TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
በጣልያን ኢምባሲ መኖር ከጀመሩ 26 ዓመት ያስቆጠሩት የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣናት👇
የደረግ ባለስልጣናቱ እንዴት ጣልያን ኤምባሲ ገቡ ?

(በ2017 በቲክቫህ ኢትዮጵያ ላይ የወጣ አጭር ፅሁፍ)

© #ViceNews #ጋዜጠኛ_ደረጄ_ኃይሌ

ነገሩ እንዲህ ነው ኢትዮጵያን ለ7 ቀናት ያስተዳደሩት ሌ/ጀነራል ተስፋዬ ገ/ኪዳን ወይም 'የተስፋዬዎች መንግስት' ሀገሪቷን መቆጣጠር ሲሳነው ይሸሻል።

ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ሀገሪቷን በተቆጣጠረበት እለት አንዳንዱ የደርግ ባለስልጣን ከሀገር ይወጣል ወደ 13 የሚጠጉ ባለስልጣናት ደግሞ የጣልያንን በር ያንኳኳሉ ጣልያንም አላሳፈረቻቸውም ኑ ግቡ ትላቸዋለች።

ከገቡት መካካል አንዳንዱ ወዲያው ወጣ ሌላውም ጥቂት ቀናትን ቆይቶ ወጣ። ካልወጡት መካከል ግን ድፍን 26 ዓመት (ይህ ፅሁፍ በወቅቱ ሲፃፍ 2017 ነበር) ሙሉ በኤምባሲው ውስጥ እየኖሩ የሚገኙት 2 ባለስልጣናት ይገኛሉ።

ሁለቱም ባለስልጣናት የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ሲሆኑ የጣልያን ህገ መንግስት የሞት ፍርድን ስለማያስፈፅም ሁለቱን የደርግ ባለስልጣናት ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፎ አልሰጠም።

የጣልያን ኤምባሲ ሰዎቹን ገፍቶ ማስወጣትም አይፈልግም።

የጣልያን መንግስትም ሰዎቹን እንደ በጎ ፍቃድ ታሳሪዎች ነው የሚቆጥራቸው።

የቀድሞ ባለስልጣናቱን 'ከሰብአዊ መብት አያያዝ' ጋር በተገናኘ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጠበቃዎች እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ይጎበኟቸዋል።

ጣልያን ኤምባሲ ከገቡት እንዲሁም ገብተው ከወጡት መካከል ሜጀር ጀነራል ስዩም መኮንን (በማረፊያ ቤት ህይወታቸው አልፏል) ፣ ወሌ ቸኮል ፣ ፍሲካ ሲደልል ፣ ሽመልስ ማዘንጊያ ፣ ዶ/ር አለሙ አበበ ፣ ሸዋንዳኝ በለጠ ይገኙበታል።

በአሁን ሰዓት ጣልያን ኤምባሲ ውስጥ የሚኖሩት ሁለቱ (2) ባለስልጣናት አንዱ የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የነበሩት ብርሀኑ ባየህ እንዲሁም በደርግ ስርዓት ከፍተኛ ተሰሚነት የነበራቸው ሌተናል ጀነራል ሀዲስ ተድላ (የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም) ናቸው።

ሀይሉ ይመንህ ራሳቸውን አጥፍተዋል።

ሌፍተናንት ጀነራል ተስፋዬ ገብረኪዳን የኢትዮጵያ የአንድ ሳምንት ፕሬዘደንት በብርሀኑ ባየህ እንደተገደሉ ይነገራል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia