TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.4K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
4 ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመገንባት የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ ነው!

አራት ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመገንባት የሚያስችል ጥናት እየተካሄደ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽን ገለጸ። ኮርፖሬሽኑ በፓርኮች ግንባታና ምርት ዙሪያ ከምሁራን፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የሙያ ማህበራት ጋር ተወያይቷል። ውይይቱ በኢትዮጵያ በመስኩ እየተካሄደ ያለው እንቅስቃሴ፣ እየተገኙ ያሉ ውጤቶችና ችግሮች ላይ ያተኮረ ነው።

የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ሺፈራው ሰለሞን እንደተናገሩት፤ አሁን ካሉት ኢንዱስትሪ ፓርኮች በተጨማሪ አራት ፓርኮችን ለመገንት የሚያስችል ጥናት እየተከናወነ ነው። አሶሳ፣ አረርቲ፣ አይሻና ሰመራ ከተሞች ላይ ለመገንባት እንደታቀደ ጠቁመው፤ በተለይ #ሰመራ ላይ #የኢትዮጵያና #ኤርትራ ግንኙነት መሻሻልን ተከትሎ የወደብ አማራጭ በመኖሩ የተሻለ እንቅስቃሴ ለማድረግ ያለመ መሆኑን አብራርተዋል።

አሶሳ ላይ ደግሞ የቀርከሃ ምርት በስፋት በመኖሩ ለቢሮ፣ ለቤት እቃዎችና መርከብ ግንባታ የሚሆን ግብዓት ለማምረት የሚያስችል የኢንዱስትሪ ፓርክ ለመገንባት እየተጠና መሆኑን ጠቁመዋል። በቀርከሃ ምርት ለመሰማራት ቻይናዊያን ባለሃብቶች ከፍ ያለ ፍላጎት ማሳየታቸውን ገልጸዋል። ”የጥናት ሂደቱ እንደተጠናቀቀ በውጤቱ መሰረት ወደ ግንባታ ይገባል” ብለዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia