TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
'የንፁሃን ዜጎቻችን ስደት'

በትግራይ ክልል ያለውን ወጊያ በመሸሽ ወደ ሱዳን እየገቡ ያሉ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ ነው።

አሁን ላይ ያለው ሁኔታም እጅግ አሳሳቢ ነው።

UNCHR ሰላማዊ ከሆነው ኑሯቸው ላይ ተፈናቅለው ሱዳን ለገቡት የሀገራችን ዜጎች ከሱዳን መንግስት ጋር በመሆን የህይወት አድን እርዳታ ለመስጠት እየሰራ ይገኛል።

እስከዛሬ ድረስ ባለው መረጃ ወጊያውን ሸሽተው ወደ ሱዳን የገቡ ዜጎቻችን ከ30,000 ይበልጣሉ።

በትግራይ የኢንተርኔት መቋረጥ ፣ የባንኮች መዘጋት ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት አለመኖር ፣ የመሰረታዊ አቅርቦት እጥረት መፈጠሩ በእጅጉ ዜጎቻችን ለችግር አጋልጧቸዋል።

በትግራይ ክልል ልጆቻቸውን የሚያስተምሩ፣ ዘመድ አዝማዶቻቸው ትግራይ ውስጥ የሚኖሩ እርስ በእርስ ከተገናኙ 15 ቀን ሊሆናቸው ነው።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#PMOEthiopia

የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል እያካደ የሚገኘውን "ሕግ የማስከበር እንቅስቃሴ" በብሔር ወይም በሌላ ወገንተኝነት ላይ የተቃኘ ነው የሚለውን የተሳሳተ እሳቤ አጥብቆ እንደሚያወግዝ ዛሬ ህዳር 9/2013 ዓ/ም ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

እየተካሄደ ባለው "የህግ ማስከበር ዘመቻ" የትግራይ ህዝብ የመጀመሪያው ተጠቃሚ ይሆናል ሲል በመግለጫው ላይ ገልጿል።

* የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ያወጣው መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ታሽገዋል

ዋልያ ቆዳ ፋብሪካ እንዲሁም አዲስ አበባ ቆዳ ፋብሪካ አክሲዮን ማህበር የአካባቢ እና የህብረተሰቡን ጤና የሚጎዳ ብክለት በማድረሳቸዉ ምክንያት ታሸጉ።

በአቃቂ ቃሊቲ እና በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የሚገኙት ሁለቱ ፋብሪካዎች የሚለቁት ከፍተኛ የሆነ ያልታከመ አደገኛ ፈሳሽ ቆሻሻ በአካባቢዉ ላይ ብክለት እያደረሰ እንደሚገኝ ህብረተሰቡ አቤቱታዎችን ሲያቀርብ ነበር።

የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን የአካባቢ ብክለት ኢንስፔክሽን ባለሙያዎችም በመስክ ባደረጉት ምልከታ ይህንን ማረጋገጥ ችለዋል።

ይህ መረጃ ከአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን የተገኘ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዶክተር ደብረፅዮን መግለጫ ፦

የትግራይ ክልል ፕሬዜዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ዛሬ በሰጡት መግለጫ "በሁሉም ግንባር ድል እየተቀዳጁ" መሆናቸው ተናግረዋል።

ሊያጠቃን የመጣው ኃይል በሁሉም ግንባሮች ከባድ ሽንፈት እየተከናነበ ነው የሚገኘው ያሉት ዶ/ር ደብረፅዮን በከተሞች ህዝብን እያንገላታ ይገኛል ብለዋል።

ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል ፥ "እስከ አሁን በጠላት ላይ የደረሰውን ከባድ ኪሳራ እና ሽንፈት በማጠናከር ወራሪዎችን ጠራርገን ለመደምሰስም መላእ የትግራይ ህዝብ ይዝመት" ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

ዛሬ የጦር ሀይሎች ጠ/ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ መግለጫ ሰጥተዋል።

ሠራዊቱ በሁሉም ግንባሮች ድልን እየተጎናፀፈ እንደሚገኝ ተነግረዋል።

ጄኔራል ብርሃኑ ፥ "ህወሓት እያንዳንዳቸው 2 ሺ 500 የሰው ሀይል የያዙ 11 ብርጌድ ልዩ ሀይል፣ 14 ብርጌድ የዞን ታጣቂ እና አንድ ብርጌድ ሚሊሻ ቢገነባም፣ አሁን ነፍስ አውጭኝ ላይ ይገኛል" ብለዋል።

ነጻ በወጡ አካባቢዎች የሚገኘው ህብረተሰብም ለሠራዊቱ ከፍተኛ የሆነ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ህዝቡ ሠራዊታችንን ከሁዋላው እንዲመታ ቢያስታጥቁትም ፣ ምንም ሳይተኩሱ 200 መትረየስና ክላሽ አዲኮኮብ እና ሽሬ ላይ ለሠራዊታችን እስረክቧል ብለዋል።

የህወሓት ቡድን ኮማንድ ፖስቱን እና ትኳሾቹን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቢያደርግም ሠራዊታችን ነጥሎ ለመምታት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል ሲሉም ተደምጠዋል።

"ህወሓት" አሁኑ ላይ ኢትዮጵያን ወደ ጦርነት ለማስገባት እና ሀገሪቷን ለመበታተን ያቀደው እንደከሸፈበት እና በመከበቡ ነፍስ አውጭኝ ላይ ይገኛል ብለዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Harari

በሐረሪ ክልል የሐኪም ወረዳ ፖሊስ ጽ/ ቤት ለጥፋት ዓላማ ሲዘጋጁ የነበሩ 17 ተጠርጣሪዎች ከተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና ሌሎች ቁሳቁሶች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳወቀ።

በ15ቱ ተጠርጣሪዎች መኖርያ ቤት በተደረገው ፍተሻ በርካታ የጦር መሳሪያዎች ተይዘዋል።

የጦር ሜዳ መነጽር ፣ የራዲዮ መገናኛ ፣ ፎቶ ካሜራ ፣ የጦር መሳርያ መያዣ ቁሳቁሶች ፣ 20 የሚደርሱ ሲም ካርዶች ፣ የጦር ሜዳ የመጀመርያ ህክምና መስጪያ ቁሳቁሶች ከተጠርጣሪዎቹ የተያዙ ናቸው።

በተጨማሪ የተለያዩ መታወቂያዎች፣ የባንክ ቤት ቼክና ደብተር፣ ላፕቶፖች፣ የጸረ ሽምቅ ውጊያ ማስተማሪያ መጽሃፎች እና ሌሎች ቁሳቁሶችም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

Via ENA
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#TikvahFamily

ሀሰተኛ ፎቶዎች/ምስሎችን እንዴት ልለይ ?

ሀገራችን ያለችበትን 'ከባድ ውጥረት' ሁላችንም የምናውቀው ነው። ይህን ተንተርሶ እጅግ በጣም ብዙ "ሀሰተኛ ፎቶዎች" እየተሰራጩ እንደሆነ ተመልክተናል።

ስለዚህ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚያጠራጥራችሁን ፎቶ ስትመለከቱ በቀላሉ የትኛውንም ሚዲያ ወይም ግለሰብ እንዲያጣራላችሁ ሳትጠብቁ በእጅ ስልካችሁ ማረጋግጥ ትችላላችሁ።

በቅደሚያ 'ሀሰተኛ' የመሰላችሁን ፎቶ/ምስል ወደ ስልካችሁ Save አድርጉት።

በቀላሉ ስልካችሁ ላይ "Google Chrome App" ካለ ፦
-www.google.com ግቡ
-ወደ Desktop Site ቀይሩት
-በቀኝ በኩል ከላይ Image የሚለውን ምረጡ
-የካሜራ ምልክቱን ተጫኑ የፎቶውን URL/ፎቶውን Upload አድርጉት።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#BREAKING

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን "የአገር ክህደት ወንጀል" ፈፅመዋል በተባሉ 76 ጄነራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች እና የበታች ሹማምንቶች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ እንደወጣባቸው አሳውቋል።

* የፌዴራል ፖሊስ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,871
• በበሽታው የተያዙ - 533
• ህይወታቸው ያለፈ - 13
• ከበሽታው ያገገሙ - 300

አጠቃላይ 103,928 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,601 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ፤ 64,593 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

305 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የዶክተር ደብረፅዮን መግለጫ ፦ የትግራይ ክልል ፕሬዜዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ዛሬ በሰጡት መግለጫ "በሁሉም ግንባር ድል እየተቀዳጁ" መሆናቸው ተናግረዋል። ሊያጠቃን የመጣው ኃይል በሁሉም ግንባሮች ከባድ ሽንፈት እየተከናነበ ነው የሚገኘው ያሉት ዶ/ር ደብረፅዮን በከተሞች ህዝብን እያንገላታ ይገኛል ብለዋል። ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል ፥ "እስከ አሁን በጠላት ላይ የደረሰውን ከባድ ኪሳራ…
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የዶ/ር ደብረጽዮን የዛሬ መግለጫ እና የመቐለ ሁኔታ ፦

(በዶቼ ቨለ & ድምፂ ወያነ)

ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሰጡት መግለጫ ራያ እና ሽረ በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መያዛቸውን አረጋግጠዋል።

ዶክተር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ፥ "በውጊያ መገፋፋት እንዳለ ድሮም እናውቃለን፤ አሁንም ገጥሞናል። ትላንት ጠላት ወደ ራያ እና ሽረ ገብቷል። ትግሉ አሁንም ቀጣይ ነው። ገና ነው። ውጊያ ውስጥ ነን። መገፋፋት እንዳለ ይታያል። ከነሙሉ አቅማችን ሆነን ነው ኣሁንም እየገጠምን ያለነው።" ብለዋል።

ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የህዝብ መፈናቀል መከሰቱ በትለይም በትግራይ ህዝብ ላይ ከባድ ችግር መድረሱን አንስተዋል።

ከትግራይ ጋር እየተዋጉ 'ያሉ ኃይሎች' በድሮን ጭምር ጉዳት እያደረሱ ነው ብለዋል ፤ መንግስታቸውም ሁሉን አቀፍ ትግል ማድረጉን እንደሚቀጥል በመግለጫቸው ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ፦

ከትናንት በስቲያ 'የአውሮፕላን ጥቃት' ያስተናገደችው መቐለ ትናንት እና ዛሬ መረጋጋት ይታይባታል። ሁሉም የግል እና የመንግሥት ባንኮች ተከፍተዋል።

የነዳጅ እጥረት በመኖሩ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ መቀነስ ጀምሯል። የስልክ እና የኢንተርኔት ግልጋሎቶች እንደተቋረጠ ነው።

* የዶክተር ደብረፅዮን መግለጫ ከላይ ተያይዟል 48 MB (WiFi ብቻ ተጠቀሙ)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

ዛሬ መግለጫ የሰጡት ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ የተናገሩት ፦

"የTPLF ወንጀለኛው ቡድን ህዝቡን በነቂስ ሰራዊታችንን ካለፈ በኃላ በጀርባው እንዲወጋ ሰርቶና ተዘጋጅቶ ነበር። ይሄ ሳይሳካለት ቀርቷል።

ህዝቡ ከሰራዊታችን ጋር ወግኗል።

እስከ ዛሬ ከሰራዊታችን ጀርባ ፣ ከሰራዊታችን ጎን የተኮሰ የትግራይ ማህበረሰብ የለም።

ውጊያው ቶሎ (ፈጥኖ) እንዲያልቅለት ይፈልጋል። ቶሎ ብሎ ወደሰላማዊ ኑሮው ለመመለስ ከፍተኛ ጉጉት አለው። ይህ አንዱ በጦርነቱ ውስጥ የታየ ክስተት ነው።

ሌላው ደግሞ ህዝቡ ለሰራዊቱ መረጃ እየሰጠ ነው።

ጠላት ከባድ ማሳሪያዎችን የት ነው ያስቀመጠው ? ፣ ከየት ነው የሚተኩሰው ? ወዴት ነው የሸሸው፣ ወዴት ነው ከፍተኛ ኃይል ያለው፣ ወዴት ነው የማስመሰል ኃይል ያለው የሚለውን ለሰራዊቱ መረጃ በመስጠት ሰራዊቱን እየደገፈ ወደ መሃል ትግራይ እንዲገባ ድጋፍ እየሰጠ ነው።"

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ ፦

የእስር ማዘዣ የወጣባቸው 'የህወሓት አመራሮች' በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እንዲሰጡ ተጠይቋል። የመጨረሻዎቹን እንጥፍጣፊ ዕድሎች መጠቀም እጅግ 'ከከፋው ዕጣ ፈንታ' ያድናቸውል ሲል መንግስት አስጠንቅቋል።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#AddisAbabaPolice

የፖሊስ የደንብ ልብስ በመልበስ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው "ወርቅ የሰረቁ" ተጠርጣሪዎች ከነኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

* ፖሊስ ጉዳዩን በተመለከተ የሰጠው ዝርዝር መረጃ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia