TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NewsAlert

ዛሬ በተካሂደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ላይ 95 በመቶ መግባባት ላይ መደረሱን ሊቀ አእላፍ ቀሲስ #በላይ_መኮንን ገለፁ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያ ተልኮ መመሪያ ዋና ኃላፊ መጋቤ ሰላም ቀሲስ #ሰለሞን_ቶልቻ በበኩላቸው፤ ውይይቱ በጥሩ መንፈስ መጠናቀቁን ገለፀው በነገው ዕለት መቋጫ እንደሚበጅለትና መግለጫ እንደሚወጣ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ዛሬ ጠዋት መወያየታቸው ይታወቃል።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia