TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" በረሃብ የሰዎች ህይወት ስለማለፉ ማረጋገጫ የለንም " - አምባሳደር ሽፈራው ተ/ማርያም (ዶ/ር)

የፌዴራል አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) " በኢትዮጵያ በረሃብ ምክንያት የሰው ህይወት አልፏል የሚል ማረጋገጫ የለንም " አሉ።

ኮሚሽነሩ ይህንን ያሉት ከፋና ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው።

አምባሳደር ሽፈራው ተ/ማርያም (ዶ/ር) ምን አሉ ?

- መንግስት 11 ቢሊዮን ብር መድቦ እየሰራ ነው።

- በፌዴራል የሚደረገው ድጋፍ ክልሎችና ከታች ያሉ መዋቅሮቻቸው እንዲሁም ማህበረሰቡ በሚያደርገው ድጋፍ ላይ ተጨማሪ ነው።

- አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የአህል ክምችት ቢኖረንም ትራንስፖርት ሰጪዎች በፀጥታው ምክንያት በፈለግነው ልክ ለማቅረብ አልቻልንም የሚሉት ነገር አለ። ይሄን ከሚመለከታቸው ጋር ተነጋግሮ ይስተካከላል።

- የድርቅ አደጋ ወደ ረሃብ ተቀይሮ የሰውን ህይወት የሚያጠፋበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ መዋቅራዊ አደረጃጀታችን የሚፈቅል አይደለም። የቀበሌ፣ የወረዳ ፣ የዞን፣ የክልል መዋቅር አለን የሚችለውን የመደጋገፍ ስራ ይሰራል። ህይወትን የመታደግ ስራ ይሰራል። እዚህ ላይ የፌዴራልም ድጋፍ አለ።

- የድርቅ አደጋ በሚኖርበት ጊዜ የስነምግብ ሁኔታዎችን በመውሰድ ምናልባት በአካባቢው የሚፈጠሩ ወረርሽኝ እና የመሳሰሉት ነገሮች የተለያዩ ነገሮችን ፈጥረው የዜጎቻችንን በሽታን የመቋቋም አቅም አዳክመው በቀላሉ የመሸነፍ እና የመሳሳሉት ጉዳዮች ሊፈጥር ይችላል።

-ሰዎች እንደሚያነሱት ፤ አንዳንድ #ሚዲያዎች እንደሚያነሱት በእህል እጥረት  ፤ ድርቅ ወደ ረሃብ ተቀይሮ የሰውን ህይወት የሚያጠፋበት ደረጃ የራሱ የሆነ ጊዜ አለው የራሱ የሆነ ጊዜ ይወስዳል በዚህ ነው ሰው የሞተው ለማለት #ምርመራ ይፈልጋል። የሰው የሞት ምክንያት ምንድነው ? እንደምናውቀው ሰው በተለያዩ ምክንያቶች ህይወቱ ያልፋል የዛ ህይወቱ ያለፈው ሰው ምክንያቱ ምንድነው ? የሚለውን የመለየት እና የማረጋገጥ ስራ የራሱ የሆነ አካሄድና  መንገድ ይጠይቃል።

- በእኛ በኮሚሽናችን ግምገማ የተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት አለመኖር የሚፈጥራቸው ተጋላጭነት ሊኖር እንደሚችል የምንገነዘብ ቢሆንም ግን በረሃብ ምክንያት ህይወቱ ያለፈ ሰው ስለመኖሩ #ማረጋገጫ_የለንም
.
.
በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ እና አማራ ክልሎች ያሉ ከታች ያሉ መዋቅሮች በረሃብ ምክንያት ሰዎች ህይወት እንዳለፈ በተደጋጋሚ መግለፃቸው ይታወሳል።

በትግራይ ክልል የላይኛው መዋቅርም 25 ህፃናትን ጨምሮ 400 ሰዎች በረሃብ ምክንያት ህይወታቸው እንደጠፋ ማሳወቁ አይዘነጋም።

በክልል ከታች እስከላይ ማዋቅር የሚሰጡት እና ነዋሪዎች የሚገልጹት የረሃብ ሁኔታ በፌዴራል አደጋ ስጋት አመራር ቅቡልነት የለውም። ኮሚሽኑ በረሃብ ምክንያት የጠፋ ህይወት ስለመኖሩም ማረጋገጫ የለኝም ብሏል።

ከዚህ ቀደም የፌዴራል አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን  " ክልሎች ትኩረት እና የተሻለ ድጋፍ ለማግኘት ሲሉ ' ይህንን ያህል ሰዎች #ሞተውብኛል፣ ይህንን ያህል ተጎድተውብኛል ' የሚል መረጃ ያቀርባሉ " ማለቱ አየዝነጋም።

@tikvahethiopia