TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#እገታ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ላይ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚፈፀመው እገታ መባባሱን ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል። በቅርብ ጊዜ እገታ ተፈፅሞባቸዋል ከተባሉ አካባቢዎች አንዱ የምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ነው። በዋናው የፌዴራል መንገድ ላይ ወረዳውን አቋርጠው በተሽከርካሪ ሲሄዱ የነበሩ 10 የግንባታ ባለሞያዎች በታጣቂዎች ታግተው 20 ቀናት ያህል ከቆዩ በኃላ የተጠየቁትን…
#እገታ

ከ3 ሳምንት በፊት መስከረም 20/2016 ዓ/ም ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ከባቱ ከተማ ወጣ ብሎ ወደሚገኘው የአሉቶ ጂኦተርማል ፕሮጀክት ሲጓዙ በታጣቂዎች ከታገቱት 6 ሰዎች ውስጥ 3ቱ ቢለቀቁም ሌሎች 3 ሰዎች ደግሞ እስካሁን እንደታገቱ ናቸው።

ከዚህ ቀደም ስማቸው ይፋ እድንዳይሆን ጠይቀው መረጃ የሰጡ የፕሮጀክቱ ሰራተኛ ታጋቾቹ እያንዳንዳቸው በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ እንደተጠየቀባቸው / በድምሩ የተጠየቀው 60 ሚሊዮን ብር እንደሆነ ተናግረው ነበር።

ከታጋቾቹ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ትላንት ቃላቸውን የሰጡት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሞገስ መኮንን ፤ ታጋቾቹን የማስለቀቅ ጥረት መቀጠሉን በማስረዳት እስካሁን 3ቱን ማስለቀቅ መቻሉን ተናግረዋል።

" ግማሾቹ ተለቀዋል፡፡ የተቀሩትንም ለማስለቀቅ ጥረቶች ቀጥለዋል " ያሉት አቶ ሞገስ ተለቀዋል የተባሉ 3ቱ ሰራተኞች በምን አይነት መንገድ እንደተለቀቁና የተቀሩት 3ቱ ደግሞ ለምን ሳይለቀቁ ቀሩ የሚለውን ጥያቄ ለታጋቾቹ ደህንነት በሚል ሳያብራሩት ቀርተዋል፡፡

ከእገታ ነፃ ከወጡት ውስጥ አንደኛው #ኬንያዊ እንደሆነ ጠቁመዋል።

የፕሮጀክቱ ሰራተኞች እንዲሁም የታጋች ቤተሰቦች እገታውንና የተለቀቁትን ታጋቾች በተመለከተ " ለደህንነታችን መልካም አይደለም " በማለት ተጨማሪ ማብራሪያ ለመስጠት አልፈለጉም።

ፌዴራል ፖሊስ ስለ ተስፋፋው የ #እገታ ተግባር ምን ይላል ? እገታን ለማስቀረት መንግሥት ምን እየሰራ ነው ?

የፌዴራል ፖሊስ ቃል አቀባይ አቶ ጄኢላን አብዲ ችግሩን ከመሰረቱ ለመከላከል ሰፊ የህዝብ ተሳትፎ ያሻዋል ብለዋል።

" እገታን ሰራዊት በማዘዝና ኮማንድ በመስጠት ሙሉ በሙሉ የምንከላከለው አይደለም፡፡ የሆነ ቦታ ላይ ተደብቀው እንደዚህ አይነት ድርጊት ሚፈጽሙ አካላት አሉ፡፡ " ሲሉ ገልጸዋል።

" ህዝብ ጋር ተባብረን መረጃ ስንቀበል አስቀድመን ያስቀረነውም ሆነ ያስለቀቅናቸው እገታዎች አሉ፡፡ " ያለቱ አቶ ጄይላን " ህብረተሰቡ ነው መጠቆም ያለበት እደዚህ አይነት ነገሮችን፡፡ " ብለዋል።

° ህብረተሰቡ ጥቆማዎችን በሚሰጥበት ወቅት ከአጋቾች ለሚደርስበት ጥቃት ምን ያህል የማምለጥ ዋስትና ይኖረዋል ? የጸጥታ ኃይሉ በፍጥነት የመድረስ ሁኔታ ላይ ጥያቄ አይነሳም ወይ ? የተባሉት የፌዴራል ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ፦

" ከህብረተሰቡ ራሱ ጥንቃቄ የጎደሉ አካሄዶች ይስተዋላሉ፡፡

ለምሳሌ መሬት ትገዛለህ ይህን ያህል ብር ይዘህ ና ተብለው የታገቱ አሉ፡፡ እገታ ድንገት በአጋቾች የሚፈጸም እንደመሆኑም እያንዳንዱን ነገር መከላከል አዳጋች ነው፡፡

እገታ ደግሞ ሳይጠበቅ ቶሎ የሚፈጸም ተግባር ስለሆነ ቶሎ ለመቆጣጠር አመቺ አይደለም፡፡ " ሲሉ መልሰዋል።

አቶ ጀኢላን ፤ ፖሊስ ጥቆማ ከደረሰው ቶሎ ወንጀሉ የተፈጸመበት ስፍራ በመድረስ እርምጃ ለመውሰድ ሚያስችል የተሸለ ቴክኖሎጂ አለው ያሉ ሲሆን በየስፍራው ፖሊሶችም እንዲኖሩ የሚያስችል የቁጥጥር ስርኣት መዘርጋቱን ገልጸዋል፡፡

አሁን አሁን በአደንዳዥ እፆች የሚደገፍ የእገታ ወንጀል በተለይ #በከተሞች መበራከታቸውንም ያስገነዘቡት አቶ ጀኢላን " ወንጀሉ ከተፈጸመም በኋላ በርካታ ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

እገታ በሚፈጸምበት ጊዜ ፖሊስ የራሱ ወታደራዊ ስልት የሚጠቀም ይሆናል እንጂ ከአጋጆች ጋር በምንም አይደራደርም ያሉ ሲሆን ይህን በሚያደርጉ ተቋማት ተግባር ላይ ማብራሪያ እንደማይሰጡ ገልጸዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ / ዶቼ ቨለ ነው።

@tikvahethiopia