TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#TiborNagy

አሜሪካ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ እንደማትገባ በይፋ አሳውቃለች።

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በሕወሓት አመራር መካከል ትግራይ ውስጥ ያለው ግጭት የሚያበቃውም በሁለቱ ኃይላት መሆኑን አሜሪካ ገልፃለች።

ትናንት ማምሻውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪቃ ጉዳዮች ረዳት ሚንስትር ቲቦር ናዥ እና በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሚካኤል ራይኖር ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ ስላለው ሁኔታ በስልክ ኮንፈረንስ ለጋዜጠኞች ልዩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ቲቦር ናዥ ፥ «የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ግጭቱ ፍጻሜ እንዲያገኝ፤ ሰላም እንዲሰፍን፤ ሰላማዊ ሰዎች መጠበቃቸውን ለማሳሰብ የተቻለውን ጥረት ያደርጋል» ብለዋል።

«ግጭቱን ማስቆም ያለበት ግን የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት አይደለም» ሲሉ አጽንዖት ሰጥተዋል።

* ዝርዝር መረጃው ከላይ ተያይዟል (በጀርመን ድምፅ ሬድዮ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TiborNagy

በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር የሆኑት ቲቦር ናጊ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ መሻሻል ቢያሳይም የሰብዓዊ እርዳታ ጉዳይ ትኩረት ሲለሰጠው ይገባል ብለዋል።

ቲቦር ናጊ ሰብዓዊ እርዳታ በሚመለከት ለBBC የተናገሩት፦

"ግጭቱ ተባብሶ በነበረበት ወቅት አንዳንድ ቁልፍ ቦታዎችን ለመቆጣጠር ፍልሚያ በሚደረግበት ወቅት የግንኙነት መስመሮች ተቋርጠው ነበር ፤ ነገር ግን በአሁን ሰዓት ወሳኝ የሚባለው ፍልሚያ ተጠናቋል።

ግጭቱ ሙሉ በሙሉ ቆሟል ማለት ግን አይደለም ፤ በዚህ ሰዓት ዋነኛው ትኩረት መሆን ያለበት ሰብዓዊ እርዳት እንዴት ወደ አካባቢው ማድረስ ይቻላል የሚለው ነው።

ተመድ እና የኢትዮጵያ መንግስት እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ያልተቋረጠ የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሳቸው ትልቅ ነገር ነው።

የዚህም ስምምነት ተግባራዊነት ደግሞ ወሳኝ ነው። እርዳታ ሰጭ ድርጅቶችም ወደ አካባቢው ለመግባት ሁኔታዎች ሁሉ ሊመቻችላቸው ይገባል።"

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia