TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Waghimra : በአማራ ክልል የዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የአደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ፅ/ቤት በጦርነት ቀጠና ያሉ ከ635 ሺህ በላይ ወገኖች በከፋ የረሃብ አደጋ ውስጥ እንደሚገኙ አመልክቷል።

የፅ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መልካሙ ደስታ ለጀርመን ድምፅ ዛሬ በሰጡት ቃል ፤ በዋግኽምራ በጦርነት ቀጠና ያሉ ከ635 ሺ በላይ ሰዎች ለከፋ የረሃብ አደጋ መጋለጣቸውን ተናግረው ዓለም አቀፍ ረጂ ድርጅቶች እስካሁን ተግባራዊ ምላሽ አልሰጡም ሲሉ ወቅሰዋል።

በአካባቢው መብራት፣ ውሃ ፣ኔትዎርክ የለም መንገድም ተዘጋግቷል ያሉት አቶ መልካሙ ከፍተኛ የሆነ የምግብ አቅርቦት ችግር መኖሩን አመልክተዋል።

በተለይም የጤና አገልግሎት መስተጓጎሉን ስር የሰደደ ህመም ያለባቸው ወገኖች መታከም እንደማይችሉ አክለዋል።

አቶ መልካሙ ፥ ብሄረሰብ አስተዳደሩ ያለበትን ሁኔታ ዝርዝር ጉዳዮችን በሚመለከታቸው አካላት በማቅረብ ለልዩ ልዩ ረጂ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ቢጠየቅም እስካሁን መልስ እንዳልተገኘ ፤ በአስከፊ ሁኔታ ችግር ላይ የወደቀውን ማህበረሰብ መታደግ እንዳልተቻለ ተናግረዋል።

የዋግኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጳውሎስ በላይ በበኩላቸው ፤ ከነሃሴ 1 ጀምሮ መሰረታዊ ፍጆታዎችን በገበያ ማግኘት እንደማይቻል ገልፀዋል።

አቶ ጳውሎስ ፥ " ጨው፣ ዘይት፣ በርበሬ፣ ሽሮ የለም፤ ቢኖርም ዋጋው ውድ ነው ፣ ባንኮችም ብሎክ ስለሆኑ ብርም የለም ፤ ከአካባቢው እየወጣ የሚመጣው ሰው የሚናገረው ሰቆቃ ነው" ብለዋል።

በሌላ በኩል ፥ በበርካታ ወረዳዎችም የአንበጣ መንጋ በማሳ ላይ የቀረችውን ቀሪ የአርሶ አደር ሰብል እያወደመ ነው ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#Waghimra

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በዚህ ሳምንት በአማራ ክልል ዋግህምራ ዞን ሳሃላ ሰየምት ወረዳ በግጭት ለተጎዱ ከ6,000 በላይ ሰዎች ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉ ሩዝ፣ ሽንብራ፣ የምግብ ዘይት እና የማዕድ ጨውን ያካተተ የምግብ ድጋፍ ነው።

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ባሳለፍነው ወር በዚሁ አካባቢ ለሚገኘው ማህበረሰብ የመጠለያ እና የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

#ICRC

@tikvahethiopoa
#Waghimra

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ያሉ ተፈናቃዮች የከፋ ችግር ላይ መውደቃቸው ተገልጿል።

አስተዳደሩ ዛሬ ባሰራጨው መልዕክት " ዋግ ከችግር ቆፈን ላይ ወድቃለች፤ የመከራ ቃፊር እየናጣት ነው የሚደርስላት ትሻለች " ብሏል።

አሁን ላይ ከአበርገሌ፣ ከጻግብጂ፣ ከዝቋላ፣ ከሰቆጣ ዙሪያ፣ ዛታ፣ ወፍላና ኮረም በጦርነት ምክንያት በየቀኑ ከ2000 ሰው በላይ የተፈናቀለ ወለህ ሜዳ ላይ ሰፍሯል እንዲሁም በሰቆጣ ከተማ ከተለያዩ ቦታዎች የሰፈረው ከ52,000 (ከሀምሳ ሁለት ሺህ ) በላይ ህዝብ መሆኑ ተገልጿል

ቤት ንብረቱን ጥሎ በመጠለያ የሚኖረው ማህበረሰብ የማይቻል ችግር ተሸክሟል ተብሏል።

አዛውንቶች፣ እናቶች፣ ህጻናት በአስቸጋሪ ሆኔታ ላይ የሚገኙ ሰሆን ከእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖባቸው እርሀባቸውን እንዳይችሉ በበሽታ ተቆራምደዋል ተብሏል።

አዛውንቶች፣ ጧሪ የሌላቸው ሽማግሌዎች በሽታው፣ እርጅናው እና ረሀቡ እየተፈራረቀባቸው ሞታቸውን እየናፈቁ ነው።

" ዋግ ላይ መቋጫ የሌለው ችግር ፣ እፎይታ የሌለው መከራ፣ እየተፈራረቀ ነው " ያለው አስተዳደሩ " የሰው ልጅ እንደዘበት ሜዳ ላይ ወድቋል ፤ በዋግ ህዝብ ላይ የመከራ ጅራፍ አልለይ ብሏል፤ የችግር ድምጽ በህጻናት አእምሮ ሰፍሮ የሳቅ አንደበታቸው ተዘግቷል " ሲል አስተድቷል።

በዋግ ያሉ ተፈናቃዮች በየጊዜው የሚመጣው የነፍስ ማቆያ እርዳታ ለጥቂት ጊዜ እንቆይ ይሆናል እንጂ ችግራችን በመሰረታዊነት ሊቀርፍልን አይችልም ያሉ ሲሆን ፤ በዋናነት ችግሩ የሚቀረፈው አከባቢያቸው ነጻ ሆኖ ወደቀያችን ሲመለሱ መሆኑን ገልፀዋል።

መንግስት ለአከባቢው #ትኩረት ሰጥቶ ማህበረሰቡን ሊታደግ ይገባል ሲሉ ጥሪ ማቅረባቸውን ከዋግኽምራ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Waghimra በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ያሉ ተፈናቃዮች የከፋ ችግር ላይ መውደቃቸው ተገልጿል። አስተዳደሩ ዛሬ ባሰራጨው መልዕክት " ዋግ ከችግር ቆፈን ላይ ወድቃለች፤ የመከራ ቃፊር እየናጣት ነው የሚደርስላት ትሻለች " ብሏል። አሁን ላይ ከአበርገሌ፣ ከጻግብጂ፣ ከዝቋላ፣ ከሰቆጣ ዙሪያ፣ ዛታ፣ ወፍላና ኮረም በጦርነት ምክንያት በየቀኑ ከ2000 ሰው በላይ የተፈናቀለ ወለህ ሜዳ ላይ ሰፍሯል…
#Waghimra📍

የሰሜን ጦርነት ክፉኛ ከጎዳቸው አካባቢዎች መካከል የአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋነኛው ነው፤ በዛ ስላለው አስከፊ ሁኔታ ከዚህ ቀደም መገለፁ የሚታወስ ነው።

አሁንም ግን ችግሩ መፍትሄ ሳይገኝለት የቀጠለ ሲሆን በተላይ ደግሞ ህፃናት አልሚ ምግብ ባለመኖሩ የተነሳ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል።

ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ለቢቢሲ በሰጠው ቃል ፤ በምግብ እጥረት የተጎዱ ሕጻናትን ጤናና ህይወት ለመታደግ የሚያስችል ድጋፍ በአስቸኳይ ማግኘት ካልተቻለ አስከፊ ነገር ሊከሰት እንደሚችል አስጠንቅቋል።

የብሔረሰብ አስተዳደሩ የኮሚኒኬሽን ኃላፊ ከፍያለው ደባሽ ፦ " አሁን ሕፃናት አፋቸውና አፍነጫቸው ቆስሏል። እንደተላላፊ በሽታ ይህ እያደገ ይሄድና ከ77ቱም የበለጠ እልቂት ሊኖር ይቸላል። ምግብ የሌላቸው ሕፃናት በሽታ ሲጨመርባቸው የሚከሰተው ችግር ቁልጭ ብሎ የሚታይ ነው " ብለዋል።

በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አብዘኛው ቆላማ ወረዳዎች በድርቅ በመጎዳታቸው፣ በቂ የሰብል ምርት ባለመኖሩ እንዲሁም በርካታ አካባቢዎች በህወሓት ቁጥጥር ሥር ስለነበሩ ከ61 ሺ 600 በላይ ተፈናቃዮች ይገኛሉ።

ከተፈናቃዮቹ መደበኛ እና መደበኛ ባልሆነ መጠለያ ውስጥ የሚገኙት 18 ሺህ 700ዎቹ ሲሆኑ በመደበኛ መጠለያ የሚገኙት ከ2 ሺህ አይበልጡም ፤ የተቀሩት ተፈናቃዮች ግን ከመጠለያ ውጪ ነው የሚገኙት።

ለተፈናቃዮች አስፈላጊውን ማኅበራዊ አገልገሎት በበቂ ሁኔታ ማቅረብ አለመቻሉንም የብሄረሰብ አስተዳደሩ አመልክቷል።

ነዋሪዎችና ተፈናቃዮችም ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ችግሩ እየባሰ መሆኑን ጠቅሰው፣ መንግሥትና የእርዳታ ድርጅቶች ለሕጻናት ልጆች እና ለእነሱም ህይወት መቆየት የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ተማፅነዋል።

@tikvahethiopia