TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#GetachewReda

ትላንት ለመጀመሪያ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የፌዴራል መንግሥት እና የህወሓት የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላት ከመከሩ በኃላ አቶ ጌታቸው ረዳ ለብሄራዊ ቴሌቪዥን (etv) ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

አቶ ጌታቸው ረዳ በጦርነት ምክንያት የተፈጠረውን የማህበራዊ ስብራትን ከማከም ጋር በተያየ ይህን ብለዋል ፦

" በመጀመሪያ ደረጃ ጎረቤቶቻችንን መምረጥ አንችልም፤ ከማንም ሰው ጋር ያለን ግንኙነት ፈለንግንም አልፈለግንም አብረን መኖራችን ስለማይቀር አብረን እስከኖርን ድረስ መከባበር መኖር መቻል አለበት።

አንዱ ፍላጎቱን ሌላው ላይ ጭኖ የሚያረጋግጠው መብት አንዱ አንዱ ላይ ፍላጎቱን ጭኖ የሚያስከብረው ጥቅም ለጊዜው ሊመስል ይችላል ግን ዘለቄታ ሊኖረው እንደማይችል ሊታወቅ ይገባል።

የተፈጠረው የማህበራዊ ስብራት (በጦርነት ምክንያት ማለታቸው ነው) እያስታወሱ እሱን ቁስል እያከኩ መኖር ከባድ ነው የሚሆነው መጠየቅ ባለብን መጠየቅ አለብን ፤ መጠየቅ ያለበት ሰው መጠየቅ መቻል አለበት ፤ እኔ በዚህ እንቅስቃሴ ውስጥ ያጠፋሁት ጥፋት ካለ ልጠየቅ እችላለሁ።

ዞሮ ዞሮ ማህበረሰቦቻችን በሰላም ወጥተው የሚገቡበትን ሁኔታ መፍጠር፡ አለ የሚባለውን ልዩነትን በሰላማዊ መንገድ መፍታት መቻልን መማር አለብን ።

ስብራቱን ለመጠገን ሙሉ ቁርጠኝነት ይዘን ካልተንቀሳቀስን በስተቀር ቁስል እያከክ ቁስል መረሳት የለበትም ግን ቁስሉን እያከኩ መኖር አይደለም መፍትሄ የሚሆነው ይሄ ነገር እንዳይደገም ያሉብን ልዩነቶች ምንድናቸው ፣ እዚህ ያደረሱን ነገሮች ምንድናቸው የሚለውን በደንብ ተንትኖ ይሄ ነገር የማይደገምበት ሁኔታ መፍጠር አስፈላጊ ነው። "

@tikvahethiopia
#GetachewReda #AntonyBlinken

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአዲስ አበባ የስራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ከህወሓት አመራሮች አንዱ ከሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

አቶ ጌታቸው ረዳ አዲስ አበባ ላይ ከብሊንከን ጋር መገናኘታቸውንና ስለ ሰላም ስምምነቱ አተገባበር እድገት እና ስላሉት እንቅፋቶች ዙሪያ መምከራቸውን ገልጸዋል።

አቶ ጌታቸው ፤ በውይይቱ ወቅት #ለሰላም ያላቸውን የማይናወጥ ቁርጠኝነት እንዲሁም ሰላምን ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች የሚፈጥሩትን ተግዳሮቶች ለመወጣት በእነሱ በኩል ያላቸው የማያወላዳ ቁርጠኝነት እንዳረጋገጡ ገልጸዋል።

" ጊዜያዊ አስተዳደር መመስረትን ጨምሮ በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን ስቃይ ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረት ሁሉ እንቅፋት የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት የበኩላችንን ለመወጣት ዝግጁ ነን " ሲሉም ገልፀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ከብሊንከን ጋር በነበረው ውይይት በትግራይ ውስጥ እና በትግራይ ላይ በተደረገው ጦርነት ለተፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂነትን ማረጋገጥ አስፈላጊት ላይ ሃሳባቸውን እንዳካፈሉ አመልክተዋል።

አቶ ጌታቸው፤ ጠንካራ የሽግግር የፍትህ ማእቀፍ ተቀባይነት ያለውና የሚያስመሰግን ቢሆንም በትግራይ ለተፈፀሙ ወንጀሎች ተጠያቂነት ከሀገራዊ ማዕቀፍ የዘለለ በመሆኑ ዓለም አቀፍ ጥረቶች አስፈላጊ ናቸው የሚል አቋማቸውን እንደገለፁ አስረድተዋል።

አንቶኒ ብሊንከን በበኩላቸው ፤ ሀገራቸው አሜሪካ የሰብአዊ ድጋፍን ለማጠናከር፣ ለመልሶ ማቋቋም ሃብት ለማሰባሰብ፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ እና በመላው ቀጣናው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ከስምምነቱ ተዋናይ ወገኖች ጋር በጋራ እንደምትሰራ በድጋሚ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

@tikvahethiopia