TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አረንጓዴ_አሻራ #ከፍተኛ_ጥንቃቄ_ይደረግ

ፌስታሉን ካልሰበሰብነዉና ካላነሳነዉ ሌላ ዘመቻ ያስፈልገናል 200 ሚሊዮን ፌስታል ለመልቀም ~ የሚተክል ያስተዉል፤ ጉዳዩ ጥንቃቄ ያሻዋል!!

#ሼር #share

Via #ዝንቅ
ፎቶ: ፋይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአማራ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ህዝቦች የጋራ የሰላምና የልማት መድረክ በአሶሳ ሊካሄድ መሆኑ ተገለፀ። የአማራ ብሄራዊ ክልል እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መድረክ ባለፉት ዓመታት በሁለቱ ክልል #ከፍተኛ አመራሮች እየተመራ መቆየቱ ይታወቃል። የሁለቱ ክልል የጋራ የሰላምና የልማት መድረክ ነገ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ ከተማ የሚካሄድ ይሆናል። በመድረኩ የሁለቱ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን የሚገኙ ሲሆን በጋራ ስምምነቱ የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም ለቀጣይ ስራዎች የጋራ ውይይት ይካሄዳል። የአማራ ክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችን ያካተተ የሉኡካን ቡድን ዛሬ አሶሳ ከተማ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።

Via የክልሉ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#REPOST አዲሶቹ የብር ኖቶች አይነት እና የደህንነት መጠበቂያ ምልክቶች ፦ ተከታታይ ቁጥሮች ፦ የገንዘቡ ቁጥሮች በሚያጎላ ማሽን ሲታዩ ከጥቁር ወደ አረንጓዴ ፍሎረሰንት ቀለም ይለወጣሉ። ማየት ለተሳናቸው እውቅና ምልክት ፦ የብሩን ዋጋ የሚገልፅ ማየት የተሳናቸው በእጅ ዳሰሳ ማወቅ የሚችሉበት የደህንነት መጠበቂያ ምልክት አለው። ጎርባጣ መስመሮች ፦ የባንክ ኖቱ ሲዳሰስ የመጎርበጥ ስሜት እንዲሁም…
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ_እያደረጋችሁ !!

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ በአሽፋ ባህራ ደረዋ ቀበሌ ሃሰተኛ 80 ሺህ ባለ መቶ የብር ኖት እጅ ከፈንጅ ተይዞ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት፥ እንጅባራ ነዋሪ የሆኑት አቶ ያረጋል ጥላሁን እና አቶ ግርማው ታፈረ በቀን 28/01/2013 ዓ/ም ከቀኑ 12፡00 አሽፋ ገበያ ሃሰተኛ ብር ይዘው ሲንቀሳቀሱ የተገኙ መሆናቸውን ገልጿል፡፡

በአሁን ሰዓት አንድ ግለሰብ ከ 15,000 ብር በላይ ይዞ መገበያየት ስለማይቻል እነሱ የሚገዙት እቃ 80 ሺህ ብር ስለሆነባቸው በእጅ እንስጥ ብለው በባጃጅ ወጥተው ከመንገድ እንደተቀባበሉት ተገልጿል።

60,000 ብሩ ወዲያውኑ የተያዘ ሲሆን 20,000 ብሩ በዛሬ 29/01/2013 ዓ.ም ደላላ የሆነው ሙሉቀን አለነ የተባለ ግለሰብ አምጥቶ አስረክቧል ተብሏል።

ሁሉም ማህበረሰብ በአሁኑ ሰዓት አዲስ የተቀየረውን የብር ኖት እንዳይጭበረበር ስለብር ኖቶቹ በደንብ አውቆ መንቀሳቀስ እንዳለበት መልዕክት ተላልፏል፡፡

(Guagusa Shikudad Communication)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#REPOST አዲሶቹ የብር ኖቶች አይነት እና የደህንነት መጠበቂያ ምልክቶች ፦ ተከታታይ ቁጥሮች ፦ የገንዘቡ ቁጥሮች በሚያጎላ ማሽን ሲታዩ ከጥቁር ወደ አረንጓዴ ፍሎረሰንት ቀለም ይለወጣሉ። ማየት ለተሳናቸው እውቅና ምልክት ፦ የብሩን ዋጋ የሚገልፅ ማየት የተሳናቸው በእጅ ዳሰሳ ማወቅ የሚችሉበት የደህንነት መጠበቂያ ምልክት አለው። ጎርባጣ መስመሮች ፦ የባንክ ኖቱ ሲዳሰስ የመጎርበጥ ስሜት እንዲሁም…
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ_እያደረጋችሁ !

በደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ የሐሙሲት ፖሊስ ጽ/ቤት በዛሬዉ ዕለት 46,000 (አርባ ስድስት ሽህ ብር) ሀሰተኛ የብር ኖት መያዙን ገልጿል።

የሐሙሲት ፖሊስ ጽ/ቤት እንደገለፀው ፥ ነዋሪነቱ ዛራ ቀበሌ የሆነ ግለሠብ "ግብይት ከፈፀምኩ በኋላ የብር ኖቱን ተጠራጠርኩ' በሚል ወደ ፖሊስ ጣቢያ አምጥቶ ዛሬ ከጧቱ 2:10 ሰዓት ብሩን ለፖሊስ አስረክቧል።

ግለሠቡ በቁጥጥር ስር ዉሎ በምርመራ እየተጣራ መሆኑንም የሐሙሲት ፖሊስ ፅህፈት ቤት አሳውቋል።

ህብረተሠቡ ሀሰተኛ በሆኑ የብር ኖቶች እንዳይሸወድ እንዲሁም ሀሰተኛ የሆኑ የብር ኖቶችን የሚያዘዋዉሩ ግለሠቦችን በመጠቆሞና በማጋለጥ ወንጀልን በጋራ እንዲከላከል ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ_እያደረጋችሁ!

ምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻክል ወረዳ አማኑኤል ከተማና ደጋሰኝን ታዳጊ ከተማ መስከረም 28 እና ጥቅምት 2/2013 ዓ.ም ወደ ገቢያ ሊሰራጭ የነበረ 24 ሺ 8 መቶ ባለ መቶ የሀሰተኛ የብር ኖት በህብረተሰቡ በተደረገ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉን የማቻክል ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ዛሬ ገልጿል፡፡

ፖሊስ በድርጊቱ ተሳትፈዋል ያላቸውን ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ከማቻክል ወረዳ ኮሚኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የማቻክል ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ኮማንደር አምሳል ሰውነት ከብር ኖት ቅያሬው ጋር ተያይዞ በወረዳው ውስጥ የሀሰተኛ የብር ኖት እየተሰራጨ ስለሆነ ህብረተሰቡ ግብይት በሚፈጽምበት ወቅት ጥንቃቄ እንዲያደርግና አጠራጣሪ ነገሮችን ሲያይ ለህግ አካላት ጥቆማ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ_እያደረጋችሁ !

(ጎንደር ኮሚኒኬሽን)

በጎንደር ከተማ ውስጥ ከ31,000 ብር በላይ ሃሰተኛ የብር ኖት በቁጥጥር ስር መዋሉ የ3ኛ ዋና ፖሊስ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

ሃሰተኛ የብር ኖቶች የተያዙት በከተማ አስተዳደሩ በማራኪ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ኮሌጅ ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው።

ሃሰተኛ የብር ኖቶች በፀጥታ ሃይል በተደረገ ክትትል ትላንት ጥቅምት 9 ቀን 2013 ከጧቱ 2 ስዓት ላይ መያዙ ተገልጿል።

የድርጊቱ አስፈፃሚዎች እንዲሁም ተባባሪዎቻቸው ፖሊስ እየተከታተላቸው መሆኑ በማወቃቸው በመታተም ላይ የነበረ ፦
• 27 ሺህ ብር አዲሱ ባለ 200 የብር ኖት
• 4 ሺህ 600 ብር ነባሩ ባለ 100 የብር ኖቶችን በባጃጅ በመጫን ከወሰዱ በኃላ ውሃ ቦይ ላይ ጥለው አምልጠዋል።

የድርጊቱ አስፈፃሚዎችና ተባባሪዎቻቸውም በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ ክትትል እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

ሃሰተኛ የብር ኖቶች የሞባል ካርድ በመግዛት ፣ ምግብ ቤት በመጠቀም እንዲሁም የሱቅ ሸቀጣሸቀጦችን በመግዛት እያዘረዘሩ በመሆኑ ህብረተሰቡ ሃሰተኛ የብር ኖት ሲያጋጥም ተጠያቂ ከመሆን በፊት ለፓሊስ ሊጠቁም እንደሚገባ ፖሊስ አሳስቧል።

በህገ ወጥ መንገድ እየተመረተ ያለው ሃሰተኛ የብር ኖቶች ከአዲሱ የብር ኖቶች ጋር ተመሳሳይ በመሆናቸው እና በሁሉም የብር ኖቶች ዓይነቶች ሃሰተኛ የብር ኖቶች እየተሰሩ ወደ ገበያ ውስጥ እየገቡ በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዳይታለል መልዕክት ተላልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ_አዲስ_አበባ😷

በየዕለቱ ከፍተኛው የኮቪድ-19 ሞት ሪፖርት እየተደረገ የሚገኘው ከአዲስ አበባ ከተማ ነው።

ለአብነትም ፦

- ዛሬ የካቲት 11 በሀገር አቀፍ ደረጃ ሪፖርት ከተደረገው የ12 ሰዎች ሞት ፤ 11ዱ ሰዎች ከአዲስ አበባ ናቸው።

- የትላንት ሪፖርት የከተማው አስተዳደር ጤና ቢሮው አላሰራጨም።

- የካቲት 9 በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተመዘገበው 14 ሞት 12ቱ ሰዎች ከአዲስ አበባ ናቸው።

- የካቲት 8 በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተመዘገበው 15 ሞት 11ዱ ሰዎች ከአዲስ አበባ ናቸው።

በየዕለቱ የሟቾች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። እጅግ በርካታ ሰዎችም በፅኑ ታመዋል ፤ በርካቶችም የመተንፈሻ መሳሪያ ማግኘት ባለመቻላቸው ከፍተኛ ስቃይ እያጋጠማቸው/ህይወታቸውንም እያጡ ነው።

ውድ አባላት በየትኛውም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑ ሳትዘናጉ እራሳችሁን እና ቤተሰቦቻችሁን ከዚህ አስከፊ ወረርሽኝ እንድትጠብቁልን አደራ እንላለን።

#Purpose #TikvahFamily

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ_እያደረጋችሁ !

በአዲስ አበባ ከባእድ ነገሮች ጋር ተቀላቅሎ ለገበያ ሊቀርብ የነበረ ከ3 ሺህ 300 ኪሎ ግራም በላይ ቅቤ፣ 480 ኩንታል በርበሬ፣ 1 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ ለቂቤ መከለሻ የሚውል የአትክልት ቅቤና የፓልም ዘይት እንዲሁም 6 መቶ ኪሎ ግራም ማር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታውቋል።

በአራት ክፍለ ከተሞች (በአዲስ ከተማ ፣ ቂርቆስ ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ፣ እና ኮልፌ ቀራንዮ) ኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ሲያካሂድ በነበረው ክትትል በዚህ ህገወጥ ድርጊት ላይ የተሳተፉ በ24 ድርጅቶች ላይ እርምጃ በመውሰድ ተሳታፊ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉ ተገልጿል።

በቁጥጥሩ ወቅት ቅቤን ለመከለስ አገልግሎት የሚውሉ የአትክልት ቅቤ፤ ፓልም ዘይት እንዲሁም በርበሬ ለመከለስ የሚሆን ከደረጃ በታች የሆነ ለሰው ምግብነት የማይውል የበርበሬ ተረፈ ምርት፤ የሻገተ በርበሬ ተገኝቷል።

በተጨማሪም ቤቶቹ ለምግብ ማምረት ስራ ፍቃድ የሌላቸው እና ከፍተኛ የሆነ የንፅህና ጉድለት ያለባቸው መሆኑ ተረጋግጧል።

ህብረተሰቡ በበዓላት ወቅት ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ያለው ባለስልጣኑ አጠራጣሪ ነገር ሲገጥም በነፃ የስልክ መስመር 8482 ላይ በመደወል ጥቆማ ማድረስ ይቻላል ተብሏል።

ምንጭ ፦ ኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ

ኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የሚሞቱባት ዜጎቿ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ ፣ የቫይረሱ ተጋላጮችም በእጅጉ እየጨመሩ ይገኛል።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 6,198 የላብራቶሪ ምርመራ 1,130 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ 19 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

ትላንት 1,492 ሰዎች አገግመዋል። አሁን ላይ 945 ሰዎች በፀና ታመዋል።

በአጠቃላይ 256,418 ሰዎች እስካሁን በቫይረሱ የታየዙ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 3,658 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 197,916 ሰዎች አገግመዋል።

#Purpose

@tikvahethiopia
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ

በኢትዮጵያ ከኮቪድ-19 ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ወደ 200 ሺህ ተጠግቷል።

ትላንት 946 ሰዎች ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 198,862 ደርሰዋል።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 6,156 የላብራቶሪ ምርመራ 1,024 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ 30 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

በአጠቃላይ 257,442 ሰዎች እስካሁን በቫይረሱ የታየዙ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 3,688 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው 54,890 ሰዎች ሲሆኑ 962 ሰዎች በፀና ታመዋል።

ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ከወዲሁ እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን ፤ በበዓል ግብይት ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እናስታውሳችኃለን።

በየትኛውም ቦታ ስትንቀሳቀሱ ማስክ ማድረግ፣ አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣ የእጃችሁን ንፅህና መጠበቅ እንዳትዘነጉ።

የበሽታው ምልክት ያለባችሁ/እራሳችሁን የምትጠራጠሩ ደግሞ ከቤታችሁ ባለመውጣት ወይም እራሳችሁን በመለየት ለሌሎች ሞት ምክንያት ላለመሆን የተቻላችሁን ሁሉ ጥንቃቄ እንድታደርጉ አደራ እንላለን።

ከወዲሁ እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ

የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤት፤ ጅዳ #ለኢትዮጵያውያን የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፏል።

ለፅ/ቤቱ ከትላንት ምሽት ጀምሮ እየደረሱ ባሉት መረጃዎች መሠረት የሳዑዲ የፀጥታ አስጠባቂ አካላት ፦
- በጄዳ ፣
- መዲና ፣
- ጂዛን እና መካ ከተሞች ላይ የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ዜጎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ ይገኛሉ።

በዚህም ምክንያት ጉዳዩ እስኪጣራ ኢትዮጵያውያን ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፏል።

በሳዑዲ አረቢያ በተጠቀሱት ከተሞች የምትገኙ የቲክቫህ አባላት በሙሉ የቆንስላ ጽህፈት ቤቱን የጥንቃቄ መልዕክት #በአፅንኦት እንድትወስዱ ፣ እራሳችሁን እንድትጠብቁ ፤ ጥንቃቄም እንድታደርጉ አደራ እንላለን።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ጥንቃቄ

በደቡብ አፍሪካ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ የተዘረፉ ንብረቶችን የሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊት ከተለያዩ የሕግ አካላት ጋር በመሆን ለማስመለስ እየሰራ ይገኛል።

በመሆኑም ግጭቱ በተነሳባቸው አካባቢዎች መውጫ እና መግቢያ ላይ #ከፍተኛ_ፍተሻ እየተደረገ ይገኛል።

በቦታው ላይ ያላችሁ ኢትዮጵያውያን ይህንን ተረድታችሁ የንግድ እቃ ዝዉዉር ማድረግ ስትፈልጉ ቀድችሁ ለሚመለከተው ህጋዊ አካል ማሳወቅ እንዳትዘነጉ። አልያም እቃው የተገዛበት ህጋዊ የሆነ የግዢ ደረሠኝ በእጃችሁ መያዛችሁን እርግጠኛ ሁኑ።

በየትኛዉም ቦታ በሚደረግ ፍተሻ የህግ አካላት ከደረሰኝ ውጭ የተያዙ እቃዎችን ህገ ወጥ የሆኑ መረጃ የሌላቸዉ በሚል ገቢ ያደርጋሉ።

አስቤዛም ሲያደርጉ ደረሰኝ አለመጣሎን ያረጋግጡ በየትኛዉም ወቅት ሊከሰት የሚችል ዝርፊያ ስለሚኖርም ጥንቃቄ አይለዮት።

Video Credit : Umhlanga Rocks, KZN (ኩዋዙሉ ናታል ዋናዉ መንገድ)

Faya (Tikvah-family )
Limpopo
South Africa

@tikvahethiopia
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ🚨

በሰሜን ሸዋ ዞን ውጊያ በተካሄደባቸው አካባቢዎች የወዳደቁ ያልፈነዱ ጥይቶችና ፈንጆች በህጻናት ላይ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን የደብረ ብርሃን ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታውቋል።

ሆስፒታሉ የአካባቢው ማህበረሰብና አመራር ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።

የደብረ ብርሃን ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ አስማረ ሳሙኤል፥ኤፍራታና ግድም ወረዳ አጣዬ አካባቢ በውጊያ መሃል ያልፈነዱ ጥይቶች በእርሻ ቦታዎች ወድቀው እየተገኙ መሆኑን ጠቁመው ከትናንት በስተያ 4 ታዳጊ ወጣቶች ማሳ ውስጥ የወደቀ ጥይት ፈንድቶባቸው እግራቸውና እጃቸው ላይ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ሁለቱ በደ/ብርሃን ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ሲሆን ሁለቱ ከሆስፒታሉ አቅም በላይ በመሆኑ ሪፈር መባላቸውን ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ዛሬ ከጀቦሃ አካባቢ አንድ የ13 ዓመት ልጅ መጫወቻ መስሎት የወደቀ ጥይት አንስቶ ሲቀጠቅጥ በተከሰተ ፍንዳታ 3 ጣቶቹ ተቆርጠው በሆስፒታሉ እየተረዳ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታሉ ክትትል እየተደረገላቸው ላሉ ተጎጂዎችም አስፈላጊው ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ዶ/ር አስማረ ሳሙኤል፦

• ህወሓት መሽጎባቸው የነበሩ አካባቢዎችና የወዳደቁ መኪናዎች ላይ የተለዬ ጥንቃቄ ያስፈልጋል።
• ወቅቱ የሰብል መሰብሰቢያ ወቅት በመሆኑ በእርሻ ቦታዎች አርሶ አደሩ በጥንቃቄ ምርቱን ሊሰበስብ ይገባል።
• በየአካባቢው ያሉ አመራሮችና የጸጥታ አካላት ህብረተሰቡን ማንቃትና አካባቢውን መፈተሽ አለባቸው።
• ወላጆች ልጆቻቸው ማንኛውንም የወደቀ ነገር አንስተው እንዳይቀጠቅቱ ሊመክሩ ይገባል።
• በአካባቢው ላይ በየማሳው የድሽቃ፣የሞርተርኛ ሌሎችም ጥይቶች የወዳደቁ በመሆኑ በባለሙያዎች ለቀማ ሊደረግ ይገባል ብለዋል።

@tikvahethiopia
#ALERT🚨

በሀገራችን ኢትዮጵያ በአንድ ቀን 5,013 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገው 14,027 የላብራቶሪ ምርመራ 5,013 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓት የ6 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።

193 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ከፍተኛ_ጥንቃቄ

@tikvahethiopia
#ከፍተኛ_የደም_እጥረት_ተከስቷል !

በብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎት የደም ለጋሾች ዘርፍ አገልግሎት ዳይሬክተር ዶክተር ተመሥገን አበጀ ፦

" በአገሪቱ ያሉት የሁለቱ ትላልቅ ሃይማኖቶች ተከታዮች ፆም ላይ መሆናቸውን ተከትሎ በመላ አገሪቱ ከፍተኛ የደም እጥረት ተከስቷል።

በአገሪቱ ያለውም የመጠባበቂያ ደም ክምችት ከ5 ቀናት የማይበልጥ ነው።

በአገር ደረጃ ሲታይ ከፆም በፊት በዚህ ዓመት የነበረው የደም ክምችት አመርቂ የሆነበት ዓመት ነበር ብሎ መውሰድ ይቻላል።

የዐቢይና ረመዷን አፁዋማት ከገቡ በኋላ የመደበኛ ደም ለጋሾችም ሆነ ሌሎች ለጋሾች ቁጥር አሽቆልቁሏል።

ይህም የደም ክምችት ላይ ከፍተኛ እጥረት እንዲፈጠር አድርጓል።

በተለይ እንደ ፕላትሌት የደም ተዋፅዖ እና ‘ኦ’ የደም ዓይነት ክምችቶች እጥረት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።

ፕላትሌት የሚባለው የደም ተዋፅዖ ለካንሰር ታማሚዎች እና የደም መፍሰስ ችግር ላለባቸው ታካሚዎች የሚሰጥ የደም ዓይነት ነው፤ ክምችቱ ለአንድ ቀን ብቻ ሲሆን ‘ኦ' የተባለው የደም ዓይነትም በዛ ቢባል ለ2 ቀናት የሚሆን ክምችት ነው ያለው "

ያንብቡ : https://telegra.ph/EPA-04-19-2

#EPA

@tikvahethiopia
#WFP #Ethiopia

የግጭት ማቆም ውሳኔ ይፋ ከተደረገበት ከመጋቢት ወር ጀምሮ ወደ ትግራይ ክልል ከሚገባው እርዳታ #ከፍተኛ መጠን ያለው ቁሳቁስ በዚህ ሳምንት ወደ ክልሉ መግባቱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል።

በዚህ ሣምንት ወደ ትግራይ የገባው 15 ሺህ ቶን ምግብ እና ሌሎች የነፍስ አድን አቅርቦቶች ሲሆን አሁንም ተጨማሪ እርዳታ ወደ ክልሉ እያመራ መሆኑን WFP ገልጿል።

ኤድሪያብ ቫን ደር ክናፕ (በዓለም ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ቢሮ ኃላፊ) ፥ " ፍጥነቱ አሁን እየጨመረ ስለሆነ በዚህ ወር መጨረሻ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ 30 ሺህ ሜትሪክ ቶን ምግብ እና የምግብ ሸቀጦች ወደ ትግራይ ይደርሳል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ። እቅዳችን በሰኔ ወር መጨረሻ 100 ሺህ ቶን ምግብ ለማድረስ ነው " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ የረድኤት ድርጅቶች አፋርን ጨምሮ በአጎራባችን ክልሎች ቀውሶች እየተባባሱ በመሆናቸው እጅ እያጠራቸው ፤ የእርዳታ ክምችታቸውም እየተመናመነ መሆኑን ጠቁመዋል።

የዩክሬን ጦርነት እና ሌሎችም በዓለም ዙሪያ የታዩት ቀውሶች የለጋሾችን የረድዔት አቅም እየቀነሰው መሆኑ የታገለፀ ሲሆን WFP በሚቀጥለው 6 ወራት ውስጥ በኢትዮጵያ ለሚያስፈልገው የእርዳታ አቅርቦት የ522 ሚሊዮን ዶላር እጥረት እንደሚያጋጥመው ገልጿል።

ከዚህ ውስጥ 220 ሚሊዮን ዶላር ትግራይን ጨምሮ በሰሜን የኢትዮጵያ ክፍል ለሚሰራው የረድኤት ስራ የሚውል ነው።

ኤድሪያብ ቫን ደር ክናፕ ፤ " ያለን ክምችት በጣም በፍጥነት እያለቀ ነው። ስለዚህ ስጋታችን ይህን አውንታዊ ድባብ ፈጥረን እነኚህን መተላለፊያዎች ከፍተን መልሰን ማቆም ሊኖርብን ነው እናም ሁሉ ነገር ከሚያዚያ በፊት ወደነበረው ስፍራ ሊመለስ ነው " ብለዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/VOA-05-21

@tikvahethiopia