያዊ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ።

አቶ ሙሰጠፋ ሞሐመድ የክልሉ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲመሩ የሶማሌ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሶህዴፓ) የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው እንደመረጣቸው አዲስ አበባ የሚገኘው የቢቢሲ ሶማልኛ ሪፖርተር #አረጋግጧል

አቶ ሙሰጠፋ ሞሐመድ የክልሉ ጊዜያዊ ፕሬዚዳንትነታቸው በተጨማሪ የሶህዴፓ ምክትል ሊቀመንበር ተደርገው ተሹመዋል።

የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጸ/ቤት ኃላፊ ሚንስትሩ አህመድ ሺዴ የሶህዴፓ ሊቀመንበር ተደርገው መሾማቸው ይታወሳል።

አቶ ሙስጠፋ የቀድሞ ፕሬዚዳንት አብዲ ሙሐመድ ኡመር የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ይፈጽማሉ በማለት በተደጋጋሚ በመተቸት ይታወቃሉ።

የቀድሞ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ አብዲ ሞሐመድ ኡመር ከስልጣናቸው ከተነሱ ሁለት ሳምንታት አልፈዋል።

አቶ አብዲ ሞሐመድ ክልል ፕሬዚዳንትነታቸው መነሳታቸው ከተሰማ ከሁለት ቀናት በኋላ አህመድ አብዲ ሼክ ሞሃመድ (ኤልካስ) ፕሬዚዳንት ተደርገው ተሹመው ነበር።

©BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia