TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የዶ/ር ደብረፅዮን መግለጫ ፦

የኤርትራ መንግስት፥ በኢ/ያ ፌደራል መንግስት እና ትግራይ ክልል መንግስት መካከል እየተካሄደ በሚገኝ ጦርነት በቀጥታ መሳተፍ ጀመረ ሲሉ የትግራይ ፕሬዝደንት ዶ/ር ደብረፅዮን ተናገሩ።

በዚህም ጦርነቱ "ወደ ተለየ ምዕራፍ ተሸጋግሯል" ብለዋል።

የኤርትራ መንግስት በትላንትናው ዕለት በትግራይ ሑመራ የከባድ መሳርያ ድብደባ መፈፀሙን ገልፀዋል።

ዶክተር ደብረፅዮን፥ በባድመ በኩልም የኤርትራ ወታደሮች ድንበር ጥሰው በመግባት ጦርነት ከፍተዋል ሲሉ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።

Via Million Hailesilase
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ መገለጫ ሰጥተዋል።

ከሽራሮ እስከ ዛላንበሳ ድረስ ያሉትን የሰሜን እዝ የጦር ክፍሎች በአሁኑ ሰዓት በጥሩ የዝግጁነት አቋም ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

ከሽራሮ እስከ ዛላንበሳ ድረስ ያሉት የሰሜን እዝ የጦር ክፍሎች በአካል አግኝተው መመለሳቸውን ገልጸዋል፡፡

ሌ/ጄኔራል ባጫ ፥ በሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈጸውን ጥቃት አስመልክተው እንደገለጹት ፣ በሠራዊቱ ውስጥ የነበሩ የህወሓት ቅጥረኞች ሦስት ተልዕኮ ተሰጥቷቸው ጥቃት ፈፅመዋል ብለዋል ፦

1ኛ. ሠራዊቱን ከውስጥ ማፍረስ፣
2ኛ. ሠራዊቱን መውጋትና
3ኛ. ማዘናጊያ የሽምግልና ስራ መስራት ስለነበር እሱን ተልዕኮ ነው የፈጸሙት ብለዋል።

ሠራዊቱን ከውስጥ ለማፍረስ የሰሜን ዕዝን የሬዲዮ መገናኛ አዲስ አበባ በሚገኘው የመገናኛ ሀላፊ አማካኝነት ወደነሱ አዙረዋል ብለዋል።

እንዲሁም መከላከያና ጦሩ እርስ በርሱ እንዳይገናኝ አድርገዋል ሲሉ ገልፀዋል።

እነዚህ አካላት የሠራዊቱን የወር ደሞዝ እና ቀለቡን ወስደውበታል፣ አዛዦችንም አፍነዋል ብለዋል።

ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ ሰራዊቱ ይህ ሁሉ ተፈፅሞበት ተዋግቷቸዋል፣ ጀግንነትም ፈፅሟል ሲሉ ተናግረዋል።

ውጊያው ከክልሉ ልዩ ሀይል ብቻ አልነበረም ያሉት ሌ/ጄኔራል ባጫ ፣ በዛላንበሳ ፣ በሽራሮ ፣ በራማ ፣ በፆረና እና በሌሎች ቦታዎች የኦነግ ሸኔ አባላት ባንዲራቸውን ይዘው አብረው ወግተውናል ብለዋል።

በስፍራው የጦር ሀይሎች ም/ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሌ/ጀኔራል አበባው ታደሰ ሠራዊቱን አብረውት እየመሩት እንደሚገኙ በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡ (ኤፍ ቢ ሲ)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የዶ/ር ደብረፅዮን መግለጫ ፦ የኤርትራ መንግስት፥ በኢ/ያ ፌደራል መንግስት እና ትግራይ ክልል መንግስት መካከል እየተካሄደ በሚገኝ ጦርነት በቀጥታ መሳተፍ ጀመረ ሲሉ የትግራይ ፕሬዝደንት ዶ/ር ደብረፅዮን ተናገሩ። በዚህም ጦርነቱ "ወደ ተለየ ምዕራፍ ተሸጋግሯል" ብለዋል። የኤርትራ መንግስት በትላንትናው ዕለት በትግራይ ሑመራ የከባድ መሳርያ ድብደባ መፈፀሙን ገልፀዋል። ዶክተር ደብረፅዮን፥ በባድመ…
#FDREDefenseForce

'የኤርትራ ወታደሮች ጥቃት እያደረሱብን ነው’ በሚል በዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል የተሰጠው መግለጫ 'ፍፁም ሃሰት' መሆኑን ሜጀር ጄነራል መሐመድ ተሰማ ገለፁ።

ሜጀር ጄነራል መሐመድ ፥ "ጁንታው በተለያዩ አጋጣሚዎች ለማደናገር ጥረት እያደረገ ይገኛል" ብለዋል።

“በቂ ተዋጊ አለኝ ፣ ሰሜን አዝ አብሮን ተሰልፏል፣ የመከላከያ ሃይሉን የጦር ጀቶች በሚሳኤል እንመታለን” የሚል ፉከራ ውስጥ ነበር ብለዋል።

‘የትግራይ ምድር ለሚዋጉን ሁሉ መቀበሪያ ትሆናለች’ የሚል ዛቻም ያሰማ እንደነበር ሜ/ጄኔራል መሀመድ ገልጸዋል።

“ያ ሁሉ ፉከራ አልሳካ ብሎ በመከላከያ ሃይሉ አከርካሪው እየተሰበረ ሲመጣ ሌላ የማደናገሪያ ሃሳብ ይዞ ብቅ ብሏል” ሲሉ ተናግረዋል። (ENA)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ100 ሺህ አለፉ።

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,360
• በበሽታው የተያዙ - 345
• ህይወታቸው ያለፈ - 7
• ከበሽታው ያገገሙ - 806

አጠቃላይ 100,327 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,537 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ፤ 61,516 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

286 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FederalPoliceCommission

የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ሜጀር ጀነራል ገብረመድህን ፈቃዱን (ወዲ ነጮ) በአገር ክህደት ወንጀል ከነ ግብረ አበሮቹ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉ ገልፀዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ጥቅምት 24/2013 የሰሜን ዕዝ ከማዕከል ጋር የሚኖረው የመገናኛ ሥርዓት እንዲቋረጥ በማድረግ "የህዋሃት የጥፋት ቡድን" ጥቃት እንዲፈፅም አመቻችተዋል ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም ሜ/ጄኔራል ገብረመድህን በውስጣቸው ቦንቦች እና የሚሳየል መሳሪያዎችን የያዙ 11 ሳጥኖች የግንኙነት መሳሪዎች ናቸው በሚል ሽፋን ወደ ትግራይ ክልል ለመላክ ሲዘጋጅ ከተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ጋር እጅ ከፍንጅ መያዙ ተገልጿል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶቻቸው በድምሩ አስራ ሰባት (17) ተጠርጣሪዎች ናቸው።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

አየር መንገዱ ኮቪድ19 ያመጣውን ቀውስ ተቋቁሞ በማለፉ እና ስኬት በማስመዝገቡ ከ “ግሎባል ፋይናንስ” መጽሔት “የ2020 Outstanding Crisis Leadership” ሽልማት ተበርክቶለታል።

ሽልማቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በወረርሽኙ ወቅት ለአለም ለሰጠው ፈጣን ምላሽ እንዲሁም ለተገበራቸው ስኬታማ የቀውስ ወቅት ስትራቴጂዎች እውቅና የሰጠ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በዛሬው ዕለት ሃገራዊ ሁኔታዎችን በማስመልከት ለውጭ መገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

“ከግጭቱ ዋዜማ የትግራይ ክልል መሪ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተደዋውለው ነበር” ያሉት ቃል አቀባዩ “ሁኔታውን በቀላሉ እንደሚይዙት እና በንግግር ሊፈቱት እንደሚችሉ ተነጋግረው ነበር” ብለዋል፡፡

ጠ/ሚሩ ይህን ታሳቢ በማድረግ በአዲስ የተቀየረውን ብር ወደ ትግራይ ለመላክ እና ክልሉ የእለት ተዕለት የቢዝነስ እንቅስቃሴ ለመደገፍ ቃል ገብተዋል፡፡

ሆኖም በዚያው ዕለት ምሽት ላይ በክልሉ በሚገኘው የሃገሪቱ ጦር የተለያዩ ጣቢያዎች ላይ ድንገተኛ ጥቃት መከፈቱ ነው የገለጹት፡፡

ጥቃቱም በተመረጡ የሰራዊቱ አካባቢዎች ላይ በተመሳሳይ ሰዓት የተፈጸመ ነው፡፡

ያንብቡ - https://telegra.ph/AlAin-11-10

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrAbiyAhmed

ጠ/ሚር ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ ምሽት በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰራጩት መልዕክት የህግ የበላይነት የማረጋገጥ ስራው ሳይጠናቀቅ ድርድር የሚባል ነገር አይኖርም ሲሉ #አረጋግጠዋል

በሌላ በኩል ፦

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር በትግራይ ክልል ያለው ግጭት በአፋጣኝ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

የፌደራሉ እና የክልሉ መንግሥት ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት ወደ ንግግር እንዲመለሱ ሊቀመንበሩ ሙሳ ፋኪ ማህማት ጠይቀዋል፡፡

ግጭቱን ለመፍታት የሚደረግን ማንኛውም ጥረት ለማገዝ የአፍሪካ ኅብረት ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።

ሀገሪቱ ወደ ዕርስ በዕርስ ግጭት ውስጥ እንዳታመራ ኅብረቱ ጣልቃ እንዲገባ የክልሉ ገዢ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ባለፈው እሁድ ጥሪ ማድረጋቸው አይዘነጋም፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጠቃሚ የስልክ ቁጥሮች #1

ከላይ ፦

1. የኦሮሚያ ክልል ከተሞች፣ ዞኖች ፖሊስ መምሪያ ስልኮች
2. በሲዳማ ክልል (ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ)
3. የአማራ ክልል የዞኖች፣ የብሄረሰብ አስተዳደሮች፣ እና ከተሞች ፖሊስ
4. የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን
5. ደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም የፀጥታ ቢሮዎችን የስልክ ቁጥሮች ማግኘት ትችላላችሁ።

* የሌሎች የከተሞች ፣ የዞኖች የፀጥታ ቢሮ ስልኮች በቀጣይነት ይቀርባሉ።

የምንኖርበትን አካባቢ የፀጥታ አካላት ስልክ ቁጥሮች በእጅ ስልካችን ላይ የመመዝገብ ባህልን እናዳብር።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

በሀገር መከላከያ ሰራዊት እየተወሰደ ያለዉን የህግ ማስከበር እርምጃ እንጂ የእርስ በርስ ጦርነት አይደለም አለ መከላከያ ሚኒስቴር።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ቀነዓ ያደታ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

'አጥፊው ቡድን' እየተወሰደ ያለውን የህግ ማስከበር እርምጃ የእርስ በእርስ ጦርነት አስመስሎ የሀሰት መረጃዎችን እየነዛ ነው ብለዋል።

ቡድኑ እያሰራጨ ያለው የሃሰት መረጃ ጭንቀቱን እና ተስፋ መቁረጡን የሚሳይ ነዉ ሲሉ ገልፀዋል።

የትግራይ እና ኢትዮጵያ ህዝብ እነዚህን የሃሰት መረጃዎችን በመለየት ከሀገር መከላከያ ሰራዊቱ ጎን መቆም አለበት ሲሉ አሳስበዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#የመከላከያ_ሰራዊቱ_ማስጠንቀቂያ

መከላከያ ሰራዊት የትግራይ ልዩ ሀይል እና የትግራይ ሚሊሻ አባላት የጥፋት ቡድኑ ከለላ ከመሆን ይልቅ ለሀገር መከላከያ እጃቸውን እንዲሰጡ አሳስቧል።

እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊት የማይሰጡ ከሆነ መከላከያው "ያለምንም ቅድመ ሁኔታ" ለመደምሰስ እንደሚገደድ በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#AddisAbaba

ዛሬ ጥዋት በአዲስ አበባ ከተማ አድዋ ድልድይ ስር ቦንብ ፈንድቶ በ1 ግለሰብ ላይ የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

* የታረመ

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የመከላከያ ሰራዊቱ በታላቅ ጥንቃቄ እና በሙያዊነት የሀገር ማዳንና ህግን የማስከበር ስራውን እየሰራ መሆኑን መከላከያ ሚኒስቴር አሳውቋል።

ሀገር መከላከያ ሰራዊቱ 'ጥፋተኛውን ቡድን' ብቻ ነጥሎ ነው እያጠቃ የሚገኘው ተብሏል።

መከላከያው ንፁሃንንና መሰረት ልማት ላይ ጥቃት ይፈፅማል እየተባለ በጥፋት ኃይሉ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው ሲል ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ የሰራዊቱ የማንንም የውጭ ኃይል ድጋፍ ሳይፈልግ የጥፋት ቡድኑን የመደምሰስ ቁመና አለው ብሏል።

"መከላከያ ሰራዊቱ የትኛውንም ጥቃት ለመመከት ተጨማሪ ድጋፍ አያስፈልገውም ፤ ቡድኑን ለማጥቃት የውጭ ድጋፍ አልጠየቀም አይጠይቅምም" ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀነዓ ያደታ ፥ "የትግራይ ህዝብ ጦርነት የሰለቸው ነው፣ ሰላምና ልማት ፈላጊ ነው ፣ ሀገሩንም አይወጋም ፣ በጠቅላላው በዚህ ጦርነት ላይ #አልተሳተፈም" ብለዋል።

ይህ ብቻም ሳይሆን የትግራይ ህዝብ ሰራዊቱ በደረሰበት ቦታ ለሰራዊቱ ያለውን ክብር በግልፅ እያሳየ እና እየደገፈ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ጦርነቱ የእርስ በእርስ ጦነርት አይደለም ፤ ጦርነቱ እየተደረገ ያለው ከጥፋተኛው ቡድን ጋር እና ህግን የማስከበር ብቻ ነው ሲሉም አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ዛሬ ጥዋት በአዲስ አበባ ከተማ አድዋ ድልድይ ስር ቦንብ ፈንድቶ በ1 ግለሰብ ላይ የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል። * የታረመ @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

በአዲስ አበባ ወድቆ የተገኘ ቦንብ ፈንድቶ በ 1 ግለሰብ ላይ 'ቀላል የአካል ጉዳት' ማድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ዛሬ ጥዋት 2፡00 ሰዓት አካባቢ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው አድዋ ድልድይ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ነው ጉዳቱ የደረሰው።

በደረሰበት ጉዳት በምኒልክ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተለ የሚገኘው ግለሰብ የታክሲ ረዳት ሲሆን ለመፀዳዳት ወደ ድልድዩ እንደገባ እና በማዳበሪያ የተጠቀለለ እቃ ተመልክቶ በእግሩ ሲረግጠው ከዚያ በኋላ ራሱን እንደሳተ ተናግሯል፡፡

Via Addis Ababa Police Commission
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia