TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#CPPI #WorldBank

የዓለም ባንክ ከኤስ ኤንድ ፒ ግሎባል ማርኬት ኢንተለጀንስ ጋር የሚያዘጋጀው የኮንቴይነር ወደብ የአፈጻጸም መለኪያ (Container Port Performance Index - CPPI) የ2023 ደረጃ ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ አድርጓል።

ይህ መለኪያ ወደቦች የመረከብ አቀባበላቸውንና እንዴት እንደሚያስተናግዱ በአጠቃላይ ያላቸውን የስራ ቅልጥፍና እና አፈጻጸም የሚለካ ነው።

በዚህም ከ409 ወደቦች የራስ ገዟ #ሶማሌላንድ " #በርበራ " ወደብ 106ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የሶማሊያ ፤ " #ሞቃዲሾ " ወደብ ደግሞ 166ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የ " #ጅቡቲ " ወደብ ከመጨረሻ ተርታ 379ኛ ደረጃ ላይ ነው የተቀመጠው።

በዚህ የዓለም ባንክ የአፈጻጸም መለኪያ የበርበራ ወደብ ከሞቃዲሾ እና ጅቡቲ ወደቦች የተሻለ ደረጃ ተሰጥቶታል።

በአጠቃላይ ዓለም አቀፍ ደረጃ ከተሰጣቸው ከ405 ወደቦች በመጨረሻ ተርታ ማለትም 379 ላይ የተቀመጠው የጅቡቲ ወደብ በሀገሪቱ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል።

የጅቡቲ ወደብ በ2022 ከዓለም የተሰጠው ደረጃ 26ኛ ሲሆን በ2023 መለኪያ 379ኛ ላይ መቀመጡ ጅቡቲን አላስደሰተም።

ሀገሪቱ " የ2023 ደረጃ አሰጣጥ ምክንያታዊነት የጎደለው በመሆኑ ያሳስበናል " ያለች ሲሆን " ምን አይነት ሳይንስ ነው የሚያብራራው በዓለም ደረጃ ከ350 በላይ ነጥብ መጣል ? " ስትል ጠይቃለች።

በአንድ ዓመት ውስጥ እንዲህ ያለው ደረጃ መሰጠቱ በመለኪያው ላይ የተዓማኒነት ጥያቄ እንደሚያስነሳ ገልጻለች።

ጅቡቲ ፥ " ደረጃ አሰጣጡ ነጻ እና ከተእጽኖ የጸዳ ነው ወይ ? " ስትል ጠይቃ " ለማንኛውም አድሏዊም ሆነ አልሆነ ጅቡቲ ከሰሃራ በታች እና ምስራቅ አፍሪካ ትልቁ እና ቀልጣፋ ማዕከል ናት " ብላለች።

ሙሉ ዶክመንቱን በዚህ ያግኙ ➡️ CPPI 2023

#WorldBank

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia