TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ግንቦት

ታሪክን መለስ ብለን ስናይ፦

√የውጫሌ ውል የተፈረመው በግንቦት ወር ነው።

√ለንግስና ያልበቁት ልጅ እያሱ በሚኒሊክ የተሾሙት በግንቦት ወር ነው።

√በደረሰባቸው የመኪና አደጋ ከዚህ አለም በሞት የተለዩት ልዑል መኮንን ኃይለስላሴ በግንቦት 1949 ነው።

√ኮ/ሌ #መንግስቱ_ኃይለማርያም የተወለዱት ግንቦት 19 ነው፤ መፈንቅለ መንግስት የተሞከረባቸው ግንቦት 8 ሆኖ ግንቦት 13/1983 ደግሞ ሀገራቸውን ጥለው የተሰደዱበት ቀን ነው።

ግንቦት 11/1982 ዓ.ም 12 ከፍተኛ ጀኔራሎች #የተገደሉበት ቀን ነው።

ግንቦት 20 ኢህአዴግ አዲስ አበባን የተቆጣጠረበት ቀን ነው።

√የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ #መለስ_ዜናዊ የተወለዱት ግንቦት 1 ነበር።

ግንቦት 7/1997 በኢትዮጵያ የብዙሃን ፓርቲ ምርጫ የተካሄደበት ነበር።

ግንቦት 18/1999 በደርግ ከፍተኛ አመራሮች ላይ ሞት የተፈረደበት ቀን ነው፤ ግንቦት 24/2003 የሞት ፍርዱ ወደ እድሜ ልክ የተለወጠበት ቀን ነው።

ግንቦት ታሪካዊ ናት!

Via ሌ/ኮሎኔል ፍስሃ ደስታ/አብዮቱና ትዝታዬ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጥቆማ

° በኢትዮጵያ 1.1 ሚሊዮን ህጻናት መደበኛ ክትባት ወስደው አያቁም።

° የአለም የህጻናት አድን ድርጅት ከክትባት ጋር የተያያዘ ችግሮችን የሚፈቱ የፈጠራ ስራዎችን እያወዳረ ነው።


አፍሪካ በዓለም ' ዜሮ ዶዝ ' ህፃናት ከሚገኙባቸው አህጉራት በቁጥር ከፍተኛውን ደረጃ ትይዛለች። ይህም ማለት መደበኛ ክትባት ወስደው የማያውቁ 8.7 ሚሊዮን ህፃናቶች አሉ ማለት ነው፡፡

ከእነዚህ ህፃናት ውስጥ ከአንድ ሦስተኛ በላይ የሚሆኑት የሚኖሩት በናይጄሪያ እና ኢትዮጵያ ውስጥ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ 1.1 ሚሊዮን ህጻናት መደበኛ ክትባት ወስደው አያቁም።

በተጨማሪም ወረርሽኝ ፣ ድህነት ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ፣ አለመረጋጋት፣ ግጭቶችናና ተያያዥ ምክንያቶች የክትባት መርሃግብሮችን እየተስተጓጎሉ ይገኛሉ።

የዓለም የህጻናት አድን ድርጅት (ሴቭ ዘ ችልድረን) እና ጂኤስኬ በመተባበር የክትባት አቅርቦትን እና አጠቃቀምን በተመለከተ ማንኛውንም አይነት ከክትባት ጋር የተያያዘ ችግሮችን የሚፈቱ የፈጠራ ስራዎችን በማወዳደር ላይ እንደሚገኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ ጠቅሷል።

የተመረጡ ኃሳቦች / ሥራዎች በፕሮጀክት እስከ 100,000 ዶላር የሚደርስ የገንዝብ እንዲሁም የቴክኒክ ድጋፍ ይደረግላቸዋል ተብሏል።

ለማመልከት www.stc-accelerator.org ይጎብኙ።

የማመልከቻ ቀን እስከ #ግንቦት_16 ቀን 2016 ዓም ድረስ ነው።

ሁለተኛው የፈጠራ ጥሪ በ2017/2025 የሚካሄድ ይሆናል።

@tikvahethiopia