TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኦንላይ ትምህርት በኢትዮጵያ :

ኢትዮጵያ ለ4 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፍቃድ በመስጠት ለመጀመሪያ ጊዜ የባሉበት ትምህርትን (online Education) መስጠት ጀምራለች።

ይህ የተገለፀው ‹‹የባሉበት ትምህርት (online Education) ዘርፉን በመልካም ጎን ይቀይረው ይሆን?›› በሚል የዘርፉ ባለሙያዎች የተሳተፉበት የበይነ መረብ ውይይት በተካሄደበት ወቅት ነው።

በውይይቱ ትምህርትን በቴክኖሎጂ መደገፍ በሚቻልበት ሁኔታ እንዲሁም ሊያጋጥሙ በሚችሉ ችግሮች እና የመፍትሄ ሃሳቦች ላይ ምክክር ተደርጓል፡፡

በዚሁ ምክክር መድረክ ላይ የከፍተኛ ትምህርት ጥራና አግባብነት ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር አንዷለም አድማሴ (ፒኤችዲ) የኦንላይን ትምህርትን በተደራጀ መልኩ ለመስጠት መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መግባቱን አስረድተዋል።

አሁን ላይም ለ4 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፍቃድ በመስጠት ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የባሉበት ትምህርትን (online Education) መስጠት ጀምራለች ብለዋል። #ኢብኮ

@tikvahethiopia
#UPDATE

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል መንግሥት የ2013 ዓ/ም ተጨማሪ በጀት ሆኖ የፀደቀውን 26 ቢሊዮን ብር ከሀገር ውስጥ ባንክ በብድር መውሰድ እንዲችል የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምፅ አፀደቀ፡፡

ተጨማሪ በጀቱ በድርቅ የተጎዱ እና በግጭት የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍ እንዲሁም ኮቪድ-19 ያስከተለውን የኢኮኖሚ ተፅእኖ ለመቋቋም እና ለተለያዩ ተግባራት የሚውል መሆኑ ተገልጿል፡፡ #ኢብኮ

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

“... ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን በቂ ዝግጅት ተደርጓል” - አቶ ተመስገን ጥሩነህ

ኢትዮጵያ የምታካሂደው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፌዴራል እና የክልል የደህንነትና የፀጥታ መዋቅር በቂ ዝግጅት ማድረጋቸው ተገለፀ።

ይህን የገለፁት የብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ ናቸው።

የፌዴራል እና የክልል የደህንነት እና የፀጥታ አካላታ ግብረሐይል በወቅታዊ የሀገሪቷን ደህንነት የሚገመግም እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን የሚያስቀምጥ ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ።

በዚሁ ወቅት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ቀጣዩ የምርጫና ድህረ ምርጫ ሰላማዊ እንዲሆን በቂ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

የፌዴራል እና ክልል የፀጥታ እና ደህንነት አካላት የጋራ ግብረ ሀይል የሀገረቷን ወቅታዊ የደህንነት ሁኔታ በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሏል። #ኢብኮ

@tikvahethiopia
የአረብ ሊግ ስብሰባ እና የኢትዮጵያ ምላሽ :

የዐረብ ሊግ የተመድ ጸጥታው ም/ቤት ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ እየገነባች ባለችው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ስንብሰባ እንዲያደርግ ትላንት ባደረገው ስበባ ጠይቋል።

የሊጉ አባል አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባደረጉት ሰብሰባ የሁሉንም አካላት ፍላጎት የሚያሳካ አስገዳጅ ስምምነት ላይ መደረስ እንዳለበት አንስተዋል።

የዐረብ ሊግ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት እየተካሄደ ያለውን ድርድር አዝጋሚ ነው ሲል ገልጾታል።

ሚኒስትሮቹ በኳታር መዲና ዶኃ ባደረጉት ስብሰባ በአፍሪካ ሕብረት ስር እየተካሄደ ያለው ድርድር አዝጋሚ በመሆኑ የጸጥታው ም/ቤት በግድቡ ዙሪያ ስብሰባ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

የሊጉ ዋና ፀሀፊ አህመድ አብዱል ጌት እንዳሉት የግብፅና የሱዳን የውሃ ደህንነት ጉዳይ የዐረብ ሀገራት ደህንነት አካል መሆኑን መግባባት ላይ መደረሱን አስታውቀዋል።

የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ የዐረብ ሊግ ለሱዳን እና ለግብፅ ድጋፍ እንዳለውም ዋና ጸሐፊው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ የህዳሴው ግድብን በተመለከተ በኳታር ተወያይቶ ያሳለፈው ውሳኔ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል አሳውቃለች።

የአረብ ሊግ የግብጽ እና የሱዳንን መሰረተ ቢስ ውንጀላ ላይ ሳይመሰረት በህዳሴ ግድቡ ድርድር ዙሪያ ገንቢ ሚና መጫወት ሲገባው ሚዛናዊነት የጎደለው እና ወደ አንድ ወገን ያደለ ውሳኔ መወሰኑ ተቀባይነት እንደሌለው ገልጻለች።

ውሳኔው በቀጠናው የአባይን ወንዝ በትብብርና በዘላቂነት ለመጠቅም የሚያስችል መንገድ አለመሆኑንም አሳውቃለች።

የአርብ ሊግ አባል ሀገራት የአባይ ወንዝን አጠቃቀም እና የኢትዮጵያን ነባር አቋም በሚገባ ሊያውቁ ይገባቸዋልም ብላለች።

#ኢብኮ #አልዓይን

@tikvahethiopia
ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ ሪጅን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎትን አሰጀመረ !

በደቡብ ሪጅን የተጀመረው የ4ጂ አድቫንስድ አገልግሎት ሀዋሳ፣ ሻሸመኔ እና ቡሌ ሆራን ጨምሮ 12 ከተሞችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል።

አገልግሎቱ የኢንተርኔት እና ሌሎች በኩባንያው የሚቀርቡ አገልግሎቶች በተሻለ ፍጥነት ለማግኘት ያስችላልም ነው የተባለው።

ኩባንያው ከፍተኛ የኢንተርኔት አጠቃቀም በሚታይባቸው 103 ከተሞች የ4ጂ .ኤል.ቲ.ኢ አገልሎትን ለማሰፋፋት እየሠራ የሚገኝ ሲሆን እሰከአሁን ባደረጋቸው የኔትወርክ ማስፋፊያ ስራዎች 65 ከተሞችን ተጠቃሚ አድርጓል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሰራ አሰፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ በአዲስ አበባ ከተማ ተወሰኖ የቆየውን የ4ጂ አገልግሎት ወደ ክልሎች በማስፋፋት ለሀገሪዊ ጥቅል ዕድገት እንዲያግዝ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።

የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ከ3ጂ አንፃር በ14 እጥፍ በተሻለ ፍጥነት አገልሎት ለማገኘት የሚያሰችል እንደሚሆን ተናግረዋል።

127 ዓመት እድሜ ያለው ኢትዮ ቴሌኮም በርካታ ማሻሻያዎች በማድረግ ለደንበኞች የተሻለ አገልግሎት ለማቅረብ እየሠራ ይገኛል ብለዋል።

ኩባንያው በአጠቃላይ በመላ ሀገሪቱ 55 ነጥብ 4 ሚሊዮን ደንበኞች ሲኖሩት ከዚህ ውስጥ 25 ነጥብ 5 ሚሊዮን ያህሉ የኢንተርኔት ተጠቃሚ መሆናቸው ተገልጿል።

#ኢብኮ

@tikvahethiopia
የአማራ ክልል መንግስት #አክቲቪስቶችን አሳሰበ።

የአማራ ክልል የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ በሰጡት መግለጫ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የህወሓት ቡድን በኃይል በወረራቸው አካባቢዎች ላይ በተሰወሰደው ወታደራዊ እርምጃ ታላላቅ የሆኑ ጀብዱዎች ተፈፅመዋል ሲሉ ገልፀዋል።

ወታደራዊ እርምጃ ከተወሰደባቸው ቦታዎች መካከል ፦
- ወልድያና አካባቢው፣
- ጋይትና አካባቢው፣
- ዛሬማና አካባቢው፣
- ሰቆጣና አካባቢው፣
- ጋሸናና አካባቢው ይገኙበታል። በእነዚህ ቦታዎች ላይ በተወሰደው ወታደራዊ እርምጃ ህወሓት ከባድ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበታል ብለዋል።

ይህ ሆኖ ሳለ ግን የማህበረሰብ አንቂዎች (#አክቲቪስቶች) በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በማህበራዊ ትስስር ገፆች (የማህበራዊ ሚዲያዎች) ላይ ሽብረተኛ ተብሎ የተፈረጀውን ህወሓት ለመደምሰስ የሚደረገውን ጥረት የሚያደናቅፉ መረጃዎችን ከማሰራጨት እንዲታቀቡ አሳስበዋል። #ኢብኮ

@tikvahethiopia
ዶላር እናትማለን በማለት ወንጀል ሲፈጽሙ የተገኙ የውጭ አገር ዜጎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በአዲስ አበባ የአሜሪካን ዶላርን እናትማለን በማለት የማታለል ወንጀል ሲፈጽሙ የተገኙ ሁለት የኮትዲቯር ዜጎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የደህንነትና የፀጥታ የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል።

የውጭ አገር ዜጎቹ በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ፍላሚንጎ በተባለ ሥፍራ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የጋራ ግብረ ኃይሉ ገልጿል።

ዤያ ሼዬዣክ እና አው ማሪ የተባሉት ሁለቱ የኮትዲቯር ዜጎች ከአንድ ግለሰብ ብቻ 260 ሺህ ብር በመቀበል ሀሰተኛ የአሜሪካን ዶላር ሰርተው ለመሥጠት ስምምነት በማድረግ የማጭበርበር ሥራ ሲያከናውኑ እጅ ከፍንጅ ተይዘው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው የተገለጸው፡፡ #ኢብኮ

@tikvahethiopia
ኢትዮጵያ 7 የUN ሰራተኞችን ሀገሪቱ ለቀው እንዲወጡ አዘዘች።

የኢትዮጵያ መንግሥት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) ስር በተለያዩ ኤጀንሲዎች ውስጥ የሚሰሩ 7 የውጭ አገር ዜጎች በ72 ሰዓት ውስጥ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ ማስተላለፉን የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የኢትዮጵያን ድንበር ለቀው እንዲወጡ የታዘዙት የመንግሥታቱ ድርጅት ባልደረቦች በአገር ውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ህገ ወጥ ሥራ ሲሠሩ የተገኙ መሆናቸውም ነው የተገለፀው።

የኢትዮጵያን ድንበር ለቀው እንዲወጡ የታዘዙት ሰባት የውጭ አገር ዜጎች ፦

1. የዩኒሴፍ የኢትዮጵያ ተወካይ UNICEF ሚስ አዴል ኮደር

2. የዩኤን የተራድኦ ምክትል አስተባባሪ ግራንት ሊያቲ

3. የዩኤን የተራድኦ ምክትል አስተባባሪ ተወካይ ሚስ ጋዳ ኤልታሂር ሙዳዊ፣

4. የዩኤን የሰላምና ልማት አማካሪ ከውሲ ሳንቼሎቲ

5. የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ቢሮ ባልደረባ ሶኒ ኦኒግ ቡላ

6. የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅ/ቤት UNOCHA ምክትል አስተባባሪ ሰኢድ መሀመድ ሀርሲ

7. የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅ/ቤት UNOCHA ኃላፊ ሚስ ማርሲ ቪጎዳ ናቸው።

#ኢብኮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አሜሪካ በኤርትራ ላይ አዲስ ማዕቀብ ጣለች። የአሜሪካ ግምጃ ቤት በድረገጹ እንዳስታወቀው በሁለት የኤርትራ ባለስለጣናት እና በ4 ተቋማት ላይ ማዕቀብ ጥሏል። አሜሪካ ኤርትራ ላይ አዲስ ማዕቀብ የጣለችው በሰሜን ኢትዮጵያ ካለው ጦርነት ጋር በተያያዘ መሆኑን አሳውቃለች። እንደ አሜሪካ ግምጃ ቤት መረጃ ማዕቀቡ የተጣለባቸው ግለሰቦች አብርሃ ካሳ ነማርያም የኤርትራ ብሄራዊ ደህንነነት ቢሮ ሀላፊ እና የኤርትራ…
ኢትዮጵያ በኤርትራ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ አወገዘች።

አሜሪካ በትናንትናው ዕለት በኤርትራ መንግስት ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ኢትዮጵያ አውግዛለች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የአሜሪካ ውሳኔ በግልጽ የሚታወቁ እውነታዎችን ከግምት ውስጥ ያላስገባ ነበር ብሏል።

የአሜሪካ መንግስት የሚከተሉትን እውነታዎች ከግምት ውስጥ እንዲያስገባ መንግስት ጠይቋል፦

1. ህወሓት በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ያደረሰውን ያልተጠበቀ ጥቃት ተከትሎ ሉዓላዊት ሀገር በሆነችው ኤርትራ ላይ ሮኬቶችን ተኩሷል።

2. የኤርትራ መንግስት በግዛቱ አንድነት እና ደህንነት ላይ ለተቋጣው ጥቃት ምላሽ የመስጠት ሉዓላዊ መብት አለው።

3. የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራ ጦር ግዛቱን አልፎ መገኘቱን አስመልክቶ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ቅሬታ አለማቅረቡንም መግለጫው አስታውሷል።

እንዲህ ዓይነት ቅሬታ የማቅረብ መብት ያለው ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ብቻ እንጂ ሌላ አካል አይደለም።

4. የኤርትራ መንግስት የኢትዮጵያ መንግስት ያወጀውን የተናጥል የሰብአዊ መብት ተኩስ አቁም ተከትሎ ወታደራዊ ሀይሉን ከኢትዮጵያ ማስወጣቱም ይታወቃል።

5. የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዳይሰፍን የኤርትራ መንግስት እንቅፋት ነው ብሎ አያምንም። በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያለው የሰላም ስጋት የህወሓት ጠብ አጫሪነት እና ወረራ ነው።

የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የህወሓትን የማተራመስ ሚና አጥብቆ ለማውገዝ አለመፈለጉም የሽብር ቡድኑን አበረታቶታል ብሎ መንግስት ያምናል።

ያንብቡ : telegra.ph/ETHIOPIA-11-13 #ኢብኮ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Sidama ከነገ ጀምሮ በሲዳማ ክልል የሰአት እላፊ ገደብን ጨምሮ ሌሎች ክልከላዎች ተላለፉ። የሲዳማ ክልል ኮማንድ ፖስት ከነገ ጀምሮ ገደብ የተጣለባቸውን የሰአት እላፊ፣ የእንቅስቃሴዎች ገደብ እና ክልከላዎችን ይፋ አድርጓል። በዚህ መሰረት ፦ - ባለሁለት እግር ተሽከርካሪ ሞተር ሳይክል (ታርጋ ያለው ብቻ) አንድ ሰው ጭኖ ከጠዋት 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ…
#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚኖረውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማስቀጠል ሲባል በክልሉ የሰዎችና ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ላይ ተጥሎ የነበረው ገደብ መነሳቱ ተገልጿል።

የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሰዎችም ሆኑ ተሸከርካሪዎች ሕግና ስርዓትን አክብረው በማንኛውም ሰዓት መንቀሳቀስ እንደሚችሉ አሳውቋል።

በተለያዩ ቦታዎች ላይ ፍተሻዎች ስለሚኖሩ ማንኛውም በክልሉ የሚዘዋወር ሰው መታወቂያ መያዝ እንዳለበት ማሳሰቢያ ተላልፏል።

#ኢብኮ

@tikvahethiopia